ቢሄዱት... ቢሄዱት... ቢሄዱት... ቢሄዱት... አያልቅ ሽቅቦሹ፥ አይቆም ቆልቁሎሹ መንገድ እየሄዱ መንገድ እየበሉ መንገዱ እየጠጡ አያልቅም ቢሄዱት፥ አያልቅም ቢጠግቡት፤ አወይ አማሪካን... አወይ የሰው አገር የበላን ያላየ፥ የዋጠን ያልሰማ አወይ አማሪካን፥ ሰው በላብ ያደማ፤ ቢሄዱት ቢሄዱት፥ እረፍትን ማን አውቆት እዚማ ከሆኑ… እንቅልፍ ለምኔን፥ ለብሶ ነዪ መኛት፤ አወይ አማሪካን፥ አገረ ማራቶን አገረ እሩጫ ለማምለጥ መፏደድ፥ ቢል ከሚሉ ጡጫ መኖር አለመኖር፥ ካንድ ራስ ፍጥጫ፤ አወይ አማሪካን... ቢሄዱት... ቢሄዱት... ቢሄዱት አያልቅ መንገድ እንደ ጅማት የሚላግበት አወይ አማሪካን ሕልም ያጠጠበት እንቅልፍ ለምኔን የሚያነቡበት_ እንቅልፍ ለምኔን የሚገምጡበት_ እንቅልፍ … [Read more...] about አወይ አማሪካን …
Literature
ጽፈኪን
ይላችኋል እስክንድር!!
ይላችኋል እስክንድር !!!! ---------------------------------- “በሚመች ሰፊ አልጋ ላይ ከሚስቶቻችሁ ጎን ብትሆኑም እንደኔ ተመችቷችሁ የሰላም እንቅልፍ አታገኙም” ይላችኋል እስክንድር ቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ ስትባንኑ ለምትኖሩት በቁም ለሞታችሁት አዝኖ ሰብእናችሁ ተሟጦ አውሬነታችሁ ቢታየውም ተፈጥሮ ሳይሆን ተመክሮ እንደሰጣችሁ አላጣውም ከሽፍታ ፍትሕ መጠበቅ ሞኝነት እንዳይመስላችሁ ለሁሉም ጊዜ ስላለው ለቅሶ ይሆናል ሳቃችሁ እና “እኔ እንደሆንኩ በዕምነቴ እንደፀናሁ በአገሬ እንደኮራሁ … ለዘላለም እኖራለሁ ምግባራችሁ ለቆሸሸው ስማችሁ ለተበላሸው እራሳችሁን ላሳነሳችሁት ግን … እስከወዲያኛው … [Read more...] about ይላችኋል እስክንድር!!
የሙት ምላስ
(ግጥሙ በPDF እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የሙት ምላስ
ቀይ-ሽብር ሲጀምር
ቀይ-ሽብር ሲጀምር ከደርግ ዲሞክራሲ ከወያኔ እኩልነት......ከሰማይ ዳቦ ስንጠብቅ ሰብዕናችን ተፍቆ ማንነታችን ተንቆ.....ከዕምነታችን ስንርቅ ውርደታችንን ተመልክተን፤ በቃ ማለት ካቃተን ታስሮ መታረድ አይቀርም እንደ በግ ተጎትተን ----------------- ዘመናት አስቆጥራ ብዙ ትውልድ ተሻግራ መቃብር ዛፍ ሲያበቅል፤ የብሶቱ ቀን ሲርቅ የደም አሻራ ሲጠፋ፤ የወላጅ እምባ ሲደርቅ ያኔ ይመስለኝ ነበር ታሪክ እራሷን የምትደግም ሕብረተ-ሰቡ ሲዘናጋ፤ ሰው ከሐዘኑ ሲያገግም ለካ ተሳስቻለሁ! መፃፍ፤ መናገር ሲከለከል: ማሰር፤ ማሳደድ ሲጀመሩ የሐሰት ዶኩሜንታሪ በቴሊቪዥን ሲሠሩ በጋዜጣ ሲያስፈራሩ፤ … [Read more...] about ቀይ-ሽብር ሲጀምር
ቀባሪ ያጣው የወያኔ/ኢህአዴግ የአገዛዝ ስረአትና ባለቤት የሌላት ኢትዮጵያ
እንደ ወያኔ/ኢህአዴግዊ ሀገርንና ትውልድን የሚያጠፋ እኩይ አመለካከትና ምግባር ይዞ ተነስቶና ተሳክቶለትም የሚገዛ ከኢትዮጵያ ውጭ በአለም ላይ ያለ ሀገርም ሆነ የሚገዛ ህዝብ የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግ የገዛ ወገኑንና ሀገሩን በጠላትነት ፈርጆ፣ ታጥቆና ተደራጅቶ የሚወጋና የሚያፈራርስ የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግዊ አገዛዝም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊንን የማጥፋቱንና የመበታተኑን ምግባር እንዲያቆም እሽሩሩ የተባለና እየተለመነ ያለ የለም።..... በልመና ቢሆን..... ፍትህ - እኩልነት በልመና ቢሆን... ነጻነት - አንድነት በልመና ቢሆን.... ሰላምና ሕይወት፤ እመጣ ነበረ- አንች ካለሽበት ትመጭልኝ ነበር - እኔ ካለሁበት ዓለም ይሆን ነበር፣ የሁላችንም ቤት። እንደ ደርግ ያለ አምባገነን መንግስት ሀገሩን በክህደትና በጥላቻ ለተሞሉ፤ እንደ ሻአቢያዊንና እንደ … [Read more...] about ቀባሪ ያጣው የወያኔ/ኢህአዴግ የአገዛዝ ስረአትና ባለቤት የሌላት ኢትዮጵያ
እንደ ሻማ
አንደ ሻማ ነው ማንባት፣ ቀልጦ ጠብ እንደሚለው፤ የነፍሳችንን ስቃይ፣ ይሉኝታ ሳይጋርደው፤ ማስመሰል ሳያርቀው፡፡ እንደ ሻማ ነው መቅለጥ፣ በነበልባል ነዶ በግኖ፤ ሰብእናን በህይወት ጣር፣ ሰርቶ በማደር ፈትኖ፡፡ እንደ ሻማ ነው መብራት፣ ማለቅም እንደ ሻማ፤ ለሌላም ባይሆን ለነፍስ፣ አብርቶ የእውነትን ፋና፡፡ በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር) ፣ /ፍካት ናፋቂዎች፤1999ዓ.ም/ ባለፈው ሁለት ግጥሞችን አቅርበን ነበር፡፡ “ቅኔ” እና “የማይጠፋ ፍቅር” በሚል ርዕሶች ለቀረቡት ግጥሞች ጨዋታውን በማድመቅ የተቀኛችሁትን እና ማብራሪያም የሰጣችሁትን ተሳታፊዎቻችንን በለው፤ YeKanadaw Kebede፤ አሥረዳው፤ እስከመቼ እና ዱባለ ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ ለዛሬው ደግሞ በግጥም ልተንፍሥ ከተባለ የፌስቡክ ገጽ ይህንን ግጥም አግኝተን ለጨዋታ አቅርበነዋል፡፡ “እንደ … [Read more...] about እንደ ሻማ
ለቅሶ ሳቅ – ሳቅ ለቅሶ
አቅቶን መለወጥ ለቅሶን በደስታ፤ ሃዘን ጠል አልብሶን ሳቅ ደርቦ ኩታ፤ ያንዱን ቤት ገንብቶ የሌላውን ሲያፈርስ፤ አንዱን ሳቅ አጅቦት ሌላው ከፍቶት ሲያለቅስ፤ ለቅሶ ሳቅ - ሳቅ ለቅሶ - እየደባለቀ፤ ግማሽ ጎኑ ሲያለቅስ - ግማሽ ጎኑ ሳቀ:: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለቅሶ ሳቅ – ሳቅ ለቅሶ
የማይጠፋ ፍቅር
ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድናችን በደቡብ አፍሪካ ያስመዘገበው ውጤት እስካሁን የብዙዎች መነጋገሪያ ዋና ሃሳብ ሆኗል፡፡ በተለይ ከእግር ኳሱ ጋር የታየው ወዳጅነት፤ አብሮነትና ተደጋጋፊነት ፖለቲከኞቻችንን “እንዴት ነገሩ፤ ካልሆነ … ብትሞክሩትስ?” የሚያስብል ሆኗል ቢባል የተጋነነ አይሆንም፡፡ ለዛሬ የግጥም ጨዋታ ይህንኑ መንፈስ የሚያንጸባርቅ ወቅታዊ ጨዋታ እንደሚሆን በማሰብ ከድንቅዬ ገጣሚዎቻችን መካከል ብሌን ከበደ በፌስቡክ ላይ የለቀቀችውን ከታላቅ ምስጋና ጋር እነሆ ብለናል፡፡ ባለፈው “የጠቆሩ ልቦች” በሚል ላቀረብነው ጨዋታ ድንቅዬ ችሎታችሁን በግጥም በመመለስ ጨዋታውን ላስዋባችሁት በለው፣ Alelign፣ Yekanadaw kebede፣ ዱባለና inkopa እጅግ የከበረ ምስጋናችንን እናቀርብላችኋለን፡፡ ክብረት ይስጥልን፡፡ … [Read more...] about የማይጠፋ ፍቅር
ቅኔ
የዘወትር የድረገጽ ጋዜጣችን ተሳታፊ የሆኑት ወዳጃችን ዱባለ፤ አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ያባታቸውን የኪነት ስራ አስባስበው ካሳተሙት መጽሕፍ ያገኘሁት የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ቅኔ ነው ብለው ገጣሚ ከሆነ ምስል ጋር የላኩልንን ግጥም ነው፡፡ እንዲህ ይነበባል፡- ጎድን ከዳቢት ስብራዳ ይገባ ነበር ለእንግዳ አያችሁት ወይ ይህን ቀን ታላቅ ታናሽ ሲሆን? … [Read more...] about ቅኔ
ቆረቆረኝ መቃብራችሁ
በየከተማው በየገጠሩ በየጥሻው በየቆንጥሩ በለጋ ሕይወታችሁ ገና ፀሐይ ሳትመታችሁ፤ “ነፃነት ነፃነት የምትሹ ተዋጉለት አትሸሹ።” እያላችሁ ቆማችሁ፤ አባራሪ ግንባር ሆናችሁ ቀንዲል ብርሃን ተነስታችሁ፤ ፀሐይዋ በዕርጋታ በሀገራችን ወጥታ ገብታ፤ ጨለማው ፈርቶ ሸሽቶ ብርሃን ባገር ሞልቶ የማይታሰበውና ደረቁ ሀቅ በውጥረትና በጭንቅ ሴትና ወንድ ወጣቶች ሕፃናትና ሽማግሎች፤ የመኖር ሕይወት ትርጉሙን ለሌሎች ሕይወት መቆምን አስተምራችሁን ያለፋችሁ ቆረቆረኝ መቃብራችሁ። እሁድ ጥር ፲፪ ቀን ፳፻፭ ዓመተ ምህረት (ስዕል: የገጣሚው) … [Read more...] about ቆረቆረኝ መቃብራችሁ