የኢትዮጵያ ህዝብ በጉያው ተሸሽገው የአሸባሪውን ሀገር የማፈረስ ሴራ እያስፈፀሙ ያሉ የወያኔ ተላላኪዎችን መንጥሮ ማውጣት እንደሚገባው የዲሞክራሲ ተሟጋቹ አቶ ነዓምን ዘለቀ አስታወቁ። የአርበኞች ግንቦት ሰባት መስራችና የዲሞክራሲ ተመጓቹ አቶ ነዓምን ዘለቀ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ አሸባሪው የህወሓት ቡድን መለዮ አልብሶ ካሰማራቸው አራዊት መንጋዎች በተጨማሪ በህዝቡ ጉያ ተሸሽገው የሽብር ሥራውን የሚያስፈፅሙ ተላላኪዎችን በስፋት በማንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።በተለይም በከተሞች አካባቢ በህቡዕ ያደራጃቸው እነዚሁ ፀረ ሰላም ኃይሎች የሃሰት ወሬ በማሰራጨት የህዝቡን ስነልቦና የሚሰርቁ አሉባልታዎችን በማራገብ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም ህዝቡ የአሸባሪውን ተላላኪዎች እንቅስቃሴ በንቃት መከታተልና መንጥሮ በማውጣት በህግ ተጠያቂ ሊያደርጋቸው ይገባል። እንደአቶ ነዓምን ገለፃ፤ ኢትዮጵያን … [Read more...] about “ከምርጫ 97 በኋላ የወያኔን ሴራ የሚያስፈፅሙ የክልሉ ተወላጆች 100ሺ ጠመንጃ እንዳከፋፈለ እናውቃለን”
Middle Column
“በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለም፤ በነጭ ፕሮፖጋንዳ ሀገርን በማፍረስ ተግባር የተጠመዱ” ላይ መንግሥት የማያዳግም ርምጃ ይወስዳል
በነጭ ፕሮፖጋንዳ ሀገርን በማፍረስ ተግባር የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት አሳሰበ፡፡ በነጭ ፕሮፖጋንዳ ሀገርን በማፍረስ ተግባር የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳሰበ፡፡ በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለም ያለው አገልግሎቱ ከዚህ ድርጊታቸው በማይቆጠቡት ላይ መንግስት የማያዳግም ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡ መላው ህዝብ ኢትዮጵያን የማዳን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኝ መሆኑን ተገንዝቦ የጀመረውን ሀገር የማዳን ንቅናቄ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል፡፡ "ዋስትናችን ህልውናችንን በአንድነት ማረጋገጥ መሆኑን በመረዳት" በአፍራሽ ኃይሎችና ግብረ አበሮቻቸው በኩል የሚነዙ መርዛማ ወሬዎች የሚመጡበትን መንገድ መዝጋት እንደሚገባም ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያውያንና የወዳጅ ሀገራት ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ ትክክለኛውን … [Read more...] about “በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለም፤ በነጭ ፕሮፖጋንዳ ሀገርን በማፍረስ ተግባር የተጠመዱ” ላይ መንግሥት የማያዳግም ርምጃ ይወስዳል
በቤኒሻንጉል ከትህነግና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 98 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 98 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመውጣቱ አስቀድሞ የክልሉ ፖሊስ የተጠናከር የክትትል ስራ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ኮሚሽነሩ እንዳሉት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ወጥቶ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የጸደቀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የክልሉን ሠላም ለማስጠበቅ ለፀጥታ አስከባሪ ኃይሉ ተጨማሪ አቅም ሆኖታል። ግለሰቦቹ በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉት ከአሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደነበራቸው ፖሊስ በደረሰው መረጃ መሰረት ከጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባደረገው ኦፕሬሽን ነው ብለዋል፡፡ አሸባሪው … [Read more...] about በቤኒሻንጉል ከትህነግና ሸኔ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የነበራቸው 98 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የመቀሌ አየር ድብደባዎች ዒላማቸውን የመቱ ናቸው
የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎች ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎች ላይ ብቻ እንደሆነና ኢላማቸውን የመቱ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገጽ ባወጣው መግለጫ፤ የመከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸውን የአየር ድብደባዎች በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው ብሏል። የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው ሲልም አስታውቋል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የመቀሌ አየር ድብደባዎች ዒላማቸውን የመቱ ናቸው
ትህነግ የዛሪማን መስጊድ አወደመ
አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የዛሪማ መስጊድን በከባድ መሳሪያ ደብድቦ ማውደሙን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አረጋ ገጠ። አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመው ድርጊትም የሰዎችን እምነት የሚጋፋ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል። የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሀጂ ሙሀመድ ሀሰን፣ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፣ በሰሜን ጎንደር ውስጥ በሚገኘውና በቅርብ በተገነባው የዛሪማ መስጊድ ላይ በከባድ መሳሪያ ተኩሶ መስጊዱን በከፊል አውድሟል። በአካባቢው አሸባሪው ቡድን ሸሽቶ ጫካ በመግባቱና ደብቆ ባከማቸው የከባድ መሳሪያ ከርቀት በማስወንጨፍ በዛሪማ መስጊድና በአካባቢው በሚገኙ ቤተ-እምነቶችና ንፁሀን ላይ ጉዳት እያደረሰ እንዳለ ገልጸዋል። አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመው ተግባርም ለእምነት ክብር እንደማይሰጥ አንዱ ማሳያ መሆኑንም … [Read more...] about ትህነግ የዛሪማን መስጊድ አወደመ
እያፈገፈገ ያለውን ሽፍታ የሚመራው ፃድቃን ጦርነቱ “በቀናት፣ ግፋ ቢል በሳምንታት ይጠናቀቃል” አለ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ አማጺ ሃይል መሪ የሆነው ጻድቃን ገብረትንሳይ ጦርነቱ እንደማይራዘም አመለከተ። አዲስ ተጀመረ የተባለውን ጦርነት “የቀናት ጉዳይ ነው፣ ግፋ ቢል በሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል” ሲል የተናገረው ለኒውዮርክ ታይምስ ነው። የትግራይ ሕዝብ የዕድሜ ልክ ጠላት ሲሉ የጠራቸው ኢሳያስ መወገድ እንዳለባቸው ለዓለም ማህበረሰብ አስታውቋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እስካሁን ማጥቃት አለመጀመሩን፣ ነገር ግን ዝግጅቱን አጠናቆ መመሪያ እየጠበቀ መሆኑንና ማጥቃት ከጀመረ “ድረሱልኝ” የሚል ጊዜ የሚሰጥ እንዳልሆነ ከዚህ በፊት ሲነገር ነበር። ትህነግ ያወጣውን የድረሱልኝ ጥሪ ተከትሎ መከላከያ ይህንን ቢልም የተለያዩ ሃላፊዎችና ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ደጋግመው ጥቃት መጀመሩን እያስታወቁ ነው። የአየር ሃይል አዛዥም በባንዲራ ቀን አየር ኃይል “ጠላትን … [Read more...] about እያፈገፈገ ያለውን ሽፍታ የሚመራው ፃድቃን ጦርነቱ “በቀናት፣ ግፋ ቢል በሳምንታት ይጠናቀቃል” አለ
መረን የለቀቀ ግፍ፤ በዛገ በርሜል የተሠራ የጎመንዘር ዘይት ለሕዝብ
በሻሸመኔ በህገወጥ መንገድ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረተ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ ድርጅት ታሸገ። በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ከሻሸመኔ ጤናና ጤና ነክ የስራ ሂደት ተቆጣጣሪ ጋር በጋራ በመሆን በኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የደቡብ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በምግብ ዘይት ላይ የገበያ ቅኝት መሥራቱን የኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል። በዚህም ቅኝት ከሚመለከተው የተቆጣጣሪ አካል የዘይት ምርት ለማምረት የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው፣ የምርት ማሸጊያ መስፈርት ባላሟላ፣ ንጽህናዉ ባልጠበቀ የአመራረት ሂደት እንዲሁም ዘይት ለማምረት ምቹ ባልሆነ ቤት ውስጥ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረቱ ለህብረተሰቡ እየሸጠ የተገኘ አንድ ድርጅት ላይ ምርት የማምረት ሥራዉን እንዲያቆሙና ድርጅቶቹ ከተመረተው የዘይት … [Read more...] about መረን የለቀቀ ግፍ፤ በዛገ በርሜል የተሠራ የጎመንዘር ዘይት ለሕዝብ
የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኃይል ለማመንጨት የሚረዳ ግንባታ ሊጀመር ነው ተባለ
የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኢነርጂ ከመሬት ውስጥ እንፋሎት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል ፕሮጀክት ሲሆን፣ የሀይል ማመንጫ ግንባታውን ለማካሄድ መታቀዱን በቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኢነርጂ ድርጅት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ነዚፍ ጀማል ገልጸዋል። ነዚፍ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት ይህንን ግንባታ ለማካሄድ ጨረታ የወጣ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የሀይል ማመንጫው ቁፋሮ ላይ የሚገኝ የግንባታ ሂደት ነው ብለዋል። በፈረንጆች 2020 የወጣው የመጀመሪያ ጨረታ ሰባት ትልልቅ አለም አቀፍ የተርባይን አምራች ድርጅቶች መወዳደራቸውንና በአሁኑ ሰዓት ኹለት ድርጅቶች ስራውን ተቀብለው ለመስራት እየተጠባበቁ መሆናቸውን ነዚፍ ጠቁመዋል። በአሁኑ ሰዓት ጨረታው ላይ በቀረበው የቴክኒክ ብቃት መሰረት ከሰባት ድርጅቶች ውስጥ ኹለት ብቻ የቀሩ ሲሆን፣ በዋናነት ግንባታውን የሚያካሂደው እና በተጠባባቂነት ያለው … [Read more...] about የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኃይል ለማመንጨት የሚረዳ ግንባታ ሊጀመር ነው ተባለ
በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅብንም
አንድ ሀገር በግዛቷ ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ የመወሰን መብቷ የተጠበቀ ነው፤ የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን ውሳኔውን ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅበትም ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ። አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከተልዕኳቸው ውጪ ሲንቀሳቀሱ ከአገር እንዲወጡ የተደረጉ የተመድ ሰራተኞችን በተመለከተ ለጸጥታው ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል። አምባሳደሩ በሰጡት ማብራርያ “የዛሬው ስብሰባ መነሻ ምክንያት የአንድን ሉዓላዊት ሀገር ውሳኔ የሚጋፋ የመወያያ አጀንዳ መፍጠሩ ተገቢ ካለመሆኑ በላይ ራስን በራስ በማስተዳደር በተወሰነ ውሳኔ ላይ እንዲሁም በሉዐላዊት አገር ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው” ብለዋል። በዓለም አቀፍ ህጎች መነሻነት ኢትዮጵያ ውሳኔውን መወሰኗንም አስታውቀዋል። የተለያዩ አገራት በተለያየ … [Read more...] about በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ማን እንደሚገባ፣ እንደሚወጣና እንደሚቆይ ለማንም ማሳወቅ አይጠበቅብንም
ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚደነግጡት መቼ መቼ ነው?
የኢትዮጵያ መንግስት በውስጥ ጉዳዬ ላይ ገብተዋል፣ ከተፈቀደላቸው ዓላማና ተግባር ውጭ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል ያላቸውን 7 በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ ግከለሰቦችን በ72 ሰአታት ውስጥ የኢትዮጵያን ግዛት ለቀው እንዲወጡ ሲል አዟል። ይህንን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ “በኢትዮጵያ ውሳኔ ደንግጫለሁ” ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ በአሸባሪው ህወሓት በርካታ ንጹሀን ሲገደሉ፣ ከ400 በላይ መኪናዎች በአሸባሪው ድርጅት ታግተው ሲቀሩ፤ አሸባሪው ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራሁ ነው ሲል ድምጻቸውን አጥፍተው አሁን ላይ መንግስት የአገር ሉአላዊነትን በተጋፉ የድርጅቶቱ ሰራተኞች ላይ እርምጃ ሲወስድ ደንግጫለሁ ማለታቸው ተገቢነት የጎደለው ነው ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ … [Read more...] about ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚደነግጡት መቼ መቼ ነው?