• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሃት ጉሮሮውን ሳይታነቅ የበላውን በ30 ቀን “እተፋለሁ” አለ

June 11, 2016 05:09 am by Editor 4 Comments

ህወሃት በቦንድ ስም ህግ ጥሶ ሲሰበስብ የነበረውን ገንዘብ ክስ ተመስርቶበት ጉሮሮው ሳይታነቅ ወዶ ለመትፋት መስማማቱ ታወቀ። ድርጊቱ ኢትዮጵያን መሳቂያ፣  የምትተዳደረው በህገ አራዊት መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑንና የህወሃትን የወሮበላነት ባህሪ እርቃን ያወጣ ነው ተባለ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ከውጭ ምንዛሬ  ገበያ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ምርመራ ሊካሄድ የሚችልባቸው በርካታ አግባቦች እንደሚኖሩ ነው።

ራሱን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ” የሚለው አገዛዝ ከቦንድ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ሰሞኑንን ይፋ የሆነበት ዜና “ነጻ አውጪው ሃይል” አሁንም ከጫካ አስተሳሰብ አለመላቀቁን የሚያመለክት እንደሆነ ተጠቆመ። በፍርድቤት ተከስሶ እና ጉሮሮውን ታንቆ ከውርደት ጋር በርካታ የገንዘብ ክፍያ ውስጥ ከመግባቱ በፊት “ጥፋተኛ ነኝ፤ ፍርድቤት አትውሰዱኝ፤ ያላችሁኝን አደርጋለሁ” በማለት ተስማምቶ ራሱን ለክፍያ አዘጋጅቷል፡፡SEC-Headquarters-1

በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል (SEC) Securities and Exchange Commission (የዋስትናዎችና ልውውጥ ኮሚሲዮን) ተብሎ የሚጠራው የአሜሪካ ፌዴራል መንግሥት መሥሪያቤት ከተቋቋም 80ዓመታት ያለፉት ሲሆን ሶስቱ መሠረታዊ ተልዕኮዎቹ ባለሃብቶችን መከላከል፤ የፋይናንስ ገበያው በሥርዓት፣ በብቃትና በእኩልነት እንዲካሄድ ማድረግና የካፒታል ምስረታን ማበረታታት ናቸው፡፡

ኮሚሽኑ ሰኔ 1፤2008ዓም (June 8, 2016) ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት በማለት የጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (በቀድሞ ስሙ የኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን) በአሜሪካ ውስጥ ያልተመዘገቡ ቦንዶችን በመሸጥ ለፈጸመው ወንጀል 6.5 ሚሊዮን ዶላር (በግምት 150ሚሊዮን ብር) ለመክፈል መስማማቱን ገልጾዋል፡፡

በተለምዶ “የአባይ ቦንድ” ተብሎ የሚጠራውን አሜሪካ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለ አሜሪካ መንግሥትና ያለ ኮሚሽኑ ፍቃድ መሸጡ በማስረጃ ሲረጋገጥ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከማምራቱ በፊት Abay-bondህወሃት 6.5 ሚሊዮን ዶላር ለኮሚሽኑ ለመክፈል መስማማቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አንዳንድ ወገኖች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ቢመራ ኖሮ ከሚያስከትለው ከፍተኛ የፖለቲካ ኪሣራ በተጨማሪ የቅጣቱ መጠን ከዚህ በእጅጉ እንደሚልቅ ያስረዳሉ፡፡ ሁኔታው ያላማረው ህወሃት ከጠበቆች በተሰጠው ሙያዊ አስተያየት በመነሳት ጥፋቱን አምኖ ክሱን በስምምነት ለመዝጋት መወሰኑን ስለ ጉዳዩ በቅርበት የሚያውቁ ለጎልጉል በሰጡት አስተያየት ጠቁመዋል፡፡

ጉዳዩ በሕግ የሚታይ በመሆኑ ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው የክስ ማመልከቻ ላይ በግልጽ እንዳመለከተው ኮርፖሬሽኑ እኤአ ከ2011 እስከ 2014 ድረስ ያለ አንዳች ፈቃድ በአሜሪካ በተለያዩ ዋና ዋና ከተሞች ሕገወጥ ቦንድ ሲሸጥ ቆይቷል፡፡ ይህንንም ለማድረግ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው “ኤምባሲ” (የኢህአዴግ ጽ/ቤት) ድረገጽ፤ እንዲሁም የተለያዩ የሬዲዮና የቲቪ ማስታወቂያዎችን መጠቀሙን ገልጾዋል፡፡ (ኮሚሽኑ ያወጣው ባለሰባት ገጽ የክስ መረጃ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡)

ከሚያዚያ 2011 ጀምሮ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በተሸጠው የአባይ ቦንድ አማካኝነት የተሰበሰበው የገንዘብ መጠን ለምሳሌ ያህል ከዚህ የሚከተለው እንደነበር የክሱ ማመልከቻ በግልጽ ያስረዳል፡፡ (የገንዘብ መጠኑ በአሜሪካ ዶላር ነው)

ሃይለማርያም ደሳለኝ በዋሽንግተን ዲሲ ለአባይ ግድብ ቦንድ ተሸጦ የተሰበሰበውንና በመጪዎቹ 30 ቀናት ውስጥ የሚመለሰውን ሰኔ 2012 በተቀበሉበት ወቅት፤ (ፎቶ ምንጭ፡ tigraionline.com)
ሃይለማርያም ደሳለኝ በዋሽንግተን ዲሲ ለአባይ ግድብ ቦንድ ተሸጦ የተሰበሰበውንና በመጪዎቹ 30 ቀናት ውስጥ የሚመለሰውን ሰኔ 2012 በተቀበሉበት ወቅት፤ (ፎቶ ምንጭ፡ tigraionline.com)

ነሐሴ 2011፤ በዴንቨር ኮሎራዶ፤ $130,000.00
ሰኔ 2012፤ በዋሽንግተን ዲሲ፤ $1,500,000.00
ሰኔ 2012፤ በሺካጎ ኤሌኖይ፤ $110,000
ሚያዚያ 2013፤ ሳን ዲያጎ ካሊፎርኒያ፤ $43,000
ሚያዚያ 2013፤ ሒውስተን ቴክሳስ፤ $50,000
ግንቦት 2013፤ ኒው ዮርክ ከተማ ኒው ዮርክ፤ $100,000

ይህ እንደ አመላካች ሆኖ የተሠራ መዘርዝር የቦንዱ ሽያጭ በኤምባሲው ስፖንሰር አድራጊነት በሕዝባዊ አዳራሾች የተሰበሰበውን ለማሳየት የቀረበ ነው፡፡ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ትኩረት ያደረገው ሽያጭ በሬዲዮና በቲቪ እንዲሁም በኤምባሲውና በሌሎች መንገዶች መቅረቡን የክሱ ማስረጃ ያመለክታል፡፡

ቦንዱ የሚወልድበት ዓመት ከደረሰ በኋላ በየስድስት ወሩ ወለድ የሚከፈል መሆኑን ገዢዎች ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚያስገቡት የማስታወቂያ መመሪያ ላይ የተመለከተ ሲሆን ክፍያው በቀጥታ ወደ ባንክ ሒሳባቸው ወይም ባንክ ቤቱ ድረስ በመቅረብ መቀበል ከሚለው አንዱን በመምረጥ ከ3,100 (ሶስት ሺህ አንድ መቶ) በላይ የሚሆኑ በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ$5 እስከ $10,000 (ከአምስት እስከ አስር ሺህ ዶላር) ዋጋ ያለውን ቦንድ መግዛታቸውን የኮሚሽኑ የክስ መረጃ ያመለክታል፡፡ ከዚሁ ጋር አያይዞ እነዚሁ ገዢዎች ያወጡት አጠቃላይ ገንዘብ $5,800,000.00 (አምስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ ዶላር) እንደሆነና ከገዢዎቹ መካከል 64 በመቶው የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ያስረዳል፡፡

አገር በዘፈቀደ የሚመራው ህወሃት/ኢህአዴግ ይህንን ሕገወጥ ቦንድ ሉዓላዊነቷ በተከበረ አገር ላይ ሲሸጥ በአገር ውስጥ እንደሚያደርገው በአሜሪካም ማንአለብኝነቱን ለማሳየት መሞከሩ ድንበር ዘለል ሕገወጥነቱን እና ወራዳነቱን ያመለክታል የሚሉ ወገኖች ይህ እንደ አገር “አሳፋሪ” ነው ይላሉ፡፡ ቢያንስ “የተማሩ” የሚላቸው “ሚኒስትሮቹና ዴኤታዎቹ” እንዲሁም ከአምባሳደሩ ጀምሮ degree millበተዋረድ ያሉ የኤምባሲው ሹማምንት ይህንን አስቀድመው ለማስቆም ወይም ህጋዊ እንዲሆን ለማድረግ አለመቻላቸው “የዲግሪ ወፍጮቤት ምሩቃን” መሆናቸውን በገሃድ የሚመሰክር፤ ህወሃት/ኢህአዴግም እስካሁን በሕገ አራዊት የሚመራ ዋልጌ መሆኑን ያለተጨማሪ ማስረጃ ገሃድ ያወጣ ተግባር ነው በማለት እነዚሁ ወገኖች ምሬታቸውን ይናገራሉ፡፡

ኮሚሽኑ ባቀረበው ማመልከቻና ህወሃት በፍርድ ቤት ከመከሰሱ በፊት በተስማማው መሠረት የክሱ ትዕዛዝ ከወጣበት ሰኔ 1፤2008ዓም (June 8, 2016) ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ “የበላውኸውን ትፋ” ተብሏል፡፡ በዚህም መሠረት ህወሃት/ኢህአዴግ $6,448,854.87 (በዶላር ስድስት ሚሊዮን አራት መቶ አርባ አራት ሺህ ስምንት መቶ አምሳ አራት ከሰማኒያ ሰባት ሳንቲም) አንዳች ሳይቀንስ በኮሚሽኑ የባንክ ሂሳብ ውስጥ ገቢ እንዲያደርግ ታዝዟል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ህወሃት ከቀነ ገደቡ ቢያልፍ በኮሚሽኑ ሕገ ደንብ መሠረት ከነወለዱ እንዲከፍል የሚገደድ መሆኑን የክሱ ማስረጃ ጨምሮ ያብራራል፡፡ ይህ ከተጠናቀቀ በኋላ በሚቀርበው ማስረጃ መሠረት ቦንዱን የገዙ ግለሰቦች ገንዘባቸው (ተገቢም ከሆነ ከነወለዱ) እንዲመለስ የሚደረግበት ሂደት እንደሚቀጥል መረጃው ጨምሮ ያስረዳል፡፡ የሁኔታውን ግዝፈትና የሚያደርሰውን ኪሣራ ጫና የተመለከቱ ወገኖች “ህወሃት ሰኔና ሰኞ ሳያስበው ገጥመውበታል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡bond 2014

ውሳኔውን ያስቆጨው አይጋፎረም “ጽንፈኛው ዳያስፖራ (በዚህ ክስ) ያሸነፈ ሊመስለው ይችል ይሆናል፤ ነገርግን ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ነች” በማለት ድንቁርና በለገሰው ድፍረት የህወሃትን መንበርከክ እንደ ሽንፈትን አልቀበልም ብሏል፡፡ ከዚህም አልፎ በዚሁ ድንቁርና በመነዳት “አሁን በሕጋዊ መልኩ ኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ትሰበስባለች” በማለት ፍቅረ ህወሃት ህልሙን በኢትዮጵያ ስም በማስታወቅ ሰዎችን እንደገና ወደገደል የሚመራ ዕቅዱን ይፋ አድርጓል፡፡ አገሪቱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ቀውስ ውስጥ ባለችበትና የዱቤ ደብዳቤ (ኤል.ሲ.) ለመፍቀድ እጅግ በርካታ ወራትን ማስቆጠሩ ነጋዴውን ፍጹም እያስመረረና እያከሰረ ባለበት ሁኔታ ህወሃት ሰብስቦ የበላውን እንዲተፋ መገደዱ የሚያስከትለው የፋይናንስና የገንዘብ ኪሣራ አፍቃሪ ህወሃቶችን እምብዛም ያስጨነቀ አይመስልም፡፡ የጉዳቱን መጠን የሚያውቁት ግን የጠገገ ቁስሉን እንደገና ሲያደሙበት የጣዕር ሲቃ እንደሚያሰማ ስስ ብልታቸው ላይ መመታታቸውን የተረዱ ጩኸታቸው ከሩቅ ይሰማል፡፡

የዛሬ አምስት ዓመት የቦንዱ ሽያጭ ይፋ በሆነ ጊዜ በወቅቱ የንግድ ባንክ ማመልከቻዎችንና የቦንድ ግዢ መመሪያዎችን አባሪ በማድረግ በጉዳዩ ላይ ባለሙያ ለሆነ ጠበቃ የማስተላለፍ ሥራቸውን የሰሩ ይህ ዓይነቱ ጉዳይ ተጠናክሮ መቀጠል ቢችል ህወሃትን ያለብዙ ችግር ማንበርከክ የሚቻል እንደሆነ አስረግጠው ይናገራሉ፡፡ ቀላሉ መንገድ የዶላሩን መስመር መከተል ብቻ ነው፤ እዚያ መስመር ላይ ህወሃትን ማግኘት ብዙም አይከብድም በማለት ሰሚ ባያገኙም አሁንም ይመክራሉ፡፡ ክቡር ከሆነው የሰው ህይወት ይልቅ ገንዘብ አምላኩ የሆነው ህወሃት የአገርን ክብር ያዋረደውና ዜጎችን በእብሪት እየረገጠ ያለው በገንዘብ ኃይል ነው፡፡ በገንዘብ መከታ ዜጎችን ድሃ ያደርጋል፤ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ያፈርሳል፤ ታማኝ ተቃዋሚ ይመሠርታል፤ ያደኸየውን “ያጠግብና” ተገዢ ያደርጋል፤ ሕገወጥ ዳኞችን ይሾማል፤ ሕግ ያወጣል፤ ሕግን በፍትህ ስም ያረክሳል፤ ፍትህንም በሕግ አንቀጽ ያዋርዳል፤ እስከ ዓለምአቀፍ ቦታዎች ድረስ በገንዘብ ኃይል አሽቃባጮቹንና ተላላኪዎቹን ያስሾማል፤ …፡፡ ህወሃት ለጌቶቹ በገንዘብ የተገዛና አንዳች ክብር የሌለው ወራዳ ስለሆነ የገንዘብን ጥቅም ከማንም በላይ ያውቀዋል፡፡ ይህንን በውል የሚረዱ ወገኖች ደግሞ የህወሃትን የገንዘብ ምንጭ በተቻለው ሁሉ ለማድረቅ ሙከራው ቢቀጥል በገንዘብ ከገዛቸው ተራ ካድሬዎች ጀምሮ እርስበርስ መበላላት መጀመራቸው አይቀሬ ይሆናል ይላሉ፡፡

ከዝግጅት ክፍሉ፤ አገራችን እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ዓይነት በወንበዴ አስተሳሰብ የሚመራ ቡድን የምትገዛ ባትሆን ኖሮ ይህ ዜና ለፍጆታ መቅረብ የሚያስፈልገው አልነበረም፡፡ ይልቁንም እንደ አገርና እንደ ዜጋ ይህ የሁላችንም ገመና በመሆኑ ሁላችንንም የሚያሳፍር መሆን ይገባው ነበር፡፡ ከታላቅ አገራዊ ቁጭትና ጥልቅ ሃዘን ጋር ይህንን ዜና ለፍጆታ ማቅረባችንን አንባቢዎቻችን እንዲረዱልን እንፈልጋልን፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. gud says

    June 11, 2016 08:10 pm at 8:10 pm

    Do not get happy slaves !

    If bond is not legal , we will donate it !

    Reply
  2. tesfai habte says

    June 20, 2016 03:13 pm at 3:13 pm

    እኛ ኤርትራውያን የፈጠርነው ወያነ በያ መጥፋቱ መሆኑን መስተዋል ያስፈልጋል። እንደፈጠርነው መጥፋቱም ተቃርበዋል!

    Reply
  3. tesfai habte says

    June 20, 2016 03:13 pm at 3:13 pm

    እኛ ኤርትራውያን የፈጠርነው ወያነ በእኛ መጥፋቱ መሆኑን መስተዋል ያስፈልጋል። እንደፈጠርነው መጥፋቱም ተቃርበዋል!

    Reply
  4. gud says

    June 25, 2016 07:09 pm at 7:09 pm

    Oops Shabia is near death !

    Eretrian youth shall accept the country and live with peace with its neighbors!

    No toxic Ethiopian diaspora invited !

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule