ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድናችን በደቡብ አፍሪካ ያስመዘገበው ውጤት እስካሁን የብዙዎች መነጋገሪያ ዋና ሃሳብ ሆኗል፡፡ በተለይ ከእግር ኳሱ ጋር የታየው ወዳጅነት፤ አብሮነትና ተደጋጋፊነት ፖለቲከኞቻችንን “እንዴት ነገሩ፤ ካልሆነ … ብትሞክሩትስ?” የሚያስብል ሆኗል ቢባል የተጋነነ አይሆንም፡፡
ለዛሬ የግጥም ጨዋታ ይህንኑ መንፈስ የሚያንጸባርቅ ወቅታዊ ጨዋታ እንደሚሆን በማሰብ ከድንቅዬ ገጣሚዎቻችን መካከል ብሌን ከበደ በፌስቡክ ላይ የለቀቀችውን ከታላቅ ምስጋና ጋር እነሆ ብለናል፡፡
ባለፈው “የጠቆሩ ልቦች” በሚል ላቀረብነው ጨዋታ ድንቅዬ ችሎታችሁን በግጥም በመመለስ ጨዋታውን ላስዋባችሁት በለው፣ Alelign፣ Yekanadaw kebede፣ ዱባለና inkopa እጅግ የከበረ ምስጋናችንን እናቀርብላችኋለን፡፡ ክብረት ይስጥልን፡፡
በለው ! says
፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤ ፤
ትውልድ የማይረሳው የማይጠፋ ፍቅር….!
ጠፋ..ጥፋ ቢሉት እንቢኝ ያለ የሚናገር
አፉ ተለጉሞ ዓይኑ እንኳ ቢታሠር
እያፈላለገ ፍቅር መጣ በግር …
ለምን? እንዴት?ብሎ ከፀብ ሊከራከር
ድምቅ ካለው ቤቱ በሩን ከፍቶት ሄዶ
ወራሽ አዘዘበት መጥቶ ከባህር ማዶ
የገባው ተቆጣ ተቆጨ እያለ ወይ ነዶ!
መለየቱ ለምን ? ተዋዶ ተዋልዶ
አንድነት ይከበር ከፋፋይ ተዋርዶ!
እንኳን ሞት አልሆነ የከፋ ከሁሉ
ያልሞተ ይገናኛል አብረው ሜዳ ዋሉ
የሰሜን ሀገር ሠው ደስታ አለው ለጎሉ !
በእንግዳ አቀባበል ዓለም ያወቀውን
ያለንን ተካፍለን ስቀን እናድራለን
ሁሌም ባይሳካ ገበታ እንኳ ቢያጥረን
ቆሎ ንፍሮ አንባሻም ፈዲሻ ፈንድሸን
ለሱስ መቁረጫቸው ቡን እንደርጋለን !።
እንኳን ደህና መጣሽ በመረጥሽው መንገድ
መልበስሽ መች ከፋ ባለ ቀለም ልብስ
ድሮም ቅር ያሰኘው ፊት አለመመለስ !!።
በለው! //////<<<<//////<<<<
YeKanadaw Kebede says
ጨዋከታው ይበልጥ
መልክቱ የላቀ
ከሆታው፤ ከልልታው
ድምጹ የደመቀ
ጥሪው የረቀቀ
የ’ሕታችን ፎቶ፤
ይታየኛል ጎልቶ
እና………
“ሙዳ ሥጋ ወድቃብኝ
አፈር አንስታብኝ
እንዳልተወው ሥጋው
እንዳልበላው አፈሩ”……እንዳለው ሆነብኝ
January 2013