ከቤተ ፋጌ እስከ እየሩሳሌም ማቴዎስ ም.፪፩፣ ፩-፩፯ ወደ እየሩሳሌም ወደ ቤተ ፋጌ ደርሰው ነበርና ደብረዘይት ግርጌ በዛን ጊዜ ጌታ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሎ አዘዘ ጠራና ሁለቱን ከዛ ከፊታችሁ ከምትገኝ መንደር አህያ ታስራለች ከውርጫዋ ጋር ሂዱ ቅደሙና አምጡልኝ ፈታችሁ ማንምደግሞበዚህ አንዳችም ቢላችሁ በሉና ንገሩት ጌታ አስፈልጎታል ይሄንን ሲሰማ ወዲያው ይሰዳታል። ፅዮን ሆይ ንጉስሽ ባህያ ጀርባ ላይ ይመጣለንዳለው አስቀድሞ ነብይ ደቀ መዛሙርቱም ሄደው አመጡለት እንዳዘዘው ሆነ እንዲፈጸም ትንቢት። ባህያ ተቀምጦ እየሱስም ሲደርስ ከህዝቡ ብዙዎቸያነጠፉ ልብስ ሌሎችም እንዲሁ ከዛፉ ጫፍ ጫፉን ቆርጠው በመጎዝጎዝ ሸፈኑት መንገዱን ቀድመው የደረሱ የተከተሉትም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና በአርያም የተባረከ ነው መጪ በጌታ ስም እያሉ በመጮህ … [Read more...] about ሆሳዕና
Literature
ጽፈኪን
ደስ ይበለን በዚህ ብስራት
አድዋ! በድልሽ የተገኘ ምስራች ጊዜው ረዘመ ብሎ ሳይሰለች ዕድሜው በዕድሜ ላይ እየጨመረ ጀግኖችን እንደገና እያነሳ እየደመረ ዛሬም በልጅ ልጅ ልጅ ልጅ ልጅ….ታሪክሽ ታውቀ የድል ብስራትሽ በዓለም ዓለም ዓለም ዓለም….አንጸባረቀ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ሻማ መሆንሽ ተወራ ሀገር ለሀገር ተሰማ ይሄው ተከበረ መቶ አስራ ስምንተኛ ዓመት ሁላችንም ደስ ይበለን በዚህ ብስራት የአበው ተጋድሎ የጀግንነት ደም ታሪኩ ተወሳ በከንቱ ፈሶ አልቀረም የአባ ዳኘው መድፍ አሁንም አገሳ መልሶ የጣይቱ ስም ተጠራ ተወደሰ አባ ነፍሶ እንደገና አስተጋባ የአድዋ ድል ገኖ ታየ ተደነቀ አባ መቻል ሀብተ ጊዮርጊስ አባ መላ ስራው በድጋሚ ጎላ። አድዋ! በድልሽ የተገኘ ምስራች ጊዜው ረዘመ ብሎ ሳይሰለች ዕድሜው በዕድሜ ላይ እየጨመረ ጀግኖችን … [Read more...] about ደስ ይበለን በዚህ ብስራት
የለም
እንትን የለም እንትን የለም በእንትን እጥረት ህይወት ማዝገም እንትና እንትን መጠቋቆም መደማደም ተስፋ ያጣ ተስፋችንን ግዜ ሰጠን እንደማከም እሱ እነሱ እንደዛ እያልን ለራስ ሚሆን ግዜ አጠረን ----- Zeynu Seid ----- ከAfendi Muteki ፌስቡክ የተገኘ … [Read more...] about የለም
“ሰዋስው ተማር”
አንድ የሰዋስው ተማሪ ውሃ ለመቅዳት ወደ ጉድጓድ ሄደ፡፡ ሆኖም በጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ ተንሸራተተና ከጉድጓዱ ውስጥ ተደፋ፡፡ እዚያም ሆኖ ዋይታውን ሲለቀው አንድ መንገደኛ ሰማውና ሊረዳው መጣ፡፡ “ምን ሆንክ?” “እንደምታየው ከዚህ ጉድጓድ ውስጥ ልሰጥም ነው፤ ቶሎ ገመድ አምጥተህ ካላወጣኸኝ መሞቴ ነው” “እሺ ገመድ ልፈልግና ልምጣ፤ እስከዚያው ግን የጉድጓዱን ዳር ይዘህ ለመንሳፈፍ ብትሞክር ይሻላል” መንገደኛው ይህንን ተናግሮ ሊሄድ ሲል ተማሪው አላስችል አለው፡፡ እናም “አንድ ጊዜ ቆየኝ እስቲ” በማለት መንገደኛውን ከመንገድ ጠራውና እንዲህ አለው፡፡ “ቅድም የተናገርከው ዐረፍተ ነገር የሰዋስው ደንብን የጠበቀ አይደለም፤ ስለዚህ ላስተካክልልህ ብዬ ነው የጠራሁህ”፡፡ መንገደኛው ይህንን ሲሰማ በጣም ተናደደ፡፡ ከጉድጓድ ውስጥ ለሚንቦጫረቀው ተማሪም እንዲህ አለው፡፡ “እንደዚያ … [Read more...] about “ሰዋስው ተማር”
እናቴ የእኔ እናት…
እኔ ልሙት አንቺ፣ አንቺ ትሞች እኔ፣ ሳያውቅብን ቀኑ፣ ሳናውቅበት ቀኑን፣ በቁም ያለን መስሎን፣ እናቴ እኔና አንቺ፣ ተለያይተን ቀረን። ሞትን መቀበር ነው፣ በጉድጓድ መከተት፣ ከምድር በታች መዋል፣ ብለህ አትናገር፣ ሌላ ሞትም አለ፣ አታውራ ዝም በል። በእኔና በእናቴ፣ በልጅና በእናት፣ ደርሷል ቆሞ መሞት፣ ቀኑ ወር ተክቷል፣ ወራት ብዙ ዓመታት፣ ሳታየኝ ሳላያት። አዎን! አለች አለሁ፣ አለን እንላለን፣ በስጋ ቆመናል፣ ነገር ግን ውሸት ነው፣ የለሁም የለችም፣ መለየት ገድሎናል። እንዴት ነው፣ ያለችው?፣ እንዴት ነው፣ ያለሁት? እሷ ልጄ እንዳለች፣ እኔ እናቴ እንዳልኳት፣ ተስፋችን ሞቶብን፣ ላታየኝ ላላያት፣ ቆመናል አልልም፣ የለሁም የለችም፣ እናቴ የእኔ እናት... … [Read more...] about እናቴ የእኔ እናት…
መርገምተ ወያኔ
“በረከተ መርገም” የሚያስፈልግ ቃሉ፣ ዛሬ ነው ተራገም ባለቅኔው ኃይሉ። ቅኔህን አፍሰው እንደድሮ እንደጥንት፣ ላሁን ዘመን ገዢ ያስፈልጋል መርገምት። አንተ በርግማንህ የጠበጠብካቸው እነዛ ሊቃውንት በፍልስፍናቸው ተወቃሽ በመሆን ቢያተርፉም ክፉ ስም ለውጥ አስገኝተዋል ላለንባት ዓለም ነገር ግን ያሁኑ ለስልጣን ለሀብቱ፣ ለስጋ ቁመናው ለሰፊው ቀፈቱ፣ አስሮ ሲያንገላታ ቆይቷል ሲገድል፣ አፍስበት በሱም ከርግማንህ ጠበል፣ ድሮ በሊቆቹ እርግማን ከጨረስክ፣ ምን ይሰራል ብለህ ወይም መርገም ከተውክ፣ እንዳሻህ በልና ፍቀድልኝ፣ ለኔ የርግማን በረከት አለኝ በወያኔ ካስፈለገም አምጣ ድርሻህን መዋጮ፣ የእኔን ግን ልጀምር ከወያኔው ቁንጮ ከኢትዮጵያ ምድር ከአብራኳ ወጥተህ፣ አንባሻዋን ገምጠህ ወተቷን ጠጥተህ፣ ፊደል ቆጥረህባት በሜዳዋ ሮጠህ፣ በፍቅር በደስታ … [Read more...] about መርገምተ ወያኔ
እኔና አንቺ… ፫
በሕዝብ ተጋርደን ባ’ገር ተከልለን ለካስ እኔና አንቺ ብዙም ዕውቀት የለን። እኔን ስመረምር አንቺን እዚህ ሳይሽ እኔም ያን አይደለሁ አንቺም ያቺ አይደለሽ። እንዲህ ካደረገን ስደት አሸንፎ ጭራሽ ከሚለየን ኑሮአችንን ገፎ ሠርግ ባንደግስም ባይረጭ አበባ በአዲስ ትውውቅ ድጋሚ እንጋባ። ****************** እኔና አንቺ … ፩ - ፖለቲካና ስደት እኔና አንቺ…፪ - ሀገርና ክህደት … [Read more...] about እኔና አንቺ… ፫
ዝምታው በዛ
አገር ሲቆረስ ድንበሩ ሲፈርስ ማንነት ታሪክ ሲሻር መሬት ሲገመስ አገር ያለ ባህር በር ስትቀር ዜጋ ማንነት በጎሳ ሲቀየር ድንበር ተቆርሶ ለባድ ሲለገስ ወገን ሲጨቆን መኖሪያ ቤቱ ሲፈርስ ሀብት ንብረቱ ተዘርፎ ከቀየው ቦታው ሲሰደድ ዜግነት ክብሩ ሲጣስ ሰብአናው ሲዋረድ በአረብ ምድር ሲገደል አንደ አንስሳ ሲታረድ ህይወት ሲቀጠፍ ሲታነቅ በገመድ ዜግነት ክብሩ ሲዋረድ ሰአብዊ መብቱ ሲናድ የመኖር ህልሙ ባዶ ሲሆን ፊቱ በአንባ ሲታጠብ ሲዋጥ በሀዘን ለስቃይ ችግር ሲዳረግ በረሀብ አለንጋ ሲገረፍ ጠኔ ሲመታው በከባድ ህመም ሕይወት ሲቀጠፍ ሀገር ወገን ሲጣራ ሰሚ ሲያጣ ሲያለቅስ መንግስት ጆሮ ሲደፈን አልሰማ ሲል ሲሆን ደንታቢስ አስከመቼ ነው ዝምታው ላገር ለወገን መድረሻው የብሶት የችግር ማብቂያው ተነሳ ወገን ህብረት አንድነት አጠንክር ጨካኝ ወያኔን … [Read more...] about ዝምታው በዛ
ለስምህ ስም ሁነው
ከሚለጥፍብህ ከአፉ እንደመጣ ሚሻለውን መርጠህ ለራስህ ስም አውጣ ሺ ጨዋ ብትሆን ሚልዮን ጥንቁቅ ሰው ሰው በሰውነትህ የሚልህ ስላለው በችሎታህ መጠን ኪሎህን መዝነህ ጭማሪ መጠሪያ ስም ስጠው ለራስህ ሚጠራህ ከጠፋ አንተ ባወጣኸው በተግባር ታይና ለስምህ ስም ሁነው። … [Read more...] about ለስምህ ስም ሁነው
ትዝታ በ60/በስድሳ
ወደ ኋላ ሄዶ አበባ ሲፈካ፣ ጊዜ ሲተካካ፣ ልጅ ስልጣኔ መጥቶ በራችን ሲያንኳዋካ፤ ከባህል ጥል ገጥሞ ለመኖር ለብቻው፣ ማየት ማስተዋል ነው፣ ኧረ የሰላም ያለህ ተው አይሆንም ሲለው ባህል ሲማጠነው ደባል እንዲሆነው፤ (ቀሪውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ትዝታ በ60/በስድሳ