ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ህዳር 26 እና 27 ቀን 2013 ዓ/ም የሶማሌ ክልል ሸንጎ ምስረታ አካሂዷል።
ከአስራ አንድ ዞኖች ተወክለው ወደ ጅግጅጋ የሄዱ አባላት የመጀመሪያው የክልላዊ ሸንጎ ስብሰባቸውን ማድረጋቸውን ፓርቲው ገልጿል።
የክልሉ ስራ አስፈፃሚ ከሁሉም ዞኖች አንዳንድ ስራ አስፈፃሚ ተካተው እንደገና መዋቀራቸውም ተነገሯል።
ላለፉት 11 ወራት በተለያዩ የሶማሌ ክልል የተከፈቱ ቢሮዎች ስራ እንቅስቃሴ በክልል ደረጃ በጅግጅጋ ዋና መስሪያ ቤት መቀመጫ ላይ ተገምግመዋል።
እስከአሁን በክልሉ በአጠቃላይ 24 የነ.እ.ፓ. ቢሮዎች ተከፍተው ስራ ላይ እንደሚገኙ ፓርቲው ያሳወቀ ሲሆን እነዚህ ቢሮዎች በክልሉ ማዕከልነት በተዋረድ እንዲሰሩ መደረጉን አሳውቋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply