
ሁሉም የፌዴራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሥርዓትን ሊጠቀሙ ነው
በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ሁሉም የፌዴራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሥርዓትን ይጠቀማሉ ሲል የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
የባለሥልጣኑ የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሲስተም ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ታደሰ ከበደ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ እስካሁን ባለው ጊዜ ውስጥ በሲስተሙ ከ25 በላይ የሚሆኑ ጫረታዎች ወጥተዋል፡፡ በቀጣይ ሁለት ዓመታት የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ ይሰራል፡፡
በቀጣይ ሥርዓቱን ወደ ክልሎች በማውረድ ይሰራል ያሉት አቶ ታደሰ፤ በ2015ና 2016 በጀት ዓመት መጨረሻ ድረስ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ጨረታዎችን የሚያወጡትና ግዥዎችን የሚያከናውኑት ሲስተሙን በመጠቀም ይሆናል ብለዋል፡፡ በዚህም እንደ አገር ያለውን የተበላሸ የግዥ ሥርዓት ማስተካከል እና የአገርንም ሀብት ከስርቆትና ከብክነት ማዳን ይቻላል ብለዋል፡፡
እንደ ማናጀሩ ገለጻ፤ በ2014 በጀት ዓመት ብቻ የኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሲስተምን በመጠቀም 66 መስሪያ ቤቶች ዓመታዊ የግዥ እቅዳቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም በ2014 በጀት ዓመት ሰባት መስሪያ ቤቶች ሃያ ሁለት ጨረታዎችን በኦንላይን ሲስተም አውጥተው ለተጫራቾችይፋ አድርገዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የመንግስት ግዥን በኤሌክትሮኒክስ መፈጸም የንግዱን ማህበረሰብ የሚጠቅምና ጤናማ ውድድር እንዲኖር በማድረግ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን እንደሚያስድግ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አሰታወቀ።
የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ በነገው ዕለት ከአቅራቢዎች ጋር የምክክር መድረክ ይካሄዳል፡፡
የምክክር መድረኩን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃጂ ኢብሳ እንደገለጹት፣ በነገው እለት ከግሉ ዘርፍ አቅራቢያዎች ጋር ውይይት ይካሄዳል። በምክክር መድረኩ ከአንድ ሺህ በላይ አቅራቢያዎች ይሳተፋሉ ብለዋል።
የንግዱን ማህበረሰብ የሚጠቅምና ጤናማ ውድድር እንዲኖር በማድረግ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል።
የኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ግዥን ያደጉ አገሮች መጠቀም ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ ውጤት ሆነዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በአሁኑ ጊዜ 72 የፌደራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ስርአቱን መጠቀም ጀምረዋል።
የኤሌክትሮኒክስ የግዥ ሥርዓት ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ሲውል ብልሹ አሰራርን በመቀነስ ለአገር እድገት ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋልም ብለዋል።
ነገ ከሚካሄደው የውይይት መድረክ በኋላ የንግዱ ማህበረሰብ የሚያወጡትን ግዥዎችን በግልጽ ያወጣሉ፣ ተጫራቾችም በግልጽ ይጫረታሉ፤ 24 ሰአት ሙሉ መጫረት ይችላሉ፣ ሁሉም ተጫራች ባለበት ቦታ መጫረት ስለሚችል ከፍተኛ የወጭ ቅነሳ ይኖረዋል።
እስከቀጣይ አምስት አመት ድረስ በሁሉም ክልሎች ያሉ ተቋማት፣ እስከወረዳ ድረስ ወደ ሲስተሙ ይገባሉ ብለዋል። (EPA)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply