ከቤተ ፋጌ እስከ እየሩሳሌም
ማቴዎስ ም.፪፩፣ ፩-፩፯
ወደ እየሩሳሌም ወደ ቤተ ፋጌ
ደርሰው ነበርና ደብረዘይት ግርጌ
በዛን ጊዜ ጌታ ደቀ መዛሙርቱን
እንዲህ ብሎ አዘዘ ጠራና ሁለቱን
ከዛ ከፊታችሁ ከምትገኝ መንደር
አህያ ታስራለች ከውርጫዋ ጋር
ሂዱ ቅደሙና አምጡልኝ ፈታችሁ
ማንምደግሞበዚህ አንዳችም ቢላችሁ
በሉና ንገሩት ጌታ አስፈልጎታል
ይሄንን ሲሰማ ወዲያው ይሰዳታል።
ፅዮን ሆይ ንጉስሽ ባህያ ጀርባ ላይ
ይመጣለንዳለው አስቀድሞ ነብይ
ደቀ መዛሙርቱም ሄደው አመጡለት
እንዳዘዘው ሆነ እንዲፈጸም ትንቢት።
ባህያ ተቀምጦ እየሱስም ሲደርስ
ከህዝቡ ብዙዎቸያነጠፉ ልብስ
ሌሎችም እንዲሁ ከዛፉ ጫፍ ጫፉን
ቆርጠው በመጎዝጎዝ ሸፈኑት መንገዱን
ቀድመው የደረሱ የተከተሉትም
ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ሆሳዕና በአርያም
የተባረከ ነው መጪ በጌታ ስም
እያሉ በመጮህ ይናገሩ ነበር
አንድ ላይ በመሆን ካሉት በዛ መንደር።
እየሩሳሌምም ገብቶ እንደረገጠ
ማነውይሄ እያለ አገር ተናወጠ
የመጣ ነው አሉ ገገሊላ ናዝሪት
እየሱስ የሚባል ነብይ ነው አሉት
ሁሉን አወጣና ገባና ከመቅደስ
ገዥንም ሻጭንም ተቆጥቶ እየሱስ
እንዲሁም አየና ገንዘብ እሚለውጡ
ወንበርም ዘርግተው እርግብ የሚሸጡ
መሆኑ ተጽፎ ቤቴ የጸሎት ቤት
የወንበዴ ጎሬ ዋሻ አረጋችሁት
አሁንም ጸሎት ቤት ይባላል አላአቸው
ወንበሮቹን ጣለ ገለባበጣቸው።
እውሮች አንካሶች ነበሩና መቅደስ
ወደሱ ቀረቡ አረገላቸው ፈውስ
የካህን አለቆች ይሄንን አዩና
ደግሞም ለዳዊት ልጅ ሲባል ሆሳዕና
ድንቅ ድንቅ ስራው አስቆጣቸውና።
ህዝቡ የሚለውን አትሰማምወይ ሲሉት
ከህጻኖቹ አፍ ደግሞም ከሚጠቡት
ምስጋና አዘጋጀህ ለራስህ የሚሆን
የሚል ቃል እንዳለ በቅድሚያ መጻፉን
እንዴት አታነቡም ብሎ በመናገር
ቢታንያ አደረ ወጣና ከዛ አገር።
Leave a Reply