• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

Archives for December 2020

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ

December 7, 2020 10:31 am by Editor Leave a Comment

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ህዳር 26 እና 27 ቀን 2013 ዓ/ም የሶማሌ ክልል ሸንጎ ምስረታ አካሂዷል። ከአስራ አንድ ዞኖች ተወክለው ወደ  ጅግጅጋ  የሄዱ አባላት የመጀመሪያው የክልላዊ ሸንጎ ስብሰባቸውን ማድረጋቸውን ፓርቲው ገልጿል። የክልሉ ስራ አስፈፃሚ ከሁሉም ዞኖች አንዳንድ ስራ አስፈፃሚ ተካተው እንደገና መዋቀራቸውም ተነገሯል። ላለፉት 11 ወራት በተለያዩ የሶማሌ ክልል የተከፈቱ ቢሮዎች ስራ እንቅስቃሴ በክልል ደረጃ በጅግጅጋ ዋና መስሪያ ቤት መቀመጫ ላይ ተገምግመዋል። እስከአሁን በክልሉ በአጠቃላይ 24 የነ.እ.ፓ. ቢሮዎች ተከፍተው ስራ ላይ እንደሚገኙ ፓርቲው ያሳወቀ ሲሆን እነዚህ ቢሮዎች በክልሉ ማዕከልነት በተዋረድ እንዲሰሩ መደረጉን አሳውቋል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ

Filed Under: Left Column, News

የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው

December 7, 2020 12:38 am by Editor Leave a Comment

የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው

በኦሮሚያ በየጊዜው እያጋጠመ ለሚገኘው የህይወትና ንብረት ውድመት በህወሓት ጁንታና ተላላኪዎቹ የሚፈፀም መሆኑንና ይህንንም ለማስወገድ ብሎም የቡድንን ዕድሜውን ለማሳጠር በ‹ጂ ፒ ኤስ› ቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ እያከናወነ መሆኑን የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መምሪያ አስታወቀ። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ኢንዶክተሬሽን መም ሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር እንዳለ ቁምላቸው ለበሪሳ ጋዜጣ እንደገለፁት፤ የህወሓት ጁንታ እና የኦነግ ሸኔን ሴራ ለማክሸፍና ዕድሜ ለማሳጠር ‹‹ጂ ፒ ኤስ›› ቴክኖሎጂ እየተጠቀመ መሆኑን አብራርተዋል። እነዚህ አካላት ዜጎችን ለምን እንደሚገድሉ እን ደማያውቁ በመጠቆም በህግ ቁጥጥር ሥር ለማዋልም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል። ቴክኖሎጂው እነዚህ አካላት ያሉበትን ቦታ ለመከታተል የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል። በዚህ ቴክኖሎጂ … [Read more...] about የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው

Filed Under: News, Right Column Tagged With: olf shanee, olf shine, operation dismantle tplf

የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ

December 6, 2020 11:41 pm by Editor Leave a Comment

የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ትላንት እሁድ በሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን መጎብኘታቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ “ዛሬ ጠዋት (እሁድ) ኢትዮጵያን ከራስ በላይ ያስቀመጡ በሆስፒታል የሚገኙ ሴት እና ወንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀግኖቻችንን ጎብኝቻለሁ! አገልግሎታችሁን እናከብራለን” ብለዋል። ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ስላደረጉበት ሆስፒታል የገለጹት ነገር የለም። (አል-አይን) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የቆሰሉ ወታደሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጎበኙ

Filed Under: News, Right Column Tagged With: operation dismantle tplf

“ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ

December 2, 2020 12:24 pm by Editor Leave a Comment

“ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ

የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመሰባሰብ በአማራ ክልል የመስተዳደር ጥያቄያቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ በህዝባዊ ሰልፍ ጠይቀዋል። የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሁመራ ነዋሪዎች በዳንሻ ከተማ በመገኘት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ጥያቄያችን የህልውና ጉዳይ ነው ሲሉ አደባባይ በመውጣት ድምፃቸወን አሰምተዋል። ነዋሪዎቹ በህወሃት የግፍ አገዛዝ በጉልበት ወደትግራይ ክልል ተካለው ሲፈፀምባቸው የቆየው ግፍ ይበቃል ብለዋል። በዚህ የህልውና ጉዳይ በሆነው የህዝብ ትእይንት የተገኙት የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሠብሳቢ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መልእክት አስተላልፈዋል። ኮሎኔል ደመቀ ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጅ ሠጥተን አንጠይቅም ብለዋል። አሁንም ቢሆን በወልቃይት ጉዳይ ሌላ ጁንታ አይኖርም ብለን ሳንዘናጋ ሁላችንም … [Read more...] about “ከዚህ በኋላ ይዘን እንታገላለን እንጂ ሠጥተን አንጠይቅም” ኮሎኔል ደመቀ

Filed Under: News, Politics, Right Column, Uncategorized Tagged With: operation dismantle tplf, wolkayit

በመቀሌ መከላከያ የማያውቀው የጦር መሳሪያ ዲፖ ተገኘ

December 2, 2020 12:20 pm by Editor Leave a Comment

በመቀሌ መከላከያ የማያውቀው የጦር መሳሪያ ዲፖ ተገኘ

በመቀሌ ከተማ የጥፋት ሃይሉን አባላትና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል የቤት ለቤት ፍተሻ ተጀምሯል። በዚህም በከተማው የጥፋት ቡድኑ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ዴፖ በብርበራ በሰራዊቱ ተይዟል። በወቅቱም ሶስት ኮንቴነር ጠመንጃ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ጥይቶች፣ ክላሽንኮብ መሳሪያ፣ ስናይፐር፣ አድማ መበተኛ የጭስ ቦምብ እና ፈንጅዎች ተይዘዋል። በተጨማሪም የትግራይ ልዩ ሃይል መለዮና የአባላት መታወቂያዎች መያዛቸውም ታውቋል። ሰራዊቱ አሁን ላይ በሚያካሂደው የፍተሻና ብርበራ የጥፋት ሀይሉ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ በርካታ የጦር መሳሪያዎች እንደሚያገኝም ይጠበቃል ነው የተባለው። ለዚህም የትግራይ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል። በተያያዘ ዜና ከቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊቱ ቁጥጥር ስር በዋለችው መቀሌ ከተማ በተወሰነ መልኩም ቢሆን … [Read more...] about በመቀሌ መከላከያ የማያውቀው የጦር መሳሪያ ዲፖ ተገኘ

Filed Under: Law, News, Right Column, Uncategorized Tagged With: operation dismantle tplf

ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ፤ መፀዳጃቤት የተሸሸገውን ኮሎኔል በቁጥጥር ሥር ያዋለች

December 2, 2020 11:36 am by Editor Leave a Comment

ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ፤ መፀዳጃቤት የተሸሸገውን ኮሎኔል በቁጥጥር ሥር ያዋለች

20ኛ ቃሉ ክ/ጦር ሰሜን ዕዝ ካሏት የጦር ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ ክ/ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው ምክትል አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ገ/ዮሃንስ አጃቢ ነች። የጁንታው ቡድን አባል መሆኑን ግን አታውቅም። ከሃዲው ቡድን የእብሪት ርምጃቸውን ከመጀመሩ ከ3 ቀናት በፊት ሰራዊቱ የምግብና መጠጥ አገልግሎት የሚያገኝባቸውን መንገድ በመዝጋት ሰራዊቱን ለከፍተኛ ርሃብና ጥም እንደዳረገው ም/አስር አለቃ ገበያነሽ ትገልፃለች። አስቀድሞ ሁሉም የሰራዊት አባል የግል ትጥቁን በአንድ ክፍል በማስቀመጥ በህብረተሰብ የድጋፍ ስራዎች ላይ እንዲረባረብ ማድረጉንም ትናገራለች። በተለይም ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ ሁሉንም የጥበቃ ቦታዎች በትግራይ ተወላጅ የሰራዊት አባላት እንዲሸፈኑ በማድረግ፣ የከሃዲው ቡድን ልዩ ሃይልና … [Read more...] about ጀግናዋ ም/አስር አለቃ ገበያነሽ ደባልቄ፤ መፀዳጃቤት የተሸሸገውን ኮሎኔል በቁጥጥር ሥር ያዋለች

Filed Under: Left Column, News Tagged With: operation dismantle tplf

ፌዴራል ፖሊስ መቀሌ ገባ፤ በትግራይ ሰላም እያስጠበቀ ነው

December 2, 2020 11:17 am by Editor Leave a Comment

ፌዴራል ፖሊስ መቀሌ ገባ፤ በትግራይ ሰላም እያስጠበቀ ነው

የአክሱም ጽዮን ማሪያም ንግስ በዓልም በሰላም ተከናውኗል በጁንታው ላይ የተወሰደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ በድል  መጠናቀቁን ተከትሎ  የፌዴራል ፖሊስ  ነጻ በወጡ አካባቢዎች ገብቶ የኅብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስከበር ላይ እንደሆነ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የጽዮን ማሪያም ንግስም በሰላም መከናወኑ ተገልጿል። ከሀዲው የህወሓት ቡድን የሀገር ሉዓላዊነትን በመዳፈር በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ በፈፀመው ጥቃት የተጀመረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በድል መጠናቀቁን ያስታወሰው ኮሚሽሽኑ፤ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ገብቶ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት እያስከበር ይገኛል። ህብረተሰቡም መደበኛ የዕለት ተዕለት ኑሮውን መጀመሩ ተገልጿል። ለተመሳሳይ የጸጥታ ማስከበር ስራ ወደ … [Read more...] about ፌዴራል ፖሊስ መቀሌ ገባ፤ በትግራይ ሰላም እያስጠበቀ ነው

Filed Under: Law, Politics, Right Column Tagged With: operation dismantle tplf

በሁመራ ለሁለተኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ

December 2, 2020 10:31 am by Editor Leave a Comment

በሁመራ ለሁለተኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ

በሁመራ ከተማ በአንድ ሆቴል በተደረገ ፍተሻ ለሁለተኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ። በከተማዋ ህግን የማስከበር ግዳጅ እየተወጡ የሚገኙ የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት ህገወጥ ድርጊቶችን ለማስወገድ እና የህዝብን ሠላም ለማስጠበቅ እየሠሩ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮማንደር ሙላት ማሞ ገልፀዋል። ከአደንዛዥ እፁ በተጨማሪ በአንድ ሰው ስም የተመዘገቡ 11 የቤት ካርታዎች እና በዚሁ ግለሠብ ስም ከፍተኛ ገንዘብ የተዘዋወረበት ቼክ ተገኝቷል። ከዚህ በተጨማሪም ገጀራዎች፣ መጥረቢያዎች እና ሌሎች መሳሪያዎች እንደተገኙ መናገራቸውን አብመድ ዘግቧል። ጎልጉል የድረጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በሁመራ ለሁለተኛ ጊዜ 37 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተገኘ

Filed Under: News, Right Column, Uncategorized Tagged With: humera, weed

“የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል

December 2, 2020 02:42 am by Editor 1 Comment

“የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል

በህወሓት ጁንታ ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ መጀመርን ተከትሎ በማይካድራ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው እልቂት በነዋሪዎች እና በተመልካች ላይ አስከፊ የስነ ልቦና ቀወስ ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር (ኢሰመኮ) ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አስታወቀዋል። ዶክተር ዳንኤል የማይካድራ ጭፍጨፋ አስመልክቶ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፣ በማይካድራ የተፈጸሙ ግፍ በቁጥር ከሚገለጸው ሪፖርት ባሻገር በነዋሪዎች ላይ ሰብዓዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ጥልቅ ሀዘን አስከትሏል። በማይካድራ አማራ እና በወልቃይት ተወላጆች ላይ ያነጣጠረውን ጥቃት ተከትሎ ቤተሰቦች መበታተናቸውንና ሕፃናት ለስነልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል፤ የጭፍጨፋው ሰለባ ቤተሰቦች ህይወታቸውን እንደቀድሞ ለማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንባቸው … [Read more...] about “የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል

Filed Under: Middle Column, Social Tagged With: mia cadra, my cadra, operation dismantle tplf, tplf

“ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት” ኬሪያ ኢብራሂም

December 2, 2020 02:29 am by Editor 2 Comments

“ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት” ኬሪያ ኢብራሂም

ከተፈላጊ የህወሓት ጁንታ አባላት አንዷ የሆነችው ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጥታለች። ኬሪያ ኢብራሂም በህውሓት ከፍተኛ አመራርነት፣ በመንግስት ከፍተኛ ሃላፊነት እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት አገልግላለች። ኬሪያ ኢብራሂም የህወሓት ጁንታው ጥቅም ይሻለኛል ብላ ወደ መቀሌ የሸሸች ሲሆን ሾፌሯ ግን የመንግሥትን ንብረት ለጁንታው አልሰጥም ብሎ እሷን መቀሌ አድርሶ ንብረቱን በሙሉ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ይዞት መምጣቱ ይታወሳል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በሰላማዊ መንገድ እንደ ኬሪያ ኢብራሂም ሌሎችም የህወሓት አመራሮች እጅ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል። እሷም የጦርነቱ አስፈላጊነት አልታየኝም፤ ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት በማለት ተናግራለች በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ በሰፊው ተነግሯል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ   … [Read more...] about “ህወሓት ተሸንፏል፤ መሸነፉንም ማመን አለበት” ኬሪያ ኢብራሂም

Filed Under: News, Right Column Tagged With: keria, operation dismantle tplf

  • « Previous Page
  • Page 1
  • Page 2
  • Page 3
  • Next Page »

Primary Sidebar

Recent Posts

  • መንግሥት ሰማ፤ ሪፖርተር ተዘጋ፤ ግን ለምን? ምሥጢሩ ምንድነው? November 3, 2026 12:09 am
  • ኢትዮጵያ በሰማይ ላይ ነዳጅ የሚሞሉ የኢሉሺን (Il-78) አውሮፕላኖችን ከሩሲያ ልትገዛ ነው October 30, 2026 08:57 am
  • ካይሮ ያጣችውን የሩሲያ ጄቶች አዲስ አበባ የታጠቀችበት ምሥጢር October 29, 2026 10:26 am
  • ኢትዮጵያ ሱ-35 ተዋጊ ጄቶች እና የኤስ-400 ዘመናዊ የአየር መከላከያ ስርአት በመታጠቅ ከሰሃራ በታች ብቸኛዋ ሀገር ሆናለች October 28, 2026 11:00 am
  • ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በ“ካሚካዜ” ድሮኖች ለመምታትና በዘር ግጭት ለማፍረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ተሰማ October 27, 2026 11:14 pm
  • ጆን መዲድ “ቀዝኖ እና ልብሱ ተበላሽቶ” ነው መከላከያ የማረከው October 27, 2026 08:41 pm
  • በጆን መዲድ መማረክ አደረጃጀቱ እየተፈረካከሰ በመሆኑ እነ ወዲ እምበይተይ፣ ምግበይ፣ ቀጣዮች ሊሆኑ ይችላሉ October 27, 2026 09:17 am
  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
  • የኒዳል ሀሰን በርሸና የሞት ፍርድ ሲፈጸምበት በቀጥታ ሥርጭት እንዲተላለፍ መወሰኑ ውዝግብ አስነሳ October 9, 2026 12:33 pm
  • ሴቶችን በመሾም ኢትዮጵያ በእርግጥ ተወዳዳሪ የሌላት ነች?  October 8, 2026 11:20 pm
  • Ethiopian Defense Forces Capture Advanced TPLF Military Drones and Documents Linked to Sudan October 7, 2026 12:40 pm
  • በሱዳን በኩል ለትህነግ የተላኩ የM6 ድሮኖችና ወታደራዊ መሣሪያዎች በመከላከያ እጅ መግባታቸው ተገለጸ October 7, 2026 11:20 am
  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
Copyright © 2026 · Goolgule