ተወዳጁ ገጣሚና ባለቅኔ ጋሽ አሰፋ ገ/ማርያም ረቡዕ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓም (October 17,2012) የታላቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲ የክቡር አቶ ሃዲስ አለማየሁ (ዶ/ር) 103ኛ ቀነ-ልደት (BIRTHDAY) በማስመልከት የጻፉትን ግጥም ልከውልናል፡፡ ግጥሙ ዘመን የማይሽረው በመሆኑ በዚህ ወቅት በድጋሚ አውጥተነዋል (በፎቶ የተከሸነውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) በተጨማሪ በአንድ ወቅት የተቀኙላቸውን በቃላቸው የሚስታውሱትን የአማርኛ መወድስ ቅኔ መርቀውልናል፡፡ ጋሽ አሰፋን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ መወድሱ እንዲህ ይነበባል፡- መውደድ ካልቀረ ማፍቀር፤ ወገንና ሃገር፤ እንደ ደራሲው አዲስ ነገር፤ ፍቅር !...እስከ መቃብር! በመጨረሻም “ለወጣቱ ትውልድ መልካም አርአያ የሚሆን ኢትዮጵያዊ እምብዛም በሌለበት በዚህ ጉደኛ ዘመን እንደነ ሃዲስ አለማየሁ የመሳሰሉትንና በየወቅቱ … [Read more...] about ዓዲስ ሰው