የገቢዎች ሚኒስቴር 60 ሚሊዮን ብር የሚሆን የውጭ ሃገራት ገንዘብና ሰባት ኪሎግራም ወርቅ ጥር 29/2011 ዓ.ም መያዙን ገለፀ። አራት ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር ቶጎ ውጫሌ ኬላ ላይ ሰባት ኪሎ ግራም ወርቅና ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ሃገራት ገንዘብ መያዙን ገልጿል።
የአሜሪካ፣ የካናዳና የአውስትራሊያ ዶላር፣ ዩሮ፣ ድርሃምና የሌሎች ሃገራት ገንዘብ ነው የተያዘው ብሏል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ።
ትናንት ምሽት ሰባት ኪሎ ግራም ወርቅና መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የውጪ አገር ገንዘብ ከአራት ተጠርጣሪ ኮንትሮባንዲስቶች ጋር በቶጎ ዉጫሌ ኬላ በጉምሩክ ሰራተኞች ተይዟል።
የተያዙት ከሚል ዑመር፣ መሃሪ አብዱ፣መሃዲ ዑመር እና ካልድ አብዲ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡
ዘጋቢ፦ ጋሻው ፈንታሁንና ራሔል ደምሰው (አብመድ)
gi Haile says
They are dead fish, no more corruption and money laundering. Lets other criminals know that there is no place to hide. Super natural eyes and Justice searching for those who violated the law of truth. Enough is enough. Honesty is the best policy thanks to all Customs officials for hunting such bad guys and report them to face justice. We proud of you Customs officials you deserve respect for what you doing. Way to go!