• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል?

January 13, 2021 04:10 am by Editor 2 Comments

ከህወሀት መደምሰስ በኋላ የብልጽግና ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥያቄ ኢትዮጵያውያን መጠየቅ የጀመሩት የአገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን መቆጣጠሩን የሚያበስረው ዜና ከተሰማ ሰአት አንስቶ ነው።

ከዚህ የድል ዜና በኋላ ብዙዎች የዜጎች መፈናቀል እና የፖለቲካ ትኩሳት የሚፈጥራቸው አሰቃቂ ክስተቶችን ከመስማት እንገላገላለን በሚል ተስፋ አድርገው ነበር።

ለመሆኑ አገር እየመራ ያለው የቀድሞው ኢህአዴግ የአሁኑ ብልጽግና ፓርቲ ከህወሀት መደምሰስ በኋላ ፈተናዎቹ ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ በሚል ኢትዮ ኤፍ ኤም በፖለቲካ ነክ ጉዳዮች ላይ ትንታኔ በመስጠት ከሚታወቁት ዶክተር አለማየሁ አረዳ ጋር ቆይታ አደርጓል።

እንደ ዶ/ር አለማየሁ ገለጸ ህወሀት በአካል ቢወገድም የዘረጋው አጠቃላይ ስርአት፣አስተሳሰቡና የመንፈስ ልጆቹ የገዢው ፓርቲ ፈተና ይሆናሉ ብለዋል።

ይህ እንዳለ ሆኖ “ዋናው የብልፅግና ቀጣይ ፈተና ራሱ ብልፅግና ነው” ብለዋል ዶክተር አለማየሁ።

የተወሰነ መረጃ እንዳገኘሁት ከሆነ ይላሉ ዶ/ር አለማየሁ ብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔውን አድርጎ ፕሮግራሙንና መታዳደርያ ደንቡብ አላፀደቀም።

የኢህአዴግ የነበረው በሙሉ ተገልብጦ ብልፅግና እንዲባል፣ አባላቱም ልክ እንደ ጃኬት ተገልብጠው ነው የመጡት ሲሉ ተናግረዋል።

የሚቀጥለውን ምርጫ እንዳሉ እነሱ በፌደራልም፣ በክልልም ተመርጠው ፤ ስልጣን ለመያዝ ተዘጋጅተዋል፤ ሽንፈት የመቀበል ስነ ልቦናዊ ዝግጅቱም ያላቸው አይመስሉም ብለዋል።

እነዚህ የብልፅግና ካድሬዎች ምን ያህል የጠራ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ አላቸው? ምን ያህልስ ለውጡን ተገንዝበውታል? ምን ያህልስ ለህዝቡ ተገቢ አመራር የመስጠት አቅም አላቸው?

የሚለው አጠራጣሪና ለፈተና ያልቀረበ ነው ያሉ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ስለ በጋራ ስለ መኖር፣ ስለ አንድነት፣ ስለ ዴሞክራሲ፣ በጋራ ስለ መበልፀግ፣ የምንሰማው ከዶ/ር አብይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሌሎቹ ካድሬዎች ባሉበት ነው ያሉት የሚሉት ዶ/ር አለማየሁ፤ በየክልሎቹ ያሉት የብልፅግና ቅርንጫፎች እውነት ለሌሎች ፓርቲዎች ሰፊ የመጫወቻ ሜዳ ይለቃሉ? የሚለው በጣም አጠራጣሪ ነው ብለዋል።

ሌላው ይላሉ ዶ/ር አለማየሁ፤ ሌላው ትልቁ በጥበብ ሊፈታ የሚገባው ቀጣዩ የገዢው ፓርቲ ፈተና ፤ የእነ ወላቃይትና ራያ ጉዳይ ነው ብለዋል።

አካባቢዎቹ ነፃ ወጥተናል ሲሉ አውጀዋል፤ የህግ የበላይነትን ለማስከበር የተካሄደ ዘመቻ መሆኑ መዘንጋት የለበትም ይላሉ።

ምርጫው እየቀረበ ሲሄድ ጥያቄዎቹ እየከረሩ ሲሄዱ ለመንግስትም ለድንበር ኮሚሽኑም ትልቅ አጣቢቂኝ ነው የሚሆነው ብለዋል።

በቃ ህወሀት ተወግዷል በሚል ከትግራይ ክልል ነጥቆ አማራ ክልል ውስጥ ማስገባት በዛ በኩል የሚያስከፋው ህዝብ ስለሚኖር ፍትሀዊ አይደለም። በሌላ በኩል ህወሀት ለዘመናት በቅኝ እንደያዛቸው አድርጎ ሲያስተዳድራቸው የነበረው፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት እስከ ዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፀምባቸው የኖረውንና ማንነታችንን ተነጥቀናል፤ የሚሉትን ዜጎች በቃ እንደ ከዚህ ቀደሙ ቀጥሉ ማለትም ተገቢ አይደለም፣ህዝቡ ነቅቷል።

ከዚህ በመለስ ለትግራይ፣ከዚህ በመለስ ደግሞ ለማራ ብሎ ሸንሽኖ ማከፍፈልም አይሆንም፤ሲሉ ተናግረዋል።

እነዚህ አካባቢዎች ኢህአዴግ ስልጣን ከመያዙ በፊት የትኛው አስተዳደር ስር ነበሩ፣ የህዝቡስ ፍላጉትና ስነ ልቦና (Psychological makeup)፣ ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ለዲሞግራፊ ተብሎ ስለ ሰፈሩ ህዝቦች፤ የሚሉትና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ የአማራ ክልልና የትግራይ ክልል ፌዴሬሽን ምክር ቤትም የሚመለከተው ሁሉ ቁጭ ብለው መነጋገር አለባቸው ያሉ ሲሆን እስከ ምርጫው ግን ግዛቶቹ በፌደራል መንግስት ስር ያሉ ልዩ አስተዳደሮች ተመስርቶላቸው ነው መቆየት ያለባቸው፣ የሽግግርና ፋታ መውሰጃ ጊዜ ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል ዶክተር አለማየሁ።

በቅድሚያ መተማመን መፈጠር አለበት ብለዋል።

ሌላው ሙሉ በሙሉ በኦነግ ሸኔ የሚላከከው፤ የመተከልና ሌሎች ኦሮሚያ ክልል ላይ በተለይ አማራ ላይ የሚፈፀሙ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች፤ ራሱ ብልፅግና በተለይ ፤ የኦሮሚያ ክንፍ ሊፈተሽባቸው የሚገቡ ወንጀሎች ናቸው ብለዋል።

ሸኔ ተደመሰሰ ሲባል ተማረከ ተብሎ የምንሰማው 7 ክላሽና 30 ኋላ ቀር መሳርያ ነው፤ ይሄ የሚያሳይህ ምን ያህል ደካማ ሀይል እንደሆነ ነው፤ መንግስት አቅቶት ሳይሆን ራሱ ገዢው ፓርቲ ውስጥ የሚገኙ ለኦነግ ሸኔ የሚያደሉ በልፅግና ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በቁጥር ትንሽ ስላልሆኑ ነው ብለዋል።

የኦሮሚያ የፖለቲካ አሰላለፍ ጥናት ይፈልጋል ያሉት ዶክተር አለማየሁ ግብፅን የመሰሉ የውጪ ሀይሎችም፤ከፍተኛ ገንዘብ የሚያፈሱበት ነው ብለዋል።

ለዶ/ር አብይ መንግስት ትልቅ ራስ ምታት ቤንሻንጉል ነው የሚሉት ዶ/ር አለማየሁ አልጀዚራ ላይ አንድ የግብፅ ሰው ቤንሻንጉል የሚባል ቦታ አለ፣ በዛም መግባት እንችላለን ሲል እንደነበር አንስተዋል።

በመጨረሻም ፤ ዶ/ር አለማየሁ ፤ ብልፅግና ራሱን እንዲያጸዳ ያሳሰቡ ሲሆን ፤ ግልፅ አቋምና ፍኖተ ካርታ እንጂ ለሁሉ ነገር ግብረ ሀይል አያስፈልገውም ሲሉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

በመጀመርያ ደረጃ ራሱ ብልፅግና ፓርቲ ኢህአዴግ ያለበሰውን ጥብቆ አውልቆ መለወጥ አለበት ይላሉ ዶ/ር አለማየሁ።

ከስር ያለው የፓርቲው መሰረት እላይ ባለው አመራር ዝም ብሎ የሚጎተት ይመስላኛል ብለዋል።

ምንድነው ግብረ ሀይል ማብዛት ሲሉ የሚጠይቁት ዶ/ር አለማየሁ ዋናው እና መሰረታዊ የሆነው የሀገራችንን ፖለቲካዊ ጥያቄ በዘላቂነት ለመፍታት ነው ገዢው ፓርቲ መሞከር ያለበት ብለዋል።

ዶ/ር አብይ የሚሰራውን አምስት በመቶ የሚሰራ ብልፅግና ውስጥ የለም ያ ሲሆን ፕሮግራሙና መተዳደርያ ደንቡ አለመፅደቁን የማያውቅ የማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳለ አውቄያለሁ። ሌላ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ደግሞ ጸድቋል ይለኛል። ሁለቱም ደግሞ የኢህአዴግ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ነበሩ ሲሉ ትዝብታቸውን ገልፀዋል።

እነዚህ ምርጫ ሲመጣ እኛ እኮ ብልፅግና ነን ወደ የትም አንሄድም ነው የሚሉን ያሉ ሲሆን ብልፅግና ቀጣዩን ፈተናውን ለመሻገር በጠራ አስተሳሰብና በጠራ ፍኖተ ካርታ መንቀሳቀስ አለበት ሲሉ ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

(ሔኖክ አስራት፤ ኤፍ ኤም 107.8)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Politics, Right Column

Reader Interactions

Comments

  1. Gashaw yismaw says

    March 15, 2021 09:03 am at 9:03 am

    በጥም ጥሩ አቅርቧል ሌላ ትንታኔዎችን እንጠብቃለን

    Reply
  2. wendwesen mekonen says

    May 15, 2021 01:30 pm at 1:30 pm

    I like this page

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule