• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወግድልኝ ወዲያ!

October 11, 2012 11:00 am by Editor Leave a Comment

አሥራደው (ከፈረንሳይ)

ሲጭኑህ አጋሰስ፤
ሲጋልቡህ ፈረስ፤
ጠምደው ሲያርሱህ በሬ _ _ _
ስትታለብ ጥገት፤
በቁም ሲያርዱህ ሙክት፤
ሲጣልልህ ውሻ – የጅ ዕባሽ ናፋቂ፤
እዳሪ ለሆዱ – ክብሩን አስነጣቂ፤
ጫንቃህ የደለበ – ለመሸከም ቀንበር፤
እንቢኝን የማታውቅ – ከእሽታ በቀር፤
እንዳህያ ጭነት – ሸክም ያስለመዱህ፤
ሲገፉት ነፃነት – የማይበርደው ገላህ፤
አጎንባሽ ለመጣው – የሞትክ ነህ በቁም፤
ወግድልኝ ወዲያ ጭራሽ አላውቅህም!
እንዳንተ ያለውን አገሬ አትናፍቅም::

የአያት የቅድም አያት – ጀግንነቱ ቀርቶ፤
ሽለላ፤ ፉከራው – ዕምቢልታ ቀረርቶ፤
በጦር ደረት መብሳት – በጋሻ መክቶ፤
አሻፈረኝ ማለት – ለበደል ለጥቃት፤
በጀግንነት መሞት – ላገር ለነፃነት፤
መሆኑ ቀረና፤
የጀግና ልጅ ጀግና፤
ሰብዕናህ ተገፎ – ዝቅ ብለህ ወደታች፤
ባይተዋር ያገሩ – የበይ ተመልካች፤
ውሎ ጦም አዳሪ – የሃብቱ ተመጽዋች፤
እራስክን ዝቅ አርገህ – ክብርህን ያዋረድክ፤
የት ቦታ ተዘርህ አገሬ ላይ በቀልክ?!
ወግድልኝ ወዲያ ጭራሽ አላውቅህም!
ለወለደህ ዕዳ ላገርህ ነህ ሸክም፡፡

ንቀት ብርድልብስህ፤
ውርደት ሆኖ አንሶላህ፤
ነፃነት ሲገፉህ – ዝም ብለህ የተኛህ፤
ጭቆና ተስማምቶ – የማይቆረቁርህ፤
በደል የተመቸህ – ጥላቻ እማይገባህ፤
ዕንቢኝን የማታውቅ – እሺን ያስለመዱህ፤
ኧረ ለመሆኑ ከወዴት ተገኘህ ?!
የቱ አባት አግኝቷት – ከምን ጉድ ጸነሰች፤
የቷ እናት አምጣ – ከቶ አንተን ወለደች?!
እንዳንተ ያለውን ወልዳ ከምታፍር፤
ምንኛ ደስ ባላት – ጨንግፈህ ብትቀር?!
አላውቅህም ጭራሽ ወግድልኝ ወዲያ!
እንዳንተ ያለውን አትሻም ኢትዮጵያ !!

መስከረም 4 ቀን 2005 ዓ.ም ( September 14/2012)

Filed Under: Literature

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ከታክስ ስወራ እስከ ሐሰተኛ ጋብቻ፦ በኢትዮጵያ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊ ዳያስፖራዎችን ለማደን የተዘረጋው አዲሱ የአሜሪካ መረብ October 21, 2026 09:26 am
  • ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ October 20, 2026 03:20 pm
  • ትውልደ ሶማሊያዊቷ ናፊሳ በተዘቀዘቀ የአሜሪካ ሠንደቅ ፊት በሶማሊኛ ምርጫ ቅስቀሳ ማድረጓ ቁጣ ቀሰቀሰ October 20, 2026 09:21 am
  • በአሜሪካ የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ደጋፊዎች ላይ የተደቀነው አዲስ ስጋት October 19, 2026 08:58 pm
  • ዜግነት ሊያሰርዝ በሚችለው የኢልሃን ዑመር ምርመራ ላይ አዳዲስ መረጃ ተገኝቷል October 19, 2026 04:45 pm
  • በትግራይ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ስም በአስቸኳይ ሊቀየር ይገባል! October 19, 2026 02:55 am
  • በትግራይ ሕዝብ ደም የሚደረገው የሥልጣን ቁማር ያብቃ! October 14, 2026 11:04 pm
  • የኒዳል ሀሰን በርሸና የሞት ፍርድ ሲፈጸምበት በቀጥታ ሥርጭት እንዲተላለፍ መወሰኑ ውዝግብ አስነሳ October 9, 2026 12:33 pm
  • ሴቶችን በመሾም ኢትዮጵያ በእርግጥ ተወዳዳሪ የሌላት ነች?  October 8, 2026 11:20 pm
  • Ethiopian Defense Forces Capture Advanced TPLF Military Drones and Documents Linked to Sudan October 7, 2026 12:40 pm
  • በሱዳን በኩል ለትህነግ የተላኩ የM6 ድሮኖችና ወታደራዊ መሣሪያዎች በመከላከያ እጅ መግባታቸው ተገለጸ October 7, 2026 11:20 am
  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
Copyright © 2026 · Goolgule