የአምቦ ዩኒቨርሲቲ በሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ስም የባህል ማዕከል እንደሚያቋቁም አስታውቋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታደሰ ቀነዓ ለኢዜአ እንደገለጹት ማዕከሉ የሚቋቋመው የሎሬቱን ጨምሮ በኪነ ጥበብ ሥራዎች ላይ ጥናትና ምርምር ለማድረግና ተሰጥኦ ያላቸውን ጠቢባን ለማፍራት ነው።
“ማዕከሉን ለሟቋቋም ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ተገብቷል” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ማዕከሉን ለማቋቋም ከአዲስ አበባ፣ ከባህር ዳርና ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ልምድ ቀስሟል ብለዋል።
ከሎሬት ጸጋዬ ወጥ ሥራዎች መካከል የአቴቴ ሥርዓት፣ የገዳ ሥርዓት፣ ዝክረ መርካቶ፣ የኩሽ ሕዝቦች ሥልጣኔ፣ ዳግማዊ ቴዎድሮስ፣ ኦዳና አቡነ ጴጥሮስን የሚዘክሩት ተጠቃሽ ናቸው።
ከትርጉም ሥራዎቻቸው መካከል የዊሊያም ሼክስፒር ድርሰቶች ሃምሌትና ኦቴሎ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች ይገኙበታል።
የአምቦ አካባቢ ተወላጅ የሆኑት ሎሬት ፀጋዬ በ60 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም የተለዩት በ1998 ነበር።
ምንጭ፦ ኢዜአ
Alem says
Tsegaye was 69 years old at death, not 60. Please make correction
sergute selassie says
ውዶቼ ይህን ዜና ሳነበው እያለቀስኩኝ ነው ያነበብኩኝ። ይህ እንዲህ ሊሆን ስንቱን የመከራ ጊዜ አሳለፍኩትን። ብቻ ተመስገን!
Sileshi Lemma says
ዛሬ አልነበረም ይህ መሆን የነበረበት፡፡አሁንም አልረፈደም፡፡ እንደኔ ጋሼ ጸጋይን ማሰብ ኢጥዮጲያን ማሰብ ነው፡፡