• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መሬት ላራሹ! Land tenure!

February 6, 2019 09:54 am by Editor 1 Comment

የኢትዮጵያን የክልሎች ወሰን ጥያቄ የሚፈታው የመሬት ላራሹ ጥያቄ ሲመለስ ነው። የኢትዮጵያ ህገ-መግስት አንቀጽ 40 ንኡስ አንቀጽ 6 ላይ ሲናገር “የኢትዮጵያ መሬት ባለቤትነት የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች…” ይላል። ይህ ማለት የሃገሪቱ መሬት በብሄሮች የተያዘ የቡድን ሃብት ነው ማለት ነው።

የደርጉ መንግስት መሬትን ከከበርቴው ነጥቆ ለመንግስት ያደረገ ሲሆን ይሄኛው መንግስት ደግሞ  ለቡድኖች ኣድሏል። እነዚህ ሁለት የመሬት ሃብት ዝውውሮች ችግሮች ኣሉባቸው። መሬት ላራሹ ማለት መሬት ለሚሰራበት ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወይም ለዜጋው ከነ ሙሉ መብቱ ይሰጥ የሚል እንድምታ ነው ያለው። ይህንን ጥያቄ መመለስና የመሬትን የሃብት ዝውውር ከቡድን ወደ ግለሰብ በማዛወር የወሰን ጥያቄዎችን እስከ ሃቹ መፍታት ይቻላል። ይህ የተቋቋመው የማንነት ኣስተዳደርና ወሰን ኮሚሽን ይህንን ኣሳብ እንዲያየው እጠቁማለሁ።

በቡድን የተያዘው መሬት ወደ ግል ሲዞር የብሄሮች የወሰን ጥያቄ አለቀለት ማለት ነው። ስለዚህ ኮሚሽኑ በክልሎች መካከል መስመሩ የት ጋር ይሁን? ብሎ ከማሰብ ከአሁኑ መሰረታዊ የሆነ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ እንዲፈታ መንግስትን ማሳሰብ ኣለበት። መሬት ላራሹ ከሆነ ኢትዮጵያውያን በወሰን አይጋጩም። መሬት የግል ይሁን ሲባል አንዳንድ ኮሙዩኒቲዎች መሬት ኣያስፈልጋቸውም ማለት ኣይደለም። መሬትን ከብሄር ባለቤትነት አውጥቶ ነገር ግን አንዳንድ ኮሙዩኒቲዎች ደግሞ የመሬት ባለቤት እንዲሆነ ማድረግ ይቻላል። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የመሬት ፖሊሲዋን በሚመለከት የሚከተለውን ለውጥ ብታደርግ ብዙ እቆቅልሶቿ ይፈታሉ።

  1. መሬትን የግል በማድረግ (Privatization)
  2. ኣንዳንድ የግጦሽ ቦታውችን የአምልኮ ስፍራዎችንና የባህል መከወኛ ስፍራዎችን በቡድን እንዲያዙ ማድረግ
  3. ወንዞችን ተራሮችን ሰው ያልደረሰባቸውን ቦታዎች መንግስት እንዲይዝ ማድረግ ይገባል።

ይህ የመሬት ፖሊሲ በተለይ የወሰን ጥያቄን ግሩም ኣድርጎ ይፈታል። የማንነትና የአስተዳደር ጉዳዮችን ደግሞ በሁለትዮሽ የፌደራል ስቴት (two federal states) ግንባታ መመለስ ይቻላልና ኮሚሽኑም መንግስትም የለውጡ ሃይልም ይህንን ኣሳብ እንዲያስበው እንመክራለን።

