ህወሓት/ኢህአዴግ በግፍ ሲገዛት በነበረችው ኢትዮጵያ፣ አንድ ዓመት ያልሞላው የለውጥ ሒደት ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ባሉት ዘጠኝ ዓመታት (እኤአ 2003 – 2012) ባሉት ዓመታት ውስጥ 20ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በሕገወጥ መንገድ ከአገር ወጥቷል፤ ተዘርፏል። የሪፖርተሩ ብርሃኑ ፈቃደ ያቀናበረው እንዲህ ይነበባል፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሥር የሚገኘው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው የአፍሪካ የጤና ክብካቤና የኢኮኖሚ ዕድገት ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ወደ ውጭ በሕገወጥ መንገድ እንደሸሸባት አስታውቆ፣ ይህ ገንዘብ ለጤናው ዘርፍ የምታውለውን 87 በመቶ በጀት እንደሚሸፍን አመለከተ። ማክሰኞ የካቲት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ … [Read more...] about ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ዶላር ተዘርፋለች!
Archives for February 2019
በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን
በሌብነት የተጠረጠሩት በረከት ስምኦንና ታደሰ ካሣ አርብ በባህር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በዕለቱ ሁለቱም ግለሰቦች ያሉባቸውን ችግሮች ያስረዱ ሲሆን በተለይ በረከት ስምዖን በእስርቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲል ማማረሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ኮምፒውተር ያስፈልገናልም ብለዋል። በዕለቱ የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ባለፈው በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ማስረጃዎችን ማየቱንና የምስክሮችን ቃል መቀበሉን አሳውቋል። ሆኖም ጉዳዩ ከባድ፣ ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ምስክሮች እና ሰነዶች በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መገኘታቸውን አስታውሶ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። በወቅቱ የቀረበውን ማራዘሚያ ቀን በረከት የተቃወመ ሲሆን ያቀረበው ምክንያትም የሕግ ሥልጣን በሌለው አካል መከሰሰሱን ነው። ይህ ሕጋዊነት … [Read more...] about በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን
የአል አሙዲ ሃብት በ9.7 ቢሊዮን ዶላር ወደረ!
የኢትዮጵያን ሃብት ከህወሓት ጋር በጥቅም በመመሳጠር ሲበዘብዝ የነበረው መሐመድ አለ አሙዲ (አላሙዲ) እጅግ በርካታ ገንዘብ ከፍሎ በሌብነት ከታሰረበት ሳዑዲ አረቢያ መለቀቁ ተሰምቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሲታሰር 10.9 ቢሊዮን ዶላር የነበረው ሃብቱ ሲፈታ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። በፎርብስ ደረጃ አሠጣጥ መሠረት ከእስር በኋላ የ159ኛ ደረጃ ሰጥቶታል። ሆኖም ፎርብስ የአላሙዲ ሃብት በእርግጥ የእርሱ መሆኑን ማረጋገጥ ስላልቻለ በ2018 ከዓለም ቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ አውጥቶታል። በርካታዎች እየሞቱና መብታቸው ተገፍፎ በእስር እየማቀቁ በነበሩበት ወቅት የንብ ካኔተራ በመልበስ የህወሓት ደጋፊነቱን በገሃድ ያስመሰከረው አላሙዲንን ከህወሓት ለይቶ “የሕዝብ ሰው” አድርጎ ማቅረብ ለህወሓት ያለን “ጥላቻ” ከአላሙዲ “ትግሬ” አለመሆን ጋር የተገናኘ ይመስላል የሚሉ ጥቂቶች … [Read more...] about የአል አሙዲ ሃብት በ9.7 ቢሊዮን ዶላር ወደረ!
የሎሬት ፀጋዬ ማዕከል ሊቋቋም ነው
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ስም የባህል ማዕከል እንደሚያቋቁም አስታውቋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታደሰ ቀነዓ ለኢዜአ እንደገለጹት ማዕከሉ የሚቋቋመው የሎሬቱን ጨምሮ በኪነ ጥበብ ሥራዎች ላይ ጥናትና ምርምር ለማድረግና ተሰጥኦ ያላቸውን ጠቢባን ለማፍራት ነው። “ማዕከሉን ለሟቋቋም ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ተገብቷል” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ማዕከሉን ለማቋቋም ከአዲስ አበባ፣ ከባህር ዳርና ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ልምድ ቀስሟል ብለዋል። ከሎሬት ጸጋዬ ወጥ ሥራዎች መካከል የአቴቴ ሥርዓት፣ የገዳ ሥርዓት፣ ዝክረ መርካቶ፣ የኩሽ ሕዝቦች ሥልጣኔ፣ ዳግማዊ ቴዎድሮስ፣ ኦዳና አቡነ ጴጥሮስን የሚዘክሩት ተጠቃሽ ናቸው። ከትርጉም ሥራዎቻቸው መካከል የዊሊያም ሼክስፒር ድርሰቶች ሃምሌትና ኦቴሎ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች ይገኙበታል። የአምቦ አካባቢ ተወላጅ የሆኑት ሎሬት … [Read more...] about የሎሬት ፀጋዬ ማዕከል ሊቋቋም ነው
ከአገር ሊሸሽ የነበረው ወርቅና ገንዘብ ወደ ብሔራዊ ባንክ ገብቷል
በቁጥጥር ስር የዋለው ወርቅና የ13 ሀገራት ገንዘብ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደረገ። በቶጎ ውጫሌ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ኮድ 3 ኦሮ የሰሌዳ ቁጥር 63100 አይሱዚ ጫት ጭኖ ወደ አርጌሳ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት ጥር 28 ቀን 2011 ከሌሊቱ 9፡00 አካባቢ 7 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወርቅ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል። በቁጥጥር ስር የዋለው ወርቅና የውጭ አገራት ገንዘብ በመከላከያ ሠራዊት አባላት ታጅቦ ትናንት ምሽት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰ ሲሆን በዛሬው ዕለት (ሐሙስ) ደግሞ ብሔራዊ ባንክ ትክክለኛነቱን አረጋግጦ ተረክቦታል። በተመሳሳይ የውጭ አገራት ገንዘብ ትክክለኛነታቸው ተረጋግጦና ተቆጥሮ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደርጓል። በአራት ዓይነት መጠን (Bar) የተዘጋጀው ወርቅ 21.7፣ 21.75፣ 22.5 እና 22.34 ካራት መሆናቸውን በብሔራዊ ባንክ የተረጋገጠ ሲሆን … [Read more...] about ከአገር ሊሸሽ የነበረው ወርቅና ገንዘብ ወደ ብሔራዊ ባንክ ገብቷል
ከአገር ሊሸሽ የነበረ ሃብት ተያዘ
የገቢዎች ሚኒስቴር 60 ሚሊዮን ብር የሚሆን የውጭ ሃገራት ገንዘብና ሰባት ኪሎግራም ወርቅ ጥር 29/2011 ዓ.ም መያዙን ገለፀ። አራት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል። የገቢዎች ሚኒስቴር ቶጎ ውጫሌ ኬላ ላይ ሰባት ኪሎ ግራም ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ሃገራት ገንዘብ መያዙን ገልጿል። የአሜሪካ፣ የካናዳና የአውስትራሊያ ዶላር፣ ዩሮ፣ ድርሃምና የሌሎች ሃገራት ገንዘብ ነው የተያዘው ብሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ። ትናንት ምሽት ሰባት ኪሎ ግራም ወርቅና መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የውጪ አገር ገንዘብ ከአራት ተጠርጣሪ ኮንትሮባንዲስቶች ጋር በቶጎ ዉጫሌ ኬላ በጉምሩክ ሰራተኞች ተይዟል። የተያዙት ከሚል ዑመር፣ መሃሪ አብዱ፣መሃዲ ዑመር እና ካልድ አብዲ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡ ዘጋቢ፦ ጋሻው ፈንታሁንና ራሔል ደምሰው (አብመድ) … [Read more...] about ከአገር ሊሸሽ የነበረ ሃብት ተያዘ
ክሱ “የተቀነባበረ ውሸት ነው” አብዲ ኢሌ
የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሐመድ የቀረበባቸው ክስ “የተቀነባበረ ውሸት ነው” አሉ። አቶ አብዲ ይህን ያሉት ጉዳያቸውን እየተመለከተ ላለው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ነው። ችሎቱ ለዛሬ ቀጠሮ ይዞ የነበረው አቶ አብዲን ጨምሮ በ47 ተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበባቸውን ክስ በንባብ ለማሰማት ነበር። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በይፋ ክስ የመሰረተው ባለፈው ረቡዕ ጥር 22 የነበረ ቢሆንም የተከሳሽ ጠበቆች በችሎት ባለመገኘታቸው የክስ ንባቡ ለዛሬ ተላልፏል። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ በሐምሌ 2010 ዓ. ም. በሶማሌ ክልል 59 ሰዎች እንዲገደሉ እና 412 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል በሚል ነው ክሱን ያቀረበው። በዛሬው የችሎት ውሎ ክሳቸውን ያደመጡት አቶ አብዲ ክሱን ተረድተውት እንደሆነ በመሐል ዳኛው … [Read more...] about ክሱ “የተቀነባበረ ውሸት ነው” አብዲ ኢሌ
ህወሓት በክህደት አከርካሪው ተመታ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በማለት ራሱን የሚጠራው የበረሓ ወንበዴዎች ስብስብ አባል የነበረው ዛዲግ አብርሃ ከድርጅቱ አባልነት ለቋል። በህወሓት ታሪክ ዓይነተኛ ቦታ የሚሰጠው ይህ ክህደት ድርጅቱን ክፉና ጎድቶታል። ዛዲግን የሚከተሉ ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል። በጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ግንቦት 2፤ 2010 በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ ሆኖ የተሾመው ዛዲግ አብርሃ የካቲት 5፤2011ዓም ከድርጅቱ መልቀቁን በጻፈው አምስት ገጽ ደብዳቤ ገልጾዋል። ከዚህኛው ሹመቱ በፊት ዛዲግ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጦር እንዲዘምት ትዕዛዝ በሰጠው የጦር ወንጀለኛ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ዘመን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ የነበረው ነገሪ ሌንጮ ምክትል በመሆን ሠርቷል። ከዚያም በፊት “የሕዳሴ ግድብ” አስተባባሪ ኃላፊ ሆኖ መሥራቱ … [Read more...] about ህወሓት በክህደት አከርካሪው ተመታ
ከምርጫ በፊት ሪፈረንደም
ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ሕዝቡ መሪውን ራሱ እንዲመርጥ የሚያስችለውን አሠራር (ፕሬዚዳንታዊ መንግስት) ወይም ደግሞ እንደ አሁኑ ፓርቲው መሪውን እንዲመርጥለት የሚያደርገውን አሠራር (ጠቅላይ ሚኒስቴራዊ መንግስት)፤ ከሁለቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ፈቃዱን እንዲያስታውቅ ለሕዝቡ በሪፈረንደም ዕድል ይሰጠው ዘንድ ለመሞገት አራት ማስረጃዎች አቀርባለሁ። 1ኛ/ ሕዝቡ አዋቂ ነውና እናውቅልሃለን ከእንግዲህ አይሰራም እናውቅልሃለን የሚሉ ሊሂቃን አንዴ ንጉስ፥ አንዴ ፕሬዚዳንት፥ አሁን አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር እያሉ መንግስት መሰረቱ። የለውጥ አየር እየነፈሰለት እፎይታን በማጣጣም ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእሳት ተፈትኖ አዋቂ የሆነ ነውና፥ ዛሬ ላይ ቆመን ቀንበር እንደ በፊቱ ባናሸክመው መልካም ነው። ጊዜውን የሚመጥን አካሄድ በመከተል ሕዝቡ መሪዉን ብቻ ሳይሆን የመንግስቱን … [Read more...] about ከምርጫ በፊት ሪፈረንደም
መሬት ላራሹ! Land tenure!
የኢትዮጵያን የክልሎች ወሰን ጥያቄ የሚፈታው የመሬት ላራሹ ጥያቄ ሲመለስ ነው። የኢትዮጵያ ህገ-መግስት አንቀጽ 40 ንኡስ አንቀጽ 6 ላይ ሲናገር “የኢትዮጵያ መሬት ባለቤትነት የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች…” ይላል። ይህ ማለት የሃገሪቱ መሬት በብሄሮች የተያዘ የቡድን ሃብት ነው ማለት ነው። የደርጉ መንግስት መሬትን ከከበርቴው ነጥቆ ለመንግስት ያደረገ ሲሆን ይሄኛው መንግስት ደግሞ ለቡድኖች ኣድሏል። እነዚህ ሁለት የመሬት ሃብት ዝውውሮች ችግሮች ኣሉባቸው። መሬት ላራሹ ማለት መሬት ለሚሰራበት ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወይም ለዜጋው ከነ ሙሉ መብቱ ይሰጥ የሚል እንድምታ ነው ያለው። ይህንን ጥያቄ መመለስና የመሬትን የሃብት ዝውውር ከቡድን ወደ ግለሰብ በማዛወር የወሰን ጥያቄዎችን እስከ ሃቹ መፍታት ይቻላል። ይህ የተቋቋመው የማንነት ኣስተዳደርና ወሰን ኮሚሽን ይህንን ኣሳብ … [Read more...] about መሬት ላራሹ! Land tenure!