በትግራይ ክልል በስምንት ቡድኖችና አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረው የሕወሓት ቡድን ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን፣ በአገር መከላከያ ሠራዊት የደቡብ ግንባር ዋና አዛዥ ሌተና ጄኔራል ባጫ ደበሌ ማክሰኞ ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡ “በትግራይ ውስጥ በስምንት ቡድኖች የተደራጀ ኃይል በአንድ ጊዜ ለመደምሰስ በሠራዊታችን ዘመቻ ተደርጎበታል፡፡ አካባቢዎቹም በምሥራቅ ትግራይ አፅቢ፣ ሐይቅ መሳል፣ ደሴአ፣ በደቡብ ትግራይ ዋጅራት፣ ቦራ፣ በሰሜን ምሥራቅ ትግራይ ጽጌረዳ፣ ሐውዜን፣ እንዲሁም በሰሜን ትግራይ ውቅሮ ማርያም፣ ዛና ናቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ሰፋ ያለ የጥቃት ድርጊት ሲፈጽሙ ስለነበር ወታደራዊ ዘመቻ ተካሂዶባቸው ተደምስሰዋል” ሲሉ ጄኔራል መኮንኑ አስረድተዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ሠራዊቱ ባደረገው ዘመቻ ትንንሽ ማሠልጠኛዎችንና የሕወሓት መሪዎችን እንደ ጠባቂ … [Read more...] about “ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቀሌና አዲስ አበባ አይገቡም” ጄኔራል ባጫ
Archives for April 2021
የስኳር ፋብሪካዎች ተሽጠው ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ተወሰነ
በመንግሥት ባለቤትነት ሥር ከሚገኙት 13 ስኳር ፋብሪካዎች ውስጥ አሥሩ ለግል ባለሀብቶች ተሸጠው፣ ከሽያጩ የሚገኘው ገቢ በከፍተኛ የዕዳ አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው ተብለው ለተለዩ ሰባት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዕዳ ክፍያ ጥቅም ላይ እንዲውል ተወሰነ። ሪፖርተር ያገኘው መንግሥታዊ መረጃ እንደሚያመለክተው ሰባቱ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ካለባቸው አጠቃላይ ዕዳ ውስጥ፣ አመዛኙ እንደ አዲስ ወደ … [Read more...] about የስኳር ፋብሪካዎች ተሽጠው ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ተወሰነ
“ኤርትራዊ ነን” በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ የኖሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ
ጀርመን መረጃ መጠየቅ ጀምራለች “የማንፈልገው ጉዳይ ውስጥ እየገባን ነው” ይላሉ ዜናውን ያረጋገጡት ዲፕሎማት። ተቀማጭነታቸው አውሮፓ የሆነው የጎልጉል የዘወትር ተባባሪያችን እንዳሉት አንዳንድ አገራት የስደተኞች መረጃ ለመጠየቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ጀርመን ወደ ሥራ ገብታለች። በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ድንበር አካባቢ ባሉ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ በተመዘገቡ ስደተኞች ስም በርካታ የትግራይ ተወላጆች “ስደተኛ ናቸው” በሚል ከአገር እንዲወጡ መደረጉን እንደ አንድ ምክንያት ጠቅሰው የዓለምአቀፉ የስደተኞች ተቋም ትግራይ ድንበር 20 ኪሎ ሜትር ላይ ያሉት ካምፖች እንዲዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው ጥያቄው የተነሳው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ንግግራቸው የኤርትራን ወደ ትግራይ መግባት አስመልክቶ ሲናገሩ ይህንኑ ማለታቸውን ተከትሎ የጀርመን … [Read more...] about “ኤርትራዊ ነን” በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ የኖሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ
ምርጫ ቦርድ የኦነግን ጥያቄ ውድቅ አደረገ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች መካከል በተፈጠረ መከፋፈልና ውዝግብን የተመለከቱ እግዶች፣ አቤቱታዎችና ከሁለቱም ወገን የሚመጡ ማሳወቂያ ደብዳቤዎችን ሲቀበል መቆየቱ እንዲሁም ችግሩን ለመፍታት ቡድኖቹን በተናጠል እንዲሁም የፓርቲውን የስነስርአትና የቁጥጥር ኮሚቴን በማነጋገር ያሉትን አስተዳደራዊና ህጋዊ መንገዶች ሁሉ እንደተጠቀመና መፍትሄዎችን ለመስጠት ጥረት ሲያደርግ እንደነበር አስታውሶ፣ በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት ፓርቲው ካለበት ችግር ብቸኛ መውጫ መንገድ መሆኑን በመረዳትና በውዝግብ ውስጥ ያሉ አመራር ክፍሎችም ያመኑበት በመሆኑ፣ በአመራሮች መካከል ያለው ችግር በጠቅላላ ጉባኤ እንዲፈታ መወሰኑ ይታወሳል። ኦነግ መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በቁጥር 19/ABO/2013 በተጻፈ ደብዳቤ ድርጅቱ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጠቅላላ … [Read more...] about ምርጫ ቦርድ የኦነግን ጥያቄ ውድቅ አደረገ
“እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ መንግሥት ኮሮጆ አይሰርቅም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
መንግሥት በምርጫ ዙሪያ በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ካድሬ እስካለፈው እሑድ ድረስ ማሠልጠኑን፣ ማክሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በተካሄደው የአዲስ ወግ ውይይት ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረው፣ ዘንድሮ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው አገራዊ ምርጫ ፓርቲያቸው ብልፅግና ከተሸነፈ ሥልጣን ለማስረከብ ዝግጁ መሆኑን አስታወቁ። “እንደ ብልፅግና ፓርቲ ከተሸነፍን ሥልጣን ለማስረከብ ተዘጋጅተናል። ይህንን ካደረግን ደግሞ ከምርጫ በኋላ ሰላም የማይኖርበት ምክንያት አይኖርም። አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ካድሬ እስካለፈው ቅዳሜና እሑድ ድረስ ሥልጠና ላይ ነበር። ዋናው መልዕክት ኢትዮጵያ አሸናፊ መሆን አለባት ነው” ብለዋል። ኢትዮጵያ አሸናፊ የምትሆነው ሽንፈት ሲኖር በማመሥገንና መልካም በመመኘት ሥልጣን መስጠት ከተቻለ መሆኑን … [Read more...] about “እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ መንግሥት ኮሮጆ አይሰርቅም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
መንግሥት ካልደረሰልን አሁንም ግድያ ይኖራል – ነዋሪዎች
በምዕራብ ወለጋ ዞን በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ግድያው የተፈጸመው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እያለ መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ “እኛ የፖለቲካ ሰዎች አይደለንም፤ ገበሬዎች ነን ፤ መንግስት ለምን አይደርስልንም?” ብለዋል። በኦሮሚ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ፣ ቦኔ ቀበሌ፣ ትናንትናምሽት 3 ሰዓት ላይ በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የአካባቢ ነዋሪዎችየተናገሩት። ነዋሪዎቹ ፤ አሁን ላይ አስክሬኖች በየቦታው ተጥለው መገኘታቸውን ገልጸው ቁጥሩ ምን ያህል ነው የሚለውን ለመግለጽ አስቸጋሪ እንደሆነ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል። ሕጻናትና ሴቶች አሁን ላይ ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ጫካዎች መግባታቸውንየገለጹት አስተያየት ሰጭዎቹ፤ መንግስት የማይደርስላቸው ከሆነ አሁንም ሌላግድያ ሊኖር እንደሚችል ስጋታቸውን … [Read more...] about መንግሥት ካልደረሰልን አሁንም ግድያ ይኖራል – ነዋሪዎች
በትግራይ ሊዘረፍ የነበረ የእርዳታ እህል ተያዘ
ትግራይ ክልል ሊዘረፍ የነበረ 430 ኩንታል የእርዳታ እህል በህበረተሰቡ ትብብር እና ጥቆማ የትግራይ ፖሊስ ኮሚሽን መያዙ ተሰማ። ከትግራይ መዲና መቀሌ ወደ ምዕራባዊ ዞን 'ሰለክለካ' የእርዳታ እህል ከጫኑ 16 መኪናዎች አንዱ ከህግ ውጭ ወደተባለው ቦታ ሳያደርስ በመቐለ ከተማ የእርዳታ እህሉን ለማራገፍ ሙከራ ሲያደርግ ህብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ ተይዟል። እንደ ትግራይ ፖሊስ መረጃ፥ መኪናው ንብረትነቱ የ "ትራንስ ኢትዮጵያ" ሲሆን የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-9672 የተሳቢው ቁጥር 2848 ኢት ነው። መኪናው ወደ ሰለክለካ 430 ኩንታል እህል ጭኖ እንዲሄድ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በመቐለ ከተማ ሰሜን ክ/ከተማ በሚገኝ የትራንስ መጋዘን በማስገባት ከደላሎች እና ነጋዴዎች ጋር በመነጋገር እህሉ ሊሸጥ ነበር የታቀደው፤ ይህን ለማድረግ በህገወጥ መንገድ 2 ሲኖትራክ መኪና ወደ … [Read more...] about በትግራይ ሊዘረፍ የነበረ የእርዳታ እህል ተያዘ