• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ ና የገቢማስባስቢያ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ ! |

June 7, 2016 04:50 am by Editor Leave a Comment

የእለቱ እንግዶች በተገኙበትሕዝባዊ ስብሠባው በኖሬጅያውያን የሰአተ አቆጣጠር ከቀኑ 16:15 ተጀምሮ እስከ ምሽቱ 00:00 ሰዓት የተካሄደ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አቢ አማረ የለቱን ፕሮግራም በማስተዋወቅ ለዝግጁት ታዳሚውች እንኮን ደህና መጣችሁ በማለት ለዝግጅቱ መሳካት ክተለያየ ቦታ እርቀት ሳይገድባቸው ረጅም መንገድ ተጉዘው ለተገኙ እንግዶቻችን በድርጅታቸው ስምና ታላቅ ምስጋ ና አክብሮት ክአቀረቡ ቡሀላ የለቱ ፕሮገራም የመክፈቻ ንግግር በማድረገ አስጀምረዋል አያይዘውም በኢትዮጵያ ውስጥ በመላ የሀገራችን ህዝቦች በወያኔ አረመናዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ አስር ቤቶች በፖለቲካ ኣስተሳስባችው ምክንያት ያለወንጀላች የሚስቃዩ ውድ ኢትዮጵያዊን ወገኖቻችን በማስብ እንዲሁም አስቃቂ የኣካል ጉዳት ለተፈጸባቸው ኢትዮጵያዊን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማስደረግ ስብሰባውን አስጀምረውታል::

በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አበበ ፕሮግራሙን እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኃላ በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከተለያዩ ሐገሮች ለመጡት አባላት እና ደጋፊዎች ያላቸውን አክብሮት እና ምስጋና አቅርበዋል። በእለቱ ለተገኙት የክብር እንግዶችም እጅግ ጠቃሚ እና ትምሕርት አዘል ንግሮችን አድርገው እንዳለቀ ዶ/ር ሙሉ አለም አዳም ፕሮግራሙን መሪ መድረኩ አስጀምረውታል።

በዝግጅቱም ላይ በእንግድነት ከተጋበዙት የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ ከኤርትራ በረሃ፣ ፕሮፈሰር ጌታቸው በጋሻው በተጨማሪም የኢሳት ጋዜጠኞች ገሊላ መኮንን አምስተርዳም እና መታሰቢያ ቀፀላ ለንደን እንግድነት ተገኝተዋል። በዚህም ዝግጅት ፕሮፈሰር ጌታቸው ስለ ኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ ትንተና በሰፊው ገልፀዋል።

ፕሮግራሙን በሰፊው ሲጠበቅ የነበረው የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሀኑ ንግግር በመቀጠል በአገሩቱ ውስጥ እየተደረገ ያለውን ትግል ሰፊ እና ጥልቅ ማብራሪያ አቅርበው በደቡብ አፍሪካ እንዲሁም በተለያዮ አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኞች አስከፊው ስደትና መከራ በወያኔ መንግስት በመሸሽ እያደረሰባቸው ባለው ስቃይ ለዚ አስከፊ ስደት የዳረጉን የወያኔን የግፍ አገዛዝ ጫፍ መድረሱንም ጭምር ያሳየ ምልክት ነው በድርጊታቸውም በቃ ልንላቸው ይገባል ትግሉን መደገፍ ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል። noslo

በቀጣዮም ፕሮግራም ታዳሚው ያልተጠበቀው ለተሳታፊውም በዓነቱ እንግዳ የሆነ ነገር በመከሰቱ ህዝቡን ያስደሰተ ክስተት ተከሰተ። በዝግጅቱም ላይ ከተሳታፊዎች ፊታቸውን በከፊል በመሸፈን ዝግጅቱን ሲከታትርሉ የነበሩት ግለሰብ ማንነታቸው በመድረክ ላይ በመወጣት ተሳታፊ ያስደመመ ያስደተና የአንድነት መንፈስን የበለጠ ያጠናከረ ክስተት በአንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙነሽ ፅጌ ያልተጠበቁ እንግዳ ሆነው ተገኝተዋል። ወ/ሮ ብዙነሽ ጽጌ ግጥም በማቅረብ ተሳታፊው በእንባ ፥ በቁጭት ስሜት ያንገበበ መልዕክት ያለው ግጥም አስተልፈዋል። የተወሰን ደቂቃ የምሳና ሻይ እረፍት በማድረግ በቀጥታ ወደ ልዩ ታሪካዊ የጨረታ ዝግጅት ነበር የታለፈው በጨረታውና የገቢ ማሰባሰቢያ የቀረበው ፎቶ የታጋይ አርበኛ ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ፣ አርበኛ ታጋይ መዓዛ ፅጌ እና አንዳርጋቸው ፅጌ በ አንድ ላይ ያጠቃለለ ነበር። ለጨረታው ቀርቦ የነበረው ከፍተኛ ዋጋ በ ወ/ሮ ብዙ አየሁ ፅጌ አሸንፈዋል። በጨረታውም ያሸነፉትን የሶስቱ ታጋይ አርበኞች ፎቶ መልሰው ለአዘጋጁ አስረክበዋል አዘጋጁም ከረጅም ርቀት ተጉዘው ከስዊድን አገር ለመጡ አገር ወዳድ አርበኞች አስረክበዋል። በፕሮግራሙ ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያዊነት ነግሶ የታየበት ነበር ። በቀሪ ልዩ ዕጣ የወጣላቸው በልዮ ስሙ ኦታ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የትግሉ አጋር በዕጣው የወጣላቸውን የኮምፒተር ዕጣ ለ አርበኞች ግንቦት 7 አባልት እና ደጋፊ ለትግሉ ይጠቅማል በማለት በስጦታ መልክ ለግሰዋል። ሌላም ሌላም ስጦታዎች የተካተቱበት እና ለትግል ሜዳ ለተሰማሩት አጋር ጋዶች የሚሆን በ አንድ ግለሰብ 1000 ቲሸርት በስጦታ ተለግሰዋል። በማጠቃለያውም በ ኖርዌዳን ክሮነር 800,162 /ስምንት መቶ ሺህ አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ሳንትም/ ተሰብስቦዋል። የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በተካሄደው የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ በደመቀ ሁኔታ እንዲሳካ ላደረጋችሁ የነጻነት ታጋዮች ሁሉ ድርጅቱ የተሰማውን ትልቅ አድናቆት በምስጋና ሲገልጽ በተለይ ከስዊድን እንዲሁም ከሰሜንና ከተለያየ የአውሮፓ ክፍል የመጣችሁ፣ ከበርገን፣ ከትሮንድሃየም፣ ከክርስትያንሳንድ፣ ስታቫንገር እንዲሁም ከተለያየ የኖርዌይ ቦታ የመጣችሁ፣ በማያያዝም የከረንት አፌር ፓል ቶክ ሩም እንዲሁም ኢካዴፍ ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና ስናቀርብ በማያያዝ የፍጻሜ የትግሉ ለሚጠይቀው መስዋእትነት ከአፍ ባለፈ በተግባር ስላሳያችሁት አጋርነት የነጻነት ታጋዮች ሁሉ ድርጅቱ የአክብሮት ምስጋናውን ያቀርባል፣ በተለይ የዘረኛው የጥጵልፍ አቃጣሪ ቡችሎች ፕሮጋራማችንን ለማስተጓጎን ያደረጉትን ያልተሳካ ሙከራ ከነሱ ውስጥ በመሆን እንቅስቃሴያቸውም ስታቀብሉን ለነበር የውስጥ አርበኞች ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና እናቀርባለን፣ በስተመጨረሻ ከአገር ቤት በመደወል የገንዘብ ድጋፍ ላደረጋችሁንም ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

ኢትዮጵያችን በክብር ለዘላለም ትኖራለች

ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ !

ዳዊት አበበ

dceson@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule