
የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመሰባሰብ በአማራ ክልል የመስተዳደር ጥያቄያቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ በህዝባዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።
የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመገኘት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ጥያቄያችን የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ አደባባይ በመውጣት ድምፃቸወን አሰምተዋል።
ነዋሪዎቹ በህወሃት የግፍ አገዛዝ በጉልበት ወደትግራይ ክልል ተካለው ሲፈፀምባቸው የቆየው ግፍ ይበቃል ብለዋል።
በዚህ የህልውና ጉዳይ በሆነው የህዝብ ትእይንት የተገኙት የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሠብሳቢ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መልእክት አስተላልፈዋል።

ኮሎኔል ደመቀ ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጅ ሠጥተን አንጠይቅም ብለዋል። አሁንም ቢሆን በወልቃይት ጉዳይ ሌላ ጁንታ አይኖርም ብለን ሳንዘናጋ ሁላችንም የጀመርነውን አጀንዳ ከግብ ማድረስ ይኖርብናል ብለዋል።
በህዝባዊ ሰልፉ እየተላለፉ ከሚገኙት መልዕክቶች መካከል የማይካድራን ዘር ጭፍጨፋ የፈፀሙት የትህነግ ህገወጥ አባላት በጦር ወንጀል ይጠየቁ፤ ሱዳን የመሸጉት የማይካድራ ጨፍጫፊዎች ተላልፈው ለህግ ይቅረቡ፣ በቋሚነት ወደ አማራነታችን ተመልሰናል፣ ተጭኖብን ወደኖረው የትግራይ አስተዳደር ላንመለስ ነፃ ወጥተናል፣ የማይገባንን አልፈን አንጠይቅም፤ የራሳችንም አሳልፈን አንሰጥም፤ ማንነታችን አማራ፣ ድንበራችን ተከዜ ነው የሚሉና ሌሎች ይገኙበታል። (ሀብተጊዮርጊስ አበይ፤ አብመድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply