• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የጠቆሩ ልቦች”

January 8, 2013 08:54 am by Editor 5 Comments

“የጠቆሩ ልቦች”

ይቺ አጉል ዘመናይ፣ የወንዜ ልጅ እቱ

አፍሪካዊ መልኳ፤ “ደብሯት” ጥቁረቱ

ፊቷን በ“ሜክ አፕ” እጇን በእንሶስላ

ፀጉሯን ባንዳች ቀለም፣ ቀባችው ልትቀላ፡፡

ግን ባይገባት እንጂ፣ እንዲህ የምትደክም

እንዲህ የምትለፋ …

የቆዳችን ሳይሆን፣ የልባችን መጥቆር ነው አገር ያጠፋ፡፡

ሰለሞን ሽፈራው
“ተወራራሽ ሕልሞች” መጽሐፍ

ባለፈው “ሕልም እንኳ የታለ?” በሚል ርዕስ ላወጣነው ጨዋታ ምላሽ በመስጠት ጨዋታውን ላደመቃችሁት ዱባለ፣ በለው፣ inkopa እና Yekanadaw kebede ምስጋናችን እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡ በተለይ በዚህኛው አስደናቂ ቅኔዎችም ተዘርፈዋል፤ ወላድ በድባብ ተሂድና አገራችን አሁንም ባለቅኔዎችንና ጥበበኞችን እንዳላጣች እናንተ ምስክር ናችሁ፡፡ ክብረት ይስጥልን፡፡ ለዚህኛው ጨዋታ ደግሞ እስቲ ተቀኙልን! (ፎቶውን ያገኘነው ከፌስቡክ ነው፤ ባለቤቱ ካስታወቀን ዕውቅና እንሰጣለን)

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    January 8, 2013 05:22 pm at 5:22 pm

    ^^^^^^^^^^^^^^^^^^
    አይ ውበት ! አይ ድምቅት !
    ተፈጥሮ ያደለሽ እንደ ማር ወተት
    የጥቁር ውብ ቆንጆ የሀገሬ ወጣት
    ማን ሊሥተካካለው ጥቁርን ሰውነት ?
    የፀጉርሽ ላይ ጌጥ የአካልሽ ንቅሳት
    የዓይኖችሽ ድምቅት የጥርስሽ ንፃት
    ነጭን ስትደርቢ በጥቁር ሰውነት
    እንዳያስመስልሽ ውሃ የገባች ድመት
    ነጭ በጣም ይጎላል ጥቁርን ለማጥፋት
    የቆዳሽን ጥቁረት ኩሪበት ኩሪበት
    ልብሽን በፍፁም ከቶ እንዳታጠቁሪያት
    ዓይንሽ በርቶ ጆሮሽ ነቅቶ ክብርሽን ጠብቂያት
    ታላቅ በረከት ነው ኢትዮጵያዊነት !!
    አህጉሪቱ አፍሪካም የመልከኞች ቤት ናት!።
    ^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
    “መልካም የክርስቶስ ልደት በዓል ለጋዜጣው ባለቤቶች አዘጋጆች ባለሙያዎችና ለተሳታፎዎች ለሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን ከምስጋና ጋር በቸር ይግጠመን