• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ዶላር ተዘርፋለች!

February 13, 2019 10:39 am by Editor 3 Comments

ህወሓት/ኢህአዴግ በግፍ ሲገዛት በነበረችው ኢትዮጵያ፣ አንድ ዓመት ያልሞላው የለውጥ ሒደት ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ባሉት ዘጠኝ ዓመታት (እኤአ 2003 – 2012) ባሉት ዓመታት ውስጥ 20ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በሕገወጥ መንገድ ከአገር ወጥቷል፤ ተዘርፏል። የሪፖርተሩ ብርሃኑ ፈቃደ ያቀናበረው እንዲህ ይነበባል፤

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት  (ተመድ) ሥር የሚገኘው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው የአፍሪካ የጤና ክብካቤና የኢኮኖሚ ዕድገት ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ወደ ውጭ በሕገወጥ መንገድ እንደሸሸባት አስታውቆ፣ ይህ ገንዘብ ለጤናው ዘርፍ የምታውለውን 87 በመቶ በጀት እንደሚሸፍን አመለከተ።

ማክሰኞ የካቲት 5 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. ከ2003 እስከ 2012 ባሉት ዘጠኝ ዓመታት በየዓመቱ ከ2.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሕገወጥ ገንዘብ በሚያሸሹ አካላት ሳቢያ ተጎጂ ሆናለች ብሏል። በዚህ ሳቢያም ለጤናው ዘርፍ የምትመድበው ዝቅተኛ በጀትም  በሚሸሸው ገንዘብ ምክንያት ከባድ ተፅዕኖ ውስጥ እንደቆየ አመላክቷል።

ኢትዮጵያ ከጠቅላላ ኢኮኖሚዋ (ከአገር ውስጥ አጠቃላይ ምርት አኳያ) አንድ በመቶ ለጤናው ዘርፍ ትመድባለች ያለው ሪፖርቱ፣ በአንፃሩ በየዓመቱ ከ2.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ እየሸሸባት በመሆኑ 87 በመቶውን የጤናውን ዘርፍ በጀት ወደ ውጭ የሚሸሸው ገንዘብ እንደሚሸፍነው ሪፖርቱ አሥፍሯል።

ከዚህም በተጓዳኝ መንግሥት ለጤናው ዘርፍ ከሚያወጣው ወጪና ለዕዳ ክፍያ ከሚያውለው ገንዘብ ተቀናንሶ ሲሰላም፣ አገሪቱ በየዓመቱ የ2.5 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ክፍተት እንደሚገጥማት ታውቋል።

እ.ኤ.አ. ከ2015 እስከ 2017 ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግሥት አማካይ ጠቅላላ የዕዳ ክምችት መጠን 55 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ተመድ አውስቶ፣ ከሕገወጥ ገንዘብ የማሸሽ ተግባር ባሻገር ለዕዳ ክፍያ የሚውለው ከፍተኛ ገንዘብም እንደ ጤናው መስክ ባሉት መሠረታዊ ዘርፎች ላይ ጫና ማሳደሩን አስታውቋል።

እንዲህ ያሉትን እውነታዎች ያጎላው የተመድ ሪፖርት፣ እ.ኤ.አ. ከ2003 እስከ 2012 ባለው ጊዜ ውስጥ አፍሪካ በጠቅላላው ከ300 እስከ 600 ቢሊዮን ዶላር  በሕገወጦች ገንዘብ የማሸሽ ድርጊት ሳቢያ ማጣቷትን አመልክቷል። ከጤናው መስክ አኳያም አገሮች ከዓመታዊ በጀታቸው አምስት በመቶ ለጤና ዘርፍ ይመድባሉ ተብሎ ቢገመት፣ በአፍሪካ ለጤናው መስክ ከሚያስፈልገው ገንዘብ ውስጥ የ66 ቢሊዮን ዶላር ክፍት እንደሚታይ ይፋ አድርጓል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የተገኙበትና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከዳንጎቴ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ባሰናዳው የ“አፍሪካ ቢዝነስ ሔልዝ ፎረም 2019” በተሰኘው መድረክ ላይ የናይጄሪያ ቢሊየነር ሐጂ አሊኮ ዳንጎቴ ልጅ ሐሊማ ዳንጎቴ ይፋ እንዳደረገችው፣ የዳንጎቴ ግሩፕ ኩባንያዎች ከታክስ ተቀናሽ በኋላ ከሚያስገቡት ትርፍ ውስጥ በአፍሪካ ጤናው ዘርፍ እንዲውል የአንድ በመቶ ገቢያቸውን ያውላሉ።

 እ.ኤ.አ. በ1994 የተመሠረተው የዳንጎቴ ፋውንዴሽን ከምሥረታው ጀምሮ፣ ለጤናና መሰል የበጎ ተግባራት የሚውል የ1.5 ቢሊዮን ዶላር በጀት በመመደብ ድጋፍ ሲያደረግ መቆየቱን የፋውንዴሽኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የአፍሪካ መንግሥታት ብቻቸውን ከፍተኛ የጤና ክብካቤ ችግሮች በሚስተዋሉባት አፍሪካ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ማቅረብ እንደማይችሉ በማመን፣ ድጋፍ ለማድረግ በዳንጎቴ ፋውንዴሽን አማካይነት መሰባሰብ የጀመሩት የአፍሪካ ባለሀብቶች፣ ለጤናው ዘርፍ የአፍሪካ የቢዝነስ ጥምረት የተሰኘ መድረክም በአዲስ አበባው ፎረም ይፋ አድርገዋል።

የዓለም እግር ኳስ ኮከቡ ኮትዲቯራዊ ዲዲዬር ድሮግባ፣ በጤናና በትምህርት መስክ ለአፍሪካውያን ድጋፍ የሚያደርግበትን የዲዲዬር ድሮግባ ፋውንዴሽንን እንቅስቃሴዎች በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥቷል።

በዚሁ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን ጨምሮ የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ፣ የቦትስዋና ፕሬዚዳንት ሞክዊትሲ ማሲሲአ፣ እንዲሁም የኬንያ፣ የግብፅና የሌሎች አገሮች የጤና ሚኒስትሮች ስለአገሮቻቸው የጤና ዘርፍ እንቅስቃሴዎች ገለጻ አቅርበዋል። (ምንጭ፤ ሪፖርተር)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    February 24, 2019 07:39 am at 7:39 am

    ፓለቲካ ነፍስና ሥጋን ያጠወልጋል። ስልጣንም ከራስ ላይ ከወጣ በህዋላ እንደ ስካር ቶሎ አይለቅም። ለዛ ነው በአለም ዙሪያ ዘልዛላ የሃገር መሪዎችን የምናየው። መዝረፉ፤ መግደሉ፤ ታጅቦ መሄድ ከውሃ ጥም የበለጠ ስለሆነባቸው ውረድ ለሃገርና ለህዝብ አልበጃቹሁም ሲባሉ በጊዜአዊ አዋጅ እጅ እና እግርን አፍን ጠፍሮና ለጎሞ በሚይዝ ህግ ሰውን የሚተበትቡት። ጊዜአዊ መረጃ የሱዳኑን መሪ መውሰድ ይቻላል። ሰው እንዴት ከጃፋር ኒሜሪ አወዳደቅ አይማርም። እንዴት ከጎረቤቱ የኡጋንዳው ኢዲአሚን እድል ፈንታ ዛሬን አይቶ በቃኝ ማለት አይችልም?
    የአፍሪቃ መሪዎች ጨካኞችና ዘረኞች ናቸው። የሚያስቡትም ለዛሬ ብቻ ነው። በዘጠኝ ዓመታት 9 ቢሊዮን ዶላር የተዘረፈችው መከረኛዋ ሃገራችን በወያኔ ዘመን የደረሰባት ገመና ጣሊያን ካደረሰባት ይከፋል። በ27 አመቱ አስከፊ ድርጊት በሃገሪቱ አንጡራ ሃብት ሲፈነጩ የኖሩት ጠባብ ብሄርተኞቹ ዛሬም እያስፈራሩ እንደሆነ ከዶ/ር ደብረጽዮን ንግግር መረዳት ይቻላል። አልፈው ከመጡ “እንጠራርጋቸዋለን” የሚጠረገው ታልፎስ የሚመጣው ማን ነው? ባህር ተሻግሮ የሃገሪቱን ድንበር አቋርጦ ለወረራ ሊመጣ የተዘጋጀ የውጭ ሃይል ካለ ይፋ ማድረግና በህብረት መፋለም ነው። ውጊያው ከወገን ሰው ጋር ከሆነ የወያኔ የመኖሪያ ብልሃት እንጂ ወራሪም ተወራሪም የለም። የሚያሳዝነው ግን ለዘብ ያለ አቋም አላቸው የተባሉት እነ ገብሩ አሥራትም ንግግራቸው ሁሉ በእሳት ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ መሆኑ ያሳዝናል። አይበቃም መገዳደል? ሌላውን ወደ እሳት እየገፋችሁ እስከ መቼ ነው እናንተ የምትኖሩት? ዘልዛሎች። በቃኝን የማታውቁ። የፓለቲከኛ ጡረታ የለውም እንዴ? ከ44 ዓመት በፊት የገመዳችሁት የመከፋፈልና የብሄርተኛ ገመድ ዛሬ ሃገሪቱን ከፍተኛ ቀውስ ላይ እንደጣላት ማየት እንዴት ይከብዳል? ህገ – መንግሥቱ ይከበር ማለትስ ምን ማለት ነው። እናነተን እስካላገለገለ ድረስ ህገ-መንግሥቱ ፈረስ ማለት ነው? ስታፍኑ፤ ስትገሉ፤ በወንድ ላይ እሴት ሽንቷን እንድትሸና ስታረጉ፤ ወንድ ወንድን እንዲደፍር ሲደረግ፤ ጥፍር በፒንሳ ሲነቀል ወዘተ… ህገ መንግሥቱን ተደግፋችሁ ነበር እንዴ የፈጸማችሁት?
    አንድ የወያኔን ግፍ ለበልና ሃሳቤን ልግታ። ጊዜው ወያኔ የከተማ አለቃ እንደሆነ ነው። ከሻቢያም ጋር እንደሙጫ ተጣብቀዋል። በዚህ መካከል የወረቀት ገንዘብና ሽርፍራፊ ሳንቲም ኤርትራ ውስጥ የለምና በአስቸኳይ ይላክልን ይላል በቅርቡ የኤርትራ አለቃ የሆነው ሻቢያ። ጉዳዮም በአቶ መለስ ታይቶ ይሰጥ ይባላል። ጉዳዮ ከባንኩ ሃላፊ ሲደርስ ጭራሽ አይሆንም በማለት ይቃወማል። ማታ የወያኔ የግድያ ኮማንዶ ተልኮ አፍነው ከገደሉት በህዋላ ራሱን ሰቀለ ለማለት ያንጠለጥሉታል። በምትኩም ለወያኔ ዝርፊያ የሚስማማ ሰው ለባንኩ ይሾማል። የተባለውም ገንዘብ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጭኖ ለሻቢያ ይሰጣል። ይህ ከሚያልፍ ውሃ የተቀዳ ታሪክ አይደለም። እውነት እንጂ! በ44 አመቱ የወያኔ ዘመን ያልተሰራ ግፍ የለም። የትግራይ ህዝብ ለትግራይ ህዝብ የሚባለው ሰውን ለማደንቆር ነው። ለዘመናት በስሙ ሲነግዱበት፤ ተርቦ የዓለም ህዝብ ያዋጣውን ገንዘብ ተከፋፍለው ይገዛ በተባለው ስንዴ ምትክ አሽዋ በጆኒያ ከምረው ስንዴ ነው በማለት እርዳታ አቅራቢዎችን የሚያታልሉ ጉዶች ናቸው። በመሰረቱ የትግራይ ህዝብ ሁለት ክፉ ሃይሎች እንደ ሥጋ ቅርጫ ሲቀራመቱት ነው የኖረው። ወያኔና ደርግ!
    ወያኔ በውጊያ ወደ ነበርንበት ስልጣን እንመለሳለን ብሎ ማሰቡ ክትዕቢት የመነጨ እንጂ ከእውነት ጋር አይገናኝም። ሃገሪቱን ያፈርሷታል እንጂ ዳግም በእነርሱ እጅ የሚገዛ ማንም አይኖርም። የትግራይም ህዝብ ጊዜውን ጠብቆ እንደ ሞሶሎኒ ዘቅዝቆ እንደ ሚሰቅላቸው አልጠራጠርም። የታፈነ ህዝብ ሲነሳ የሚያቆመው ሃይል አይኖርምና! አቦይ ስብሃት ይኖሩ ይሆን ከሚሰቅሉት መካከል ወይስ ቀድመው የተፈጥሮ ሞትን ይሞቱ! የቆየ ሰው ያያል!!

    Reply
  2. Yabdeta says

    March 17, 2019 12:15 pm at 12:15 pm

    Is golgool frozen in time since February? Is it your sources have dried up or there are not topics worth googol’s editorial policies to write about. Or could it be googol losing the neutral ground in the current old-odp-jawarian led ethnographies politics? We wonder as we see many showing their true colours. – is golgool also a chameleon?

    Reply
  3. Golguayoo says

    March 19, 2019 05:10 pm at 5:10 pm

    Stuck in time Golgool? Nothing to report since this article? Nothing happened since or you don’t want to report it? Shut down your web then.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am
  • የኦነግ ሸኔ አባላትን ዕድሜ ለማሳጠር የጂፒኤስ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው December 7, 2020 12:38 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule