• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከምርጫ በፊት ሪፈረንደም

February 6, 2019 10:04 am by Editor Leave a Comment

ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ሕዝቡ መሪውን ራሱ እንዲመርጥ የሚያስችለውን አሠራር  (ፕሬዚዳንታዊ መንግስት) ወይም ደግሞ እንደ አሁኑ ፓርቲው መሪውን እንዲመርጥለት የሚያደርገውን አሠራር (ጠቅላይ ሚኒስቴራዊ መንግስት)፤ ከሁለቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ፈቃዱን እንዲያስታውቅ ለሕዝቡ በሪፈረንደም ዕድል ይሰጠው ዘንድ ለመሞገት አራት ማስረጃዎች አቀርባለሁ።

1ኛ/ ሕዝቡ አዋቂ ነውና እናውቅልሃለን ከእንግዲህ አይሰራም

እናውቅልሃለን የሚሉ ሊሂቃን አንዴ ንጉስ፥ አንዴ ፕሬዚዳንት፥ አሁን አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር እያሉ መንግስት መሰረቱ።  የለውጥ አየር እየነፈሰለት እፎይታን በማጣጣም ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእሳት ተፈትኖ አዋቂ የሆነ ነውና፥ ዛሬ ላይ ቆመን ቀንበር እንደ በፊቱ ባናሸክመው መልካም ነው።  ጊዜውን የሚመጥን አካሄድ በመከተል ሕዝቡ መሪዉን ብቻ ሳይሆን የመንግስቱን ዓይነት /system/ ጭምር እንዲመርጥ ቢደረግ የሚመሰረተው መንግስት የሕዝብ መንግስት ለመሆኑ ዋስትና በመስጠት ያፀናዋል።  ሊሂቃን የትኛው እንደሚበጅ በየፊናቸው ጥናታቸውንና አመለካከታቸውን ለሕዝብ በውይይትና በክርክር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።  ከዚያ ባለፈ ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቃት ባገናዘበ ሁኔታ፥ እኛ እናውቅልሃለን ብለው ከመወሰን ተቆጥበው፥ ፍርዱን ለሕዝብ እንዲተው ለሂሊናቸው አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።  ይህን አዋቂና ትልቅ ሕዝብ በማክበር ሕዝቡ ያለው እንዲሆን ውሳኔውን ለሕዝብ ይለቃሉ የሚል እምነት አለኝ።

2ኛ/ ሕገ መንግስቱን ማስታመም

ሕገ መንግስቱ ተዐማኒ እንዲሆን ሕዝብ በመረጠው ሞግዚትነት ይፈተሽ ዘንድ ይገባዋል።  ስለዚህ የሕዝብ መንግስት እስኪኖረን ድረስ ወደድንም ጠላንም በዚህ ሕገ መንግስት ታስረናል።  ዝም ብለን በዚህ ሕገ መንግስት ደግሞ ወደ ምርጫው እንዳንሄድ የሕዝብ መንግስት ለመመስረት ብቃት አይሰጠንም።  ስለዚህ ቢያንስ ቢያንስ ምርጫውን በተመለከተ ሕገ መንግስቱ ይፈታን ዘንድ ማሻሻያ ማድረግ የግድ ነው።  ይህን የምርጫ ማሻሻያ ለማድረግ ደግሞ ያለው ፓርላማ አሁንም የሕዝብ ስላልሆነ (በሀቀኛ ምርጫ) ውሳኔ ሊያስተላልፍልን አቅም የለውም።  ስለዚህ ሕገ መንግስቱን የማሻሻያ አውድ ሕዝቡ ራሱ እንዲሰጥ የመንግስትን ዓይነት ለመወሰን (ፕሬዚዳንት ወይስ ጠ/ሚኒስቴር) የሚለውን እንዲረዳ ይህን ሪፈረንደም ማድረግ የሕዝብን መንግስት ለመውለድ ተዐማኒነት ይሰጣል።

3ኛ/ ሁሉ አቀፍ መግባባት ወሳኝ ነው

ዶ/ር አብይ እንደ ሽግግር መንግስት ለማገልገል አሁን አይችሉም።  በአሁን ወቅት ተልዕኳቸው የዲሞክራሲ አዋላጅ መሆን ብቻ ነው።  ከአምባገነንነት ወደ ሕዝብ መንግስትነት የሚያሻግረን በመጀመሪያ ምርጫ የሚመሰረተው የሕዝብ መንግስት ነው።  የመጀመሪያ የሕዝብ መንግስት ለወደፊቱ መሰረት የሚጥል፥ ሕገ መንግስቱን ሕዝባዊ የሚያደርግ፥ አሻጋሪ መንግስት ነው።  ስለዚህ የመጀመሪያው ምርጫ ወደፊት ከምናደርጋቸው ምርጫዎች የተለየና ፈር ቀዳጅ ነው።  ስለዚህ ወደዚህ በዓይነቱ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ አዋላጅ ወደሆነው ምርጫ ስንሄድ ከሞላ ጎደል ሁሉ አቀፍ መግባባት መኖር አለበት።  ለምሳሌ ፕሮፌሰር መራራ ምርጫ እንዳይራዘም ሲሉ፥ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ሊራዘምም ይችላል ሲሉ ይታያሉ።  ሁለቱም የተፈተኑ ንፁህ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ ልባቸው ለኢትዮጵያ ደህንነት እንዲሆን በማለት ብቻ ይህንን ተቃራኒ አሳብ ያነሳሉ።  ታዲያ ሪፈረንደም በሚደረግበት ጊዜ፥ ለዋናው ምርጫ ግብሃት የሚሆን መረጃ /data/ በሁለቱም ጎራ ለተሰለፉ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ይኖራቸዋል።  ሪፈረንደም ሲደረግ የምናየሁ ሁኔታ ምርጫውን ለማድረግ መቼ መቻልን እንደምናገኝ ፍንጭ በመስጠት መግባባት ላይ ያደርሰናል።

4ኛ/ እንከን የለሽ ምርጫ የግድ ነው

ከዚህ በፊት እንደጠቀስኩት የመጀመሪያው ምርጫ የተለየ ነው።  እንከን የለሽ መሆን ያለበትና ውዝግብ የማያመጣ ፍፁምነትን የተላበሰ ምርጫ ማካሄድ እንዳለብን ለድርድር አይቀርብም።  ታዲያ ከዚህ በፊት የተደረጉት ምርጫዎች ውሸት ስለነበሩ የምንማርበት ሆነው አይጠቅሙንም።  ሪፈረንደም ብናደርግ ግን፥ ለወሳኙ ምርጫ መማሪያና ወደፊት ምርጫም ሲደረግ እንከን የለሽ እንዲሆን ቀደም ተብሎ ማስተካከያ ለማድረግ ዕድል ይሰጣል።  ሪፈረንደም ማድረጉ ከታለመለት ዓላማ ተጨማሪ ድምፅ የመስጠት ልምድ የምንቀስምበትና ራሳችንን በብቃት ለምርጫ የምናበቃበት አድማስ ያሰፋልናል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አሰበ። ይጎበኛታልም።

Email: Z@myEthiopia.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule