• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከፍትህና ከዲሞክራሲ እየተጣሉ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ መቆም አይቻልም!

June 9, 2016 05:00 am by Editor Leave a Comment

“ለትግላችን ብቸኛውን ሚና የሚጫወተውን የኤርትራ ሕዝብና መንግስትን ለማዳከም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያደርገውን ሴራ ለመቃወም ይህንን ፒትሽን ፈርሙ” – ነአምን ዘለቀ (አ. ግንቦት 7)

“Particular individuals, including officials at the highest levels of State, the ruling party – the People’s Front for Democracy and Justice – and commanding officers bear responsibility for crimes against humanity and other gross human rights violations.” UN UN Commission of Inquiry on Human Rights in Eritrea

ሰሞኑን በማህበረ-ድረገጾች ላይ ግንቦት 7 በአመራሩ አቶ ነአምን ዘለቀ በኩል ያቀረበውን የኤርትራን መንግስት ደግፉልን የሚል ጥሪ የያዘ አንድ የቪዲዮ ምስል ተመልክቼ ነበር፡፡ ላላያችሁት ቪዲዮው ይህንን ቢጫኑ ያገኙታል፡፡

የድርጅታቸው ጥሪ ባጭሩ ጥላና ከለላ የሆነንን የኤርትራን መንግሥት የአለም አቀፉ ማህበረሰቡ በክፉ አይን እያየብን ነውና የኢሳያስን መንግስት በክፉ አይን ያየውን የተባበሩት መንግስታት በማውገዝ ለኢሳያስ ያለንን የወዳጅነት ድጋፍ ለማሳየት ከዚህ የሚከተለውን ፊርማ በመፈረም አጋርነታችሁን ግለጹ የሚል ነው፡፡ የፊርማ ማሰባሰቢያው መልዕክትም ይህን ይመስላል፡-

I Reject the COIE and SR Report

I the undersigned, categorically and unequivocally reject the politically motivated report of the Report of the Commission of Inquiry on Human Rights in Eritrea (COIE) and the Special Rapporteur (SR) on the Human Rights Situation in Eritrea.

The resolution and the appointment of the SR and establishment of the COIE are in fact a continuation of an orchestrated 16-year long political campaign that seeks to demonize and delegitimize Eritrea in the international arena, and erode the final and binding Eritrea Ethiopia Boundary Commissions delimitation and demarcation decisions.

ወደ ግል አስተያዬቴ ከመግባቴ በፊት ይህ የኤርትራን መንግስት ሰላም የነሳውና ስጋት ውስጥ የጣለው፤ እንዲሁም የግንቦት 7 አመራሮች አይናቸውን በጨው አጥበው ያለ አንዳች ሃፍረት በአደባባይ የተቃውሞ ጥሪ ያቀረቡበትን ሪፖርት ይዘት ላላያችው ሰዎች ነገሩን ለማመዛዘን ያመቻችሁ ዘንድ ይህን ቪዲና የተባበሩት መንግስታትን መግለጫ ከዚህ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመጨቆን ልትመለከቱዋቸው ትችላላችዉ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ትላንት ባወጣው በዚህ ሪፖርት አንባገነኑ የኤርትራ መሪ አቶ ኢሳያስ በዜጎቻቸው ላይ የሰውን ስብእናን የሚጻረር ከፍተኛ ወንጀል መፈጸማቸውን ያረጋገጠ መሆኑን እና ለዚህም ወንጀላቸው ተጠያቂ መሆናቸውን ገልጽዋል፡፡ እንዲህም ሲል በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የከፋ ሁኔታ ገልጻል፡-

“There is no genuine prospect of the Eritrean judicial system holding perpetrators to account in a fair and transparent manner. The perpetrators of these crimes must face justice and the victims’ voices must be heard. The international community should now take steps, including using the International Criminal Court, national courts and other available mechanisms to ensure there is accountability for the atrocities being committed in Eritrea”

አምባገነኑ ኢሳያሳ አፎረቄ አመራር በዙ ሺ ዎች ተገድለዋል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኤርትራዊያንን ከአገር ተሰድደዋላ፤ በሪፖርቱ ላይ እንደተገለጸው በ2015 ብቻ ከ42 ሺ በላይ ኤርትራዊያን ከአገር ተሰደዋል፣ እጅግ በርካቶች ታፍነው የደረሰቡበት አይታወቅም፤ ይህም ጋዜጠኞችን እና ምሁራንን ያካትታል፡፡

ከዚህ አይነቱ አውሬ አንባገነናዊ ሥርዓት ጋር ግንባር ፈጥሮ ሥልታዊ የሆነ የመታገያ መንገድ ማመቻቸት አልበቃ ብሎ ይህ ወንጀለኛ ሥርዓት እንዳይወገድ በፊርማችሁ ድጋፍ አድርጉለት ብሎ አይን ባወጣ መልኩ በአደባባይ ጥሪ ማድረግ የግንቦት 7 አመራሮችን ከግራ መጋባት ያለፈ ክሽፈት ከማሳየት ባለፈ እንታገልለታለን ከሚሉት የፍትህና የዴሞክራሲያዊ መርህ በምን ያህል ጥልቀት በተቃርኖ መቆማቸውንም ነው የሚያመላክተው፡፡

በአዲስ አበባ የከተመውን እና ለ25 አመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያስለቅስ፣ ሲገድል፣ ሲያፍን፣ ሲያስርና ለስደት ሲዳርግ የኖረውን የወያኔን ክፉና አፋኝ ሥርዓት ሊዋጋ አደባባይ የወጣና ጫካ የገባ ኃይል፣ ወያኔ ማቅ ያለበሰውን እና መቀመቅ የከተተውን የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የሕግ ልዕልና ጭላንጭል በትግላችን ከወደቀበት ቅርቃር አውጥተን ኢትዮጵያን የሰላም፣ የልማትና የዜጎች ነጻነት ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠባት አገር እናደርጋለን ብለው ሌት ተቀን የሚምሉና የሚገዘቱ የግንቦት 7 አመራሮች ምን ግራ ቢገባቸው ነው በአደባባይ አለም በሰው ዘር ላይ የከፋ ወንጀል በመፈጸም ተጠታቂ ያደረገውን የኤርትራን መንግስት ለመታደግ ባደባባይ ድጋፍ የሚያሰባስቡት፡፡

ለሻቢያ እድሜ እየለመኑ የወያኔን እድሜ ያሳጥርንልን ማለት ለእኔ ግራ ከመጋባት ያለፈ ትርጉም የለውም፡፡ ሁለትም ከአንድ ምንጭ የተቀዱ፣ በአንድ መስክ ያደጉ፣ በአንድ አይነት መርዝ የናወዙ፣ በተመሳሳይ የጥፋት ተልኮ ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያንና የዛሬዋን ኤርትራን ተባብረው መቀመቅ የከተቱና ሕዝቦቹንም ያዋረዱ እኩይ ስርዓቶች ናቸው፡፡

እንደ ግንቦት 7 ላለ ድርጅት መመሸጊያ በማጣት ኤርትራ በርሃዎች ውስጥ መከተሙና ወያኔን ለማስወገድ ከኢሳያስ ጋር ማደሙ አማራጭ ላይኖረው ይችላል፡፡ ከዚያ ባለፈ ኢሳያስን ታላቅና ተወዳጅ መሪ በማስመሰልና ሌላው አለም፤ የተባበሩት መንግስታትና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በኢሳያስ ላይ የሚያሰሙትን እሮሮና ውንጀላ ለመከላከል እሱን በማውገዝ ለኢሳያስ ጥብቅና መቆም በታሪክ ተጠያቂ ያደርጋል፤ በነገው የሁለቱ አገሮችና ሕዝቦች ግንኙነትም ላይ መጥፎ ጠባሳን ይተዋል፡፡

ከዚያም ባለፈ ይህ አይነቱ ድርጊት ኢሳያስን ከመደገፍ ባለፈ በኤርትራ በየማጎሪያ ቤቱ ታስረው ስቃይ በሚፈጸምባቸው ግፉአን ላይ ማላገጥ ነው የሚሆነው፡፡ ለብዙ ሚሊዮን ኤርትራዊያን ሲዖል የሆነችው አገራቸው ለእኛ መሸሸጊያ ሆናናለች በሚል እርካሽ ስሌት የኢሳያስን እድሜ ያርዝምልን፣ ሻቢያንም በመንበሩ ያቆይልን የሚለው ጸሎት በምድርም በሰማዩም ሰሚ ባይኖረውም ያስተዛዝባል፡፡ ከግፉአን ጎን አብረን መቆም ቢያቅተን እንኳ በበደላቸው ላይ ሌላ በደል እንዲፈጸም በሃሊዮም ይሁን በግብር ከግፍ ፈጻሚዎቹ ጎን እንዳንቆም የሚያደርገን ትንሽም የሞራን እንጥፍጣፊ ካለች ትበቃናለች፡፡ የግንቦት 7ቱ አቶ ነአምን ዘለቀ ጥሪ ግን በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ የፓርቲዎች ክርክር ወቅት “ማፈር ድሮ ቀረ” የምትለዋን የፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን ንግግር አስታወሰኝ፡፡

አገርን የማዳኑ ትግል እየተስተዋለ ቢሆን ይበጃል!
ያሬድ ኃይለማርያም፣ yhailema@gmail.com
ከብራስልስ፣ ቤልጂየም


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule