የሱዳን ወታደሮች በሱዳን ግዛት ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረ ኢትዮጵያዊ የሚሊሻ መሪ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታወቁ። የሚሊሻ መሪ ነው የተባለው ግለሰብ በሱዳን ክልል ውስጥ ከህወሓት ወገን ሆኖ ሲዋጋ የነበረ መሆኑንም ሱዳን ትሪቢዩን ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። ማንነቱ ያልተጠቀሰው ግለሰብ ከቤተሰቦቹ እና በርካታ ቁጥር ካላቸው ወታደሮችና አጃቢዎች ጋር በገዳሪፍ ግዛት አልፋሻቃ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተገለጸው። በወቅቱም አምስት ቢሊየን ፓውንድ (የሱዳን ይሁን የእንግሊዝ ያልተጠቀሰ)፣ መጠኑ ያልተገለጸ ወርቅ፣ የእንጨት ስራ ውጤቶች እና ሁለት ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ጋር መያዙም ተገልጿል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about አምስት ቢሊየን (የሱዳን) ፓውንድ በሱዳን ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረ የወንበዴው አባል ተያዘ
Archives for December 2020
ምሽግ ሠባሪው የራያው ግምባር ልዩ ኮማንዶ ኃይል
በራያ ግንባር ተሰልፎ ያለው የኮማንዶ ኃይል ኮንክሪት ምሽጎች እና አስቸጋሪ ተራራማ ቦታዎችን በመስበር ከፍተኛ ስራ እንደሠራ በልዩ ዘመቻዎች ሃይል የኮማንዶ አዛዥ የሆኑት ኮ/ል ከማል በሪሱ ገልጸዋል። ባልተጠበቁ ቦታዎች ላይ በፍጥነት ቆርጦ በመግባት፤ የታፈነ ወገንን በማስለቀቅ እና በቀጥታ ውጊያዎች ከሌሎች የሰራዊቱ ክፍሎች ጋር በመቀናጀት የኮማንዶ አባላት የላቀ ጀግንነት መፈፀማቸውንና እየፈፀሙም እንደሚገኙ ኮ/ል ከማል ገልፀዋል። ቀደም ሲልም በሁመራ ግንባር ቅርቅር በተባለው ቦታ የተያዘውን ስትራቴጂክ ቦታ በማስለቀቅና የህውሓት ቡድን ከወታደራዊ ጠቀሜታ አንፃር ምቹ የሆኑትን የመሬት ግፆችን እንዳይጠቀባቸው በማድረግ አንጻር ትልቅ ስራ መሰራቱን ኮሎኔል ከማል ተናግረዋል። (መረጃውን ለቲክቫህ የላከው በራያ ግንባር የሚገኘው ሃምሳ አለቃ አበበ ሰማኝ ነው) ጎልጉል … [Read more...] about ምሽግ ሠባሪው የራያው ግምባር ልዩ ኮማንዶ ኃይል
በማይካድራ 18 ሰው በጉድጓድ ተጥሎ፤ 57 ደግሞ በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ተገድለው ተገኙ
ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በንጹኃን የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት በማይካድራ ከተማ መፈፀሙ ይታወቃል። ይህን አስነዋሪ ተግባር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦታው በመገኘት ባደረገው ጥናት እና ይፋ ባደረገው መረጃ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 እንደሆነ ገልጾ ነበር። ግድያውም ዘርን መሠረት ያደረገና በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ጭፍጨፋ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እንጂ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 ነው ተብሎ የተገለጸው በማይካድራ ከተማ በየቤቱ ህይወታቸው አልፎ የተገኙ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀበሩትን ብቻ መሠረት ያደረገ ነው። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥናት አድርጎ ከተመለሠ በኃላ ከማይካድራ ከተማ ወጣ ባሉ የገጠር አካባቢዎች በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች በቦታው … [Read more...] about በማይካድራ 18 ሰው በጉድጓድ ተጥሎ፤ 57 ደግሞ በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ተገድለው ተገኙ
ለደቡብ ሱዳን ሰላም ማጣት የስዩም መስፍን ሤራ
5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰጡት ማብራሪያ፤ ከሀዲው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን በክልልና በዘር ከመከፋፈል አልፎ ጎረቤት ሀገራትን ጭምር በጎሳና በዘር ሲያባላ እንደነበር ተናግረዋል። “ሶማሊያ ስንሄድ እኛ እኮ እናንተን አናምናችሁም፤ በክልልና በጎሳ ከፋፍላችሁ የምታባሉን እናንተ ናችሁ፤ የእናንተ መንግስት ነው ይህን የሚያደርገን፤ በጣም ነው የምንጠላችሁ” በማለት ሳይደብቁ ኢትዮጵያን ይወቅሱ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። “በተመሳሳይ ደቡብ ሱዳን ስንሄድም አሁን ላይ በሀገራችን እየተባላንበት ያለው ጉዳይ የእናንተው ውጤት ነው” በማለት ኢትዮጵያን እንደሚወቅሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤቱ አብራርተዋል። “በኢጋድ ውስጥ ስዩም መስፍን የሚባለውን ሰውዬ መድባችሁ ከፋፍሎን አባልቶን … [Read more...] about ለደቡብ ሱዳን ሰላም ማጣት የስዩም መስፍን ሤራ
በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ። የከተማው ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ፤ የከተማው ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት ጋር ባደረጉት ክትትል ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል። ግለሰቡ ለሽብር ተግባር ለመጠቀም ካዘጋጃቸው 35 ተቀጣጣይ ቁሳቁስ፣ 216 ማሰልጠኛ ማንዋል፣ ሶስት የተለያዩ ባንኮች ደብተር፣ 20 ገንዘብ ገቢና ወጪ ደረሰኝ እና ከአንድ ላፕቶፕ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ተናግረዋል። በግለሰቡና በግብረ አበሮቹ ላይ የሚደረገው ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር አየልኝ ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃ እንደሚሰጥም ጠቅሰዋል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በጎንደር ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም በዝግጅት ላይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
ባለፉት 2ተኩል ዓመታት ትህነግ ስፖንሰር ያደረጋቸው ግጭቶች
ሰኞ ዕለት በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ትንታኔ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “መንግሥት ሥራ እንዳይሠራ በተቀናጀ መልኩ በየቦታው ሽብር ይፈጠርለት ነበር” በማለት ትህነግ/ህወሓት ስፖንሰር ያደረጋቸው 113 ግጭቶች እንደነበሩ ገልጸዋል - ዝርዝራቸውን በዚህ መልኩ ነበር ያቀረቡት በኦሮሚያ ውስጥ ብቻ 37 ግጭቶች ነበሩ፤በአማራ ክልል 23 ግጭቶች ነበሩ፤በቤባሻንጉል ጉሙዝ 15 ግጭቶች ነበሩ፤በአዲስ አባበ 14 ግጭቶች ነበሩ፤በደቡብ፣ በጋምቤላና በተቀሩት የአገሪቷ ክልሎች ግጭቶች ነበሩ፤በሁሉም ክልሎች ችግሮች አሉ፤ ትግራይ ብቻ ነው ሰላም የነበረው፤እነሱም አያፍሩም እኛ ብቻ ነን ሰላም ይሉ ነበር፤ ዋናው የችግሩ ባለቤቶች እነሱም ነበሩ፤አሠራራቸው ተራ አልነበረም፤ ገንዘብ፣ ስልጠና ስምሪት ሚዲያም ነበራቸው፤ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ባለፉት 2ተኩል ዓመታት ትህነግ ስፖንሰር ያደረጋቸው ግጭቶች