• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች እስካልተቀየሩ ድረስ ሕይወታችን የከፋ አደጋ ላይ ነው”

June 3, 2016 05:38 am by Editor 1 Comment

ዛሬ አቶ በቀለ ገርባ በውስጥ ከነቴራ፣ በቁምጣና በባዶ እግራቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ጉዳዩን የተከታተለው ኤሊያስ ገብሩ ጎዳና ይህንን የአቶ በቀለን ንግግር በፌስቡክ ገጹ ላይ አትሞአል፡፡ ይህ ምስክርነት በፍርድ ቤት ካሰሙ በኋላ በአማርኛ በኦሮሚኛ እና በ እንግሊዝኛ በየማህበራዊ ገጾችና ድረገጾች ተሰራጭቶዋል፡፡


“በባለፈው ቀጠሯችን ለብሰን ፍርድ ቤት ልንቀርብ የነበረውን ጥቁር ልብስ አውልቁ ተባልን፡፡ አናወልቅም አለን፡፡ የፈለግነውን የመልበስ ሕገ-መንግስታዊ መብታችን ነው፡፡ ጥቁር ልብስ የለበስነውም፤ ከ50ሺህ በላይ የአንድ ብሄር ተወላጆች እስር ቤት መገኘታቸውንና በዚህ ዓመትም በጥቂት ወራት ውስጥ ከ200-300 የሚደርሱ የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች መገደላቸውን በማዘን ለመግለጽ ነው፡፡ ድርጊታችንም ይሆን የነበረው የፍርድ ቤትን አሰራርን ምንም በማይነካ መልኩ በሰላም ነው፡፡ ይሄ አይሆንም ተብለን ዛቻና ስድብ ተደሰብን፡፡

“ትናንት ከሰዓት በኋላ ዛሬ ፍርድ ቤት የምንቀርብ ሰዎች ለይተን ከየክፍላችን እንድንመጣ ተደረገ፡፡ ልብሶቻችንንም ይዘን እንድንወጣ አደረጉ፡፡ ከልብሶቻችን መካከል ጥቁር ልብስ እየተፈለገ ተወሰደ፡፡ እኛም ‘ልብሶቻችንን በሙሉ ልትመልሱልን ይገባል’ ብለን ጠየቅን፡፡ ወደጨለማ ክፍል ወሰዱን፡፡ ከመካከላችን የተወሰኑትንም ክፉኛ ደበደቧቸው፡፡ የተደበደቡት ሰዎች እዚሁ ስላሉ ለችሎቱ መናገር ይችላሉ፡፡ ልብሶቻችን ሜዳ ላይ ተበትኖ ስለነበረ ሌሎች እስረኞች የሚፈልጉትን ወሰዱ (ተቀራመቱት)፡፡ የተረፈውን አምጥተው ክፍላችን ውስጥ አስቀመጡት፡፡ bekele

“ዛሬም ድረስ ምግብ አልበላንም፡፡ እጆቻችን ጥዋት ድረስ በካቴና ታስሮ ነበር፡፡ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ድርጊት ነው የተፈጸመብን፡፡ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ እየተመረጠ ተደብድቧል፡፡ የታሰርንበት ቦታ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ተቋም ነው፡፡ ‘አንተ ነህ እንዲህ የምታደርገው፡፡ እናገኝሃለን’ ብለውኛልም፡፡

“ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ/ተቀያሪ ማቆያ ቦታ ያዘጋጅልን፡፡ አሁንም ተመልሰን ቂሊንጦ ስንሄድ ምን እንደሚደርስብን አናውቅም፤ ስጋት አለን፡፡ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች እስካልተቀየሩ ድረስ ሕይወታችን የከፋ አደጋ ላይ ነው፤ በጣም ያሰጋናል፡፡ ለቀጣይ ቀጠሮ መገኘታችንም እርግጠኞች አይደለንም፡፡ ቤተሰቦቻችን እንዳያዩን እየተደረገ ነው፡፡ ዛሬም ፍርድ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከገባን በኋላ ሰዎች እንዳያዩን ተደርጓል፡፡ እንዲህ የተድበሰበሰ ነገር መንግስት ለምን ይሰራል? እንደዜጎች እየተቆጠርን አይደለም፡፡”

[ይህንን ልብ የሚነካ ንግግር ከአንድ ሰዓት በፊት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ቆመው ሲናገሩ ያደመጥኳቸው በጸረ-ሽብርተኝነት ወንጀል ተከስሰው ከ22 ሰዎች ጋር የፍርድ ሂደታቸውን የሚከታተሉት አቶ በቀለ ገርባ ነበሩ፡፡ አቶ በቀለ በዛሬው የችሎት ወሎ ከፊል ሰውነታቸውን የሚሳይ የውስጥ ነጭ ከነቴራ (ፓክ-አውት)ና ጥቁር ቁምጣ ለብሰው በባዶ እግራቸው ነበሩ፡፡ (ሌሎች አምስት ተከሳሾችም ተመሳሳይ አለባበስ ለብሰው ነበር) በቅርብ ርቀት እንዳየኋቸው ከሆነ፣ የግንባራቸው ደምስር ጎሎቶ ይታያል፡፡ እንቅልፍ አለመተኛታቸውንም ፊታቸው ይናገራል፡፡ በችሎቱ የነበሩ ከ10 በላይ ወታደሮች (መሳሪያ የታጠቁም ጭምር) የአቶ በቀለን ንግግር በተመስጦ ሲዳምጡ አስተውያለሁ፡፡ …እንግዲህ 25 ዓመታትም ታልፎ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ በእስረኞች ላይ አንድም ይህንን ይመስላል፤ ማዘን ብቻ!] (ፎቶ: Ethiopia Ethiopia ፌስቡክ የተገኘ – እነ አቶ በቀለ ገርባ በፍርድቤት በቀረቡ ጊዜ የእጅ ስልኮች ፍጹም የተከለከሉ ቢሆንም ባቅራቢያው በነበሩ የለበሱትን የሚያሳይ በእጅስልክ የተነሳ)

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Rasdejen says

    June 9, 2016 09:20 pm at 9:20 pm

    Stop blaming Holy TPLF and enjoy watching these:

    1. https://www.youtube.com/watch?v=-pn6w5vvMO8

    2. https://www.youtube.com/watch?v=O-QmWORxnKQ

    3. https://www.youtube.com/watch?v=MxIZAjxMhHQ

    4. https://www.youtube.com/watch?v=e7wqbM4y_6M

    5. https://www.youtube.com/watch?v=je23QNfN8tA

    6. https://www.youtube.com/watch?v=miMBghOvrvo

    7. https://www.youtube.com/watch?v=czT4OtG48S8

    8. https://www.youtube.com/watch?v=czT4OtG48S8

    9. https://www.youtube.com/watch?v=0F93U9BQIfI

    10. https://www.youtube.com/watch?v=v0qSVRT17Xk

    11. https://www.youtube.com/watch?v=6S72PX8JxAQ

    12. https://www.youtube.com/watch?v=jZ0T9y6pumk

    13. https://www.youtube.com/watch?v=aCk-rMSr6ro

    14. https://www.youtube.com/watch?v=8kcJyCxylCM

    15. https://www.youtube.com/watch?v=9WNI6p-ue-A

    16. https://www.youtube.com/watch?v=0ZZRp5EMt1I

    17. https://www.youtube.com/watch?v=OfGVBh7-w6c

    18. https://www.youtube.com/watch?v=LVKCwedFU3w

    19. https://www.youtube.com/watch?v=7MtwMUTWzos

    20. https://www.youtube.com/watch?v=flsLGLkRgXY

    21. https://www.youtube.com/watch?v=dkdkZWKPJRI&list=PLEGZNjdn0MM658xCi5V4qFTmAswCEfxMx

    22. https://www.youtube.com/watch?v=n6t7dDhSPhI&list=PLjc6iyLtkLuT_HAqLAmyl4yfDS4KNVGHV

    23. https://www.youtube.com/watch?v=OuW4rzqLWOY

    24. https://www.youtube.com/watch?v=f90xVlV44cw

    25.https://www.youtube.com/watch?v=ZWhW34r0rNg

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule