እኔ ምን አገባኝ እኔ ምን አገባኝ የምትሉት ሐረግ እሱ ነው ሀገሬን ያረዳት እንደ በግ የሚል ግጥም ልጽፍ ስሜት አንዘርዝሮኝ ብድግ አልኩኝና ምን አገባኝ ብየ ቁጭ አልኩ እንደገና:: ግጥሙ የተወሰደው ከኑረዲን ዒሳ ፌስቡክ ነው:: ባለፈው ሌባዬ በሚል ርዕስ ላወጣነው የግጥም ጨዋታ የተሳተፋችሁትን ሁሉ በተለይ ደግሞ Tsinat ፣ Gedion Adenew እና አበበ አዲስ ከልብ እናመሰግናለን:: እስቲ ለዚህኛውም አንድ ሁለት ሁላችንም እንበል!! እንደበፊቱ ሁሉ ምላሹ በግጥም ቢሆን ጨዋታዋን ሞቅ ያደርገዋል:: … [Read more...] about እኔ ምን አገባኝ?
Literature
ጽፈኪን
ወግድልኝ ወዲያ!
አሥራደው (ከፈረንሳይ) ሲጭኑህ አጋሰስ፤ ሲጋልቡህ ፈረስ፤ ጠምደው ሲያርሱህ በሬ _ _ _ ስትታለብ ጥገት፤ በቁም ሲያርዱህ ሙክት፤ ሲጣልልህ ውሻ - የጅ ዕባሽ ናፋቂ፤ እዳሪ ለሆዱ - ክብሩን አስነጣቂ፤ ጫንቃህ የደለበ - ለመሸከም ቀንበር፤ እንቢኝን የማታውቅ - ከእሽታ በቀር፤ እንዳህያ ጭነት - ሸክም ያስለመዱህ፤ ሲገፉት ነፃነት - የማይበርደው ገላህ፤ አጎንባሽ ለመጣው - የሞትክ ነህ በቁም፤ ወግድልኝ ወዲያ ጭራሽ አላውቅህም! እንዳንተ ያለውን አገሬ አትናፍቅም:: የአያት የቅድም አያት - ጀግንነቱ ቀርቶ፤ ሽለላ፤ ፉከራው - ዕምቢልታ ቀረርቶ፤ በጦር ደረት መብሳት - በጋሻ መክቶ፤ አሻፈረኝ ማለት - ለበደል ለጥቃት፤ በጀግንነት መሞት - ላገር ለነፃነት፤ መሆኑ ቀረና፤ የጀግና ልጅ ጀግና፤ ሰብዕናህ ተገፎ - ዝቅ ብለህ ወደታች፤ ባይተዋር ያገሩ - … [Read more...] about ወግድልኝ ወዲያ!
ሌባዬ. . .
ሌባዬ. . . ድምጹ ሳይሰማ ኮቴውን አጠፍቶ በጠራራ ፀሐይ የደጄን በር ከፍቶ መዝለቅ የጀመረው ክርችም በሬን ከፍቶ ምን ሊዘርፈኝ ይሆን በምኔ ጎምጅቶ? በማለት ኖላዊት ሽመልስ ስትጠይቅ የሚከተሉት መልሶች ተሰጥተዋታል፡፡ (ምልልሱን ያገኘነው ከፌስቡከ ሲሆን እርስዎም የሃሳብ በመስጫውን በመጠቀም ምላሽዎን እንዲሰጡ እንጋብዝዎታለን፡፡) ************************************************************************************* ጠንቀቅ አለሽ ንብረት አለሽ አንቺዬ ሃብት አለሽ ገንዘብ የማይገዛው ለራስሽ ያልታየሽ እጅግ የበለጠ ከወርቅ፤ አልማዝ፤ ከእንቁ አድፍጦ ሊዘርፍሽ ያመጣው ከሩቁ እመኚኝ ሃብት አለሽ ዘብ የሚያስፈልገው ብቻ ችላ ብለሽ እንዳታሰርቂው፡፡ (ብሌን … [Read more...] about ሌባዬ. . .
የኔ ውብ ከተማ
የኔ ውብ ከተማ ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር? የኔ ውብ ከተማ ሕንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር የኔ ውብ ከተማ መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡ ሕንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ? የሰውን ልብ ነው፡፡ ምን ቢነድ ከተማው ተንቦግቡጎ ቢጦፍ ቢሞላ መንገዱ በሺ ብርሃን ኩሬ በሺ ብርሃን ጎርፍ ምን ያደርጋል? ምን ያሳያል? ካለሰው ልብ ብርሃን ያ ዘላለማዊ ነበልባል ያ ተስፋ ሻማ ጨለማ ነው ሁሉም ጨለማ፡፡ በዓሉ ግርማ … [Read more...] about የኔ ውብ ከተማ