ሁለትዮሽ የፌደራል ስቴት  ማለት በአንድ በኩል የብሄር ባህላዊ የፌደራል ስቴትና በሌላ በኩል ሲቪክ የፌደራል ስቴት ወይም የዜጎች የፌደራል ስቴት በመመስረት የማንነትና ኣስተዳደር ጉዳዮችን ማስታረቅ ይቻላል። ይህ መንገድ እጅግ ኣስፈላጊ ነውና ኮሚሽኑ ይህንን ከግንዛቤ እንዲያስገባ ከወዲሁ እጠይቃለሁ። የሁለትዮሽ የፌደራል ስቴት ግንባታው በሁለት ጽንፍ ያለውን ፖለቲካ በዶክተር አብይ አህመድ አገላለጽ “ዋልታ ረገጥ” ፖለቲካችንን ያስታርቃል። የዜግነት ፖለቲካንና የቡድን መብትን አቻችሎ ይይዛል።

ከፍ ሲል እንዳልኩት የመሬት ላራሹ ጥያቄ ከተመለስና ከላይ ባነሳሁት መሰረት መልክ የመሬት ይዞታ ፖሊሲው ከተቀረጸ የአዲስ ኣበባ ጥያቄም ይፈታል። የመሬት ላራሹ ጥያቄ የከተማ ቦታንም ይመለከታልና ከተሜው የቦታው ባለቤት ሲሆን የአዲስ ኣበባ የባለቤትነት ጥያቄ እስከ ሃቹ ተፈታ ማለት ነው። የመሬት ፖሊሲያችን ሲፈታ መሬት ላራሹ ሲሆን ደቡብ ውስጥ ያሉ የወሰን ግጭቶች መፈናቀሎች ሁሉ ይቆማሉ። ስለዚህ ዛሬም መሬት ላራሹ! ዛሬም መሬት ላራሹ! ዛሬም መሬት ላራሹ! … ወጣቶች ይህንን ጥያቄ አንግበው የቀዳሚውን ትውልድ ጥያቄ ሊቋጩት ይገባል። አዲስ ኣበቤዎች ይህንን ጥያቄ ሊያነሱ ይገባል። ገበሬው ይህንን ጥያቄ ሊያነሳ ይገባል።

የዶክተር ኣብይ መንግስት ወደ ለውጥ ሲገባ ከሚመለከታቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ይህ የመሬት ፖሊሲና የማንነት ጉዳዮች ናቸው። ማንነትን ከፍ ሲል እንዳልኩት በሁለትዮሽ ፌደራል ስቴት ቤቶች ጠብቆ የወሰኑን ጉዳይ በመሬት ፖሊሲ ለውጥ እስከ ሃቹ መዝጋት ይቻላል። መሬት ላራሹን የማይደግፍ ኦሮሞ፣ ኣማራ፣ ትግሬ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ወዘተ ኣለ ብየ ኣላምንም። የዜጎች የመሬት ሃብት ባለቤትነት (land ownership) ሲመለስ ልማት ይፈጥናል እንዳልኩት የወሰን ጉዳይ ያልቅለታል። እናም መሬት ላራሹ!

geletawzeleke@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: land, Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. gi Haile says

    February 8, 2019 05:01 pm at 5:01 pm

    ብዙዎች የሞቱለት የመሬት ለኣራሹ ጥያቄ ዛሬም ኣልተሠለሰም። ይህ ከ 40 አመት በላይ ደም ሲያፋስስ የቆየው የመሬት ጥያቄ በወቅቱ ካልተፈታ በ27 አመት መፍትሔ አድርጎ ሕወኣት ያወጣው የድንበርና የመሬት ፖሊስ ጨርሶ ደርግ አድርጎት ከነበረው የከፋ ፖሊስ ነበር። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄው ከመጀመሪያው ዲሞክራሲ፣ መሬት ለኣራሽ፣ የዜጎች እኩልነት መብት ጥያቄ እስከዛሬ መልስ ያላገኘ መመለስ ያለበት መሠረታዊ ጥያቄ ነው። የጊዜውም ጥያቄ ሰለሆነ መልስ ሊሰጠው የሚገባ ነው። ድልና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule