ተወዳጁ ገጣሚና ባለቅኔ ጋሽ አሰፋ ገ/ማርያም ረቡዕ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓም (October 17,2012) የታላቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲ የክቡር አቶ ሃዲስ አለማየሁ (ዶ/ር) 103ኛ ቀነ-ልደት (BIRTHDAY) በማስመልከት የጻፉትን ግጥም ልከውልናል፡፡ ግጥሙ ዘመን የማይሽረው በመሆኑ በዚህ ወቅት በድጋሚ አውጥተነዋል (በፎቶ የተከሸነውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) በተጨማሪ በአንድ ወቅት የተቀኙላቸውን በቃላቸው የሚስታውሱትን የአማርኛ መወድስ ቅኔ መርቀውልናል፡፡ ጋሽ አሰፋን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ መወድሱ እንዲህ ይነበባል፡-
መውደድ ካልቀረ ማፍቀር፤
ወገንና ሃገር፤
እንደ ደራሲው አዲስ ነገር፤
ፍቅር !…እስከ መቃብር!
በመጨረሻም “ለወጣቱ ትውልድ መልካም አርአያ የሚሆን ኢትዮጵያዊ እምብዛም በሌለበት በዚህ ጉደኛ ዘመን እንደነ ሃዲስ አለማየሁ የመሳሰሉትንና በየወቅቱ ለኢትዮጵያ ነፃነትና አንድነት የተሰዉትን ጀግኖቻችን ማስታወስና ለወጣቱ ትውልድ ማስተላለፍ የዜግነት፤ የኢትዮጵያዊነትና የሞራል ግዴታ ይመስለኛል” በማለት ጋሽ አሰፋ ገ/ማርያም መልዕክታቸውን በማስተላለፍ መልካም ቀነ-ልደት ተመኝተዋል፡፡
(ፎቶ: Addis Journal)
dawit says
ሕ – ያውነት
በጉደኛው ዘመን – ውል በረከሰበት
አዲስን ማስታወስ – ዘመንን መቃኘት
አቤት ዘመን – አቤት ጊዜ
የኛ ዘመን – የ – ዚያ ጊዜ
ስንመዘን – በዘመን ልክ
እኛ ሞተን – አዲስ ባበብክ፤
ሕያውነት ይሏል
እንዲህ ይዘከራል፤
koster says
It is very unfortunate that great Ethiopians like Haddis Alemayehu, Professer Asrat Woldeyes, Dr. Dagnatchew Yirgou etc are now replaced by fascists like Meles Zenawi, Sebhat Nega and hodams like Addisu Legesse, Bereket Simeon etc, etc……………..
Alem says
So you think only Amharas are “great Ethiopians?” I am just referring to the persons you listed.