በቁጥጥር ስር የዋለው ወርቅና የ13 ሀገራት ገንዘብ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደረገ። በቶጎ ውጫሌ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ኮድ 3 ኦሮ የሰሌዳ ቁጥር 63100 አይሱዚ ጫት ጭኖ ወደ አርጌሳ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት ጥር 28 ቀን 2011 ከሌሊቱ 9፡00 አካባቢ 7 ኪሎ ግራም የሚመዝን ወርቅ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።
በቁጥጥር ስር የዋለው ወርቅና የውጭ አገራት ገንዘብ በመከላከያ ሠራዊት አባላት ታጅቦ ትናንት ምሽት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰ ሲሆን በዛሬው ዕለት (ሐሙስ) ደግሞ ብሔራዊ ባንክ ትክክለኛነቱን አረጋግጦ ተረክቦታል።
በተመሳሳይ የውጭ አገራት ገንዘብ ትክክለኛነታቸው ተረጋግጦና ተቆጥሮ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ተደርጓል። በአራት ዓይነት መጠን (Bar) የተዘጋጀው ወርቅ 21.7፣ 21.75፣ 22.5 እና 22.34 ካራት መሆናቸውን በብሔራዊ ባንክ የተረጋገጠ ሲሆን ዋጋው 8,005,931.28 ብር ተገምቷል።
ምንጭ፡- የገቢዎች ሚኒስቴር
Yalew says
By the time of tplf meles did a wrong thing so it’s become home work for any so we must support aby