የኢትዮጵያን የክልሎች ወሰን ጥያቄ የሚፈታው የመሬት ላራሹ ጥያቄ ሲመለስ ነው። የኢትዮጵያ ህገ-መግስት አንቀጽ 40 ንኡስ አንቀጽ 6 ላይ ሲናገር “የኢትዮጵያ መሬት ባለቤትነት የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች…” ይላል። ይህ ማለት የሃገሪቱ መሬት በብሄሮች የተያዘ የቡድን ሃብት ነው ማለት ነው። የደርጉ መንግስት መሬትን ከከበርቴው ነጥቆ ለመንግስት ያደረገ ሲሆን ይሄኛው መንግስት ደግሞ ለቡድኖች ኣድሏል። እነዚህ ሁለት የመሬት ሃብት ዝውውሮች ችግሮች ኣሉባቸው። መሬት ላራሹ ማለት መሬት ለሚሰራበት ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወይም ለዜጋው ከነ ሙሉ መብቱ ይሰጥ የሚል እንድምታ ነው ያለው። ይህንን ጥያቄ መመለስና የመሬትን የሃብት ዝውውር ከቡድን ወደ ግለሰብ በማዛወር የወሰን ጥያቄዎችን እስከ ሃቹ መፍታት ይቻላል። ይህ የተቋቋመው የማንነት ኣስተዳደርና ወሰን ኮሚሽን ይህንን ኣሳብ … [Read more...] about መሬት ላራሹ! Land tenure!