የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በማለት ራሱን የሚጠራው የበረሓ ወንበዴዎች ስብስብ አባል የነበረው ዛዲግ አብርሃ ከድርጅቱ አባልነት ለቋል። በህወሓት ታሪክ ዓይነተኛ ቦታ የሚሰጠው ይህ ክህደት ድርጅቱን ክፉና ጎድቶታል። ዛዲግን የሚከተሉ ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል ተብሏል። በጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ግንቦት 2፤ 2010 በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ ሆኖ የተሾመው ዛዲግ አብርሃ የካቲት 5፤2011ዓም ከድርጅቱ መልቀቁን በጻፈው አምስት ገጽ ደብዳቤ ገልጾዋል። ከዚህኛው ሹመቱ በፊት ዛዲግ፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጦር እንዲዘምት ትዕዛዝ በሰጠው የጦር ወንጀለኛ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ዘመን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ የነበረው ነገሪ ሌንጮ ምክትል በመሆን ሠርቷል። ከዚያም በፊት “የሕዳሴ ግድብ” አስተባባሪ ኃላፊ ሆኖ መሥራቱ … [Read more...] about ህወሓት በክህደት አከርካሪው ተመታ