በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር ሲል የኢትዮጵያ (ህወሃት/ኢህአዴግ) ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ዓለም በሙሉ በሚያውቀው በየትኛውም ሚዛን እርምጃው ተመጣጣኝም፣ አስፈላጊም አልነበረም ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም “የኢትዮጵያ መንግሥት እንኳን ያላለውን ኮሚሽኑ ደፍሮ ‘ተመጣጣኝ ነው’ ማለቱ አስቂኝም አስገራሚም ነው”ብለዋል። ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው ግጭት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት ሪፖርቱ ሃሣብ ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መስተዳድር ቀደም ብሎ ይቅርታ መጠየቁን አስታውቋል፡፡ ዝርዝሩን ከዚህ በታች ይገኛል ተጭነው ያድምጡ:: (ምንጭ: የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ - VOA) … [Read more...] about ከ300 በላይ ዜጋ መገደሉ “አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነው” የህወሃት ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
Archives for June 2016
መጥፎ እልህ አያራምድም!
እልህ መጋባት በመሠረቱ መጥፎ ጠባይ ነው፤ መጥፎ የሚሆንበትም ምክንያት ዓይንን ስለሚጨፍን፣ ጆሮን ስለሚያደነቁር፣ ልብን ስለሚያደነድን፣ አእምሮን ስለሚዛባ ነው፤ ይህንን ሁሉ የሚያስደርግ ጠባይ መጥፎ ካልተባለ ሌላ ምን ይባላል? በቤተሰብ ውስጥ በባልና ሚስት መሀከል እልህ ከገባ ትዳርን ማፍረሱ የማይቀር ነው፤ ባለሥልጣኖችም ከሕዝብ ጋር እልህ ከተጋቡ እንደልጅነታችን ጨዋታ ፈረሰ! ዳቦ ተቆረሰ! ማለት ነው፤ ክፉ እልህ መጥፎ ነው፤ አገር ያጠፋል፡፡ ፈረንጆች (አውሮፓውያን ነጮች ማለቴ ነው፤) ጥሩ እልህ አላቸው፤ ፍርሃታቸውን ለማሸነፍ እልህ ውስጥ ይገባሉ፤ የሙያ ብቃታቸውን ወደፍጹምነት ለማስጠጋት እልህ ይይዛቸዋል፤ በውድድር አንደኛ ለመውጣት እልህ ውስጥ ይገባሉ፤ … እልሃቸው አያስተኛቸውም፤ እልሃቸው እረፍት አይሰጣቸውም፤ እልሃቸው በርትተው እንዲሠሩ ይገፋፋቸዋል፤ በየጊዜው … [Read more...] about መጥፎ እልህ አያራምድም!
የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ከሌሎች ሀገራት ትግሎች ነጥሎ ማየት አይቻልም!
በመጀመሪያ ደረጃ፤ ለነፃነትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚደረገው ትግል፤ ትክክለኛ መፍትሔ የሚሆነው፤ የማያወላውል ቆራጥ የዴሞክራሲ ጠበቆች ሆነው፤ ለዴሞክራሲ አሰራር ጽኑ ዕምነት ባላቸው ሀቀኛ ታጋዮች ሲመራ ብቻ ነው። የኒህ ታጋዮች የዴሞክራሲያዊ አሰራር እና የነፃነት ምንነት ግንዛቤ፤ እዚህ ቦታ ይሠራል እዚያ ቦታ ግን አይሠራም የሚባል የቦታና የጊዜ ክልል የለውም። ለጊዜያዊ ጥቅም ወይንም አንድን ወገን ጎድቶ ሌላውን ለሚረዳ ተግባር እጃቸውን አይዘረጉም። ለዴሞክራሲ ጥብቅና ለሚቆምና ለምትቆም ግለሰብ፤ ቦታ ሆነ ጊዜ አይከልላቸውም። ያንን በውስጥ የድርጅታቸው አሰራርና በውጭ ግንኙነታቸው ይገልጹታል። ተማሪ ሆኜ፤ ለፓሪስ ኮሚውን መቶኛ ዓመት መታሰቢያ ትምህርት አቁመን ስንዘክር ትዝ ይለኛል። ከኔ የቀደሙት ደግሞ፤ የኢያን ስሚዝን የሮዴዥያ ነፃነት ማወጅ አውግዘው፤ የአፍሪቃ ሀገራት … [Read more...] about የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ከሌሎች ሀገራት ትግሎች ነጥሎ ማየት አይቻልም!
ህወሃት ጉሮሮውን ሳይታነቅ የበላውን በ30 ቀን “እተፋለሁ” አለ
ህወሃት በቦንድ ስም ህግ ጥሶ ሲሰበስብ የነበረውን ገንዘብ ክስ ተመስርቶበት ጉሮሮው ሳይታነቅ ወዶ ለመትፋት መስማማቱ ታወቀ። ድርጊቱ ኢትዮጵያን መሳቂያ፣ የምትተዳደረው በህገ አራዊት መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑንና የህወሃትን የወሮበላነት ባህሪ እርቃን ያወጣ ነው ተባለ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ከውጭ ምንዛሬ ገበያ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ምርመራ ሊካሄድ የሚችልባቸው በርካታ አግባቦች እንደሚኖሩ ነው። ራሱን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ” የሚለው አገዛዝ ከቦንድ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ሰሞኑንን ይፋ የሆነበት ዜና “ነጻ አውጪው ሃይል” አሁንም ከጫካ አስተሳሰብ አለመላቀቁን የሚያመለክት እንደሆነ ተጠቆመ። በፍርድቤት ተከስሶ እና ጉሮሮውን ታንቆ ከውርደት ጋር በርካታ የገንዘብ ክፍያ ውስጥ ከመግባቱ በፊት “ጥፋተኛ ነኝ፤ ፍርድቤት አትውሰዱኝ፤ ያላችሁኝን አደርጋለሁ” በማለት … [Read more...] about ህወሃት ጉሮሮውን ሳይታነቅ የበላውን በ30 ቀን “እተፋለሁ” አለ
ከፍትህና ከዲሞክራሲ እየተጣሉ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ መቆም አይቻልም!
“ለትግላችን ብቸኛውን ሚና የሚጫወተውን የኤርትራ ሕዝብና መንግስትን ለማዳከም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያደርገውን ሴራ ለመቃወም ይህንን ፒትሽን ፈርሙ” – ነአምን ዘለቀ (አ. ግንቦት 7) “Particular individuals, including officials at the highest levels of State, the ruling party – the People’s Front for Democracy and Justice – and commanding officers bear responsibility for crimes against humanity and other gross human rights violations.” UN UN Commission of Inquiry on Human Rights in Eritrea ሰሞኑን በማህበረ-ድረገጾች ላይ ግንቦት 7 በአመራሩ አቶ ነአምን ዘለቀ በኩል ያቀረበውን የኤርትራን … [Read more...] about ከፍትህና ከዲሞክራሲ እየተጣሉ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ መቆም አይቻልም!
The mad mullah of 21st century, Abdi Mohamed Omar, Somali Regional State President
The Somali Regional State is inhabited by all Somali Clans. Even there are some Somali clans that exclusively live in Ethiopia only. Despite the fact that the Somali Regional State is inhabited by all Somali clans, the regional state is currently completely dominated by one clan. It is true that most of Somali clans that inhabit Ethiopia have rarely fought against the Ethiopian government or people. The Ethiopia’s government, however, seems to ignore the pleas of many Somali clans that are daily … [Read more...] about The mad mullah of 21st century, Abdi Mohamed Omar, Somali Regional State President
ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ ና የገቢማስባስቢያ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ ! |
የእለቱ እንግዶች በተገኙበትሕዝባዊ ስብሠባው በኖሬጅያውያን የሰአተ አቆጣጠር ከቀኑ 16:15 ተጀምሮ እስከ ምሽቱ 00:00 ሰዓት የተካሄደ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አቢ አማረ የለቱን ፕሮግራም በማስተዋወቅ ለዝግጁት ታዳሚውች እንኮን ደህና መጣችሁ በማለት ለዝግጅቱ መሳካት ክተለያየ ቦታ እርቀት ሳይገድባቸው ረጅም መንገድ ተጉዘው ለተገኙ እንግዶቻችን በድርጅታቸው ስምና ታላቅ ምስጋ ና አክብሮት ክአቀረቡ ቡሀላ የለቱ ፕሮገራም የመክፈቻ ንግግር በማድረገ አስጀምረዋል አያይዘውም በኢትዮጵያ ውስጥ በመላ የሀገራችን ህዝቦች በወያኔ አረመናዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ አስር ቤቶች በፖለቲካ ኣስተሳስባችው ምክንያት ያለወንጀላች የሚስቃዩ ውድ ኢትዮጵያዊን ወገኖቻችን በማስብ እንዲሁም አስቃቂ የኣካል ጉዳት ለተፈጸባቸው … [Read more...] about ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ ና የገቢማስባስቢያ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ ! |
የሸንጎ ድምጽ – ልዩ ዕትም
በአንድ ከባቢ የሚኖሩ ሰዎች ድንገት ሰፈራቸው በእሳት ጋይቶ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ፣ምናልባት ብንድን ብለው ወደሌላ አቅጣጫ ካለው ሰፈር ለመጠለል ሲሮጡ፣ ከዛኛውም ሰፈር እንደዚሁ እሳት ተነስቶ ኑሮ፣ ብዙ ሰዎች ወደዚህኛው ሰፈር ሲገሰግሱ መሃል ቦታ ላይ ተገናኙ። ከመካከላቸው አንዱ የእኛ ሰፈር በእሳት ጋይቶ ለመጠለል ወደ እናንተ ሰፈር እየመጣን እናንተ ደግሞ በእጥፍ ቁጥር ወደእኛ እየገሰገሳችሁ ነው፡፡ ለመሆኑ የደረሰብንን ጉዳት ሰምታችሁ እሳቱን ለማጥፋት ነው ወይስ እኛን ከመንገድ ላይ ተቀብላችሁ ልታስተናግዱን ነው ይኸ ሁሉ ሰው የመጣው? ብሎ የወዲያኛውን ሰፈር ኗሪ ጠየቀ። የተጠየቀውም ሰው ግር ብሎት የእሳቱ መነሳት እንዴት ከእናንተ ጆሮ ደረሰ? ለማጥፋት ልትተባበሩን ነው የመጣችሁት? ብሎ በመገረም መልሶ ጠየቀው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የሸንጎ ድምጽ – ልዩ ዕትም
“[እምቢ ካሉ] አጠቃላይ የትምህርት ሥርዓቱን የሚያሽመደምድ ስልት አለን”
ህወሃት ኦህዴድን ለማጽዳት በሚል ከ800 የሚበልጡ ሃላፊዎችን በየእርከኑ ቢያሰናብትም ለውጥ የሚታይ አልሆነም። ይልቁኑም የተጠኑ በሚመስሉ ማህበራዊ ጉዳዮች መናጡ እየተባባሰ ነው። አቶ ጃዋር መሐመድ ኢህአዴግ የቀረበለትን “የምክር ሃሳብ” የሚሰማ ካልሆነ አጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱን የሚያሽመደምድ ስልት አለን ማለታቸው “እንዴት” የሚል ጥያቄ ቢያስነሳም ጆሮ ያገኘ ወሬ ሆኗል። ይህንኑ ተከትሎ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ጉዳዩን ከተወዳጁ ደራሲ በአሉ ግርማ ትንቢታዊ ድርሰት ጋር በማያያዝ “የኢህአዴግ ኦሮማይ እየተቃረበ ነው” ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል። በትላንትናው እለት የቪኦኤ አማርኛ ክፍለ ጊዜ ካቀረበው ቃለ ምልልስና ካጠቃላይ እውነታዎች ለመረዳት እንደተቻለው ኦሮሚያ ውስጥ የተጀመረው “ሰላማዊ” ትግል እየበሰለ የሄደ ይመስላል። ቀደም ሲል በተደረጉ የድርጅትና የውስጥ ግንኙነቶች የኦሮሞዎች … [Read more...] about “[እምቢ ካሉ] አጠቃላይ የትምህርት ሥርዓቱን የሚያሽመደምድ ስልት አለን”
“የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች እስካልተቀየሩ ድረስ ሕይወታችን የከፋ አደጋ ላይ ነው”
ዛሬ አቶ በቀለ ገርባ በውስጥ ከነቴራ፣ በቁምጣና በባዶ እግራቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ጉዳዩን የተከታተለው ኤሊያስ ገብሩ ጎዳና ይህንን የአቶ በቀለን ንግግር በፌስቡክ ገጹ ላይ አትሞአል፡፡ ይህ ምስክርነት በፍርድ ቤት ካሰሙ በኋላ በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በ እንግሊዝኛ በየማህበራዊ ገጾችና ድረገጾች ተሰራጭቶዋል፡፡ "በባለፈው ቀጠሯችን ለብሰን ፍርድ ቤት ልንቀርብ የነበረውን ጥቁር ልብስ አውልቁ ተባልን፡፡ አናወልቅም አለን፡፡ የፈለግነውን የመልበስ ሕገ-መንግስታዊ መብታችን ነው፡፡ ጥቁር ልብስ የለበስነውም፤ ከ50ሺህ በላይ የአንድ ብሄር ተወላጆች እስር ቤት መገኘታቸውንና በዚህ ዓመትም በጥቂት ወራት ውስጥ ከ200-300 የሚደርሱ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች መገደላቸውን በማዘን ለመግለጽ ነው፡፡ ድርጊታችንም ይሆን የነበረው የፍርድ ቤትን አሰራርን ምንም በማይነካ መልኩ በሰላም … [Read more...] about “የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች እስካልተቀየሩ ድረስ ሕይወታችን የከፋ አደጋ ላይ ነው”