
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ትላንት እሁድ በሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን መጎብኘታቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ “ዛሬ ጠዋት (እሁድ) ኢትዮጵያን ከራስ በላይ ያስቀመጡ በሆስፒታል የሚገኙ ሴት እና ወንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀግኖቻችንን ጎብኝቻለሁ! አገልግሎታችሁን እናከብራለን” ብለዋል።
ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ስላደረጉበት ሆስፒታል የገለጹት ነገር የለም። (አል-አይን)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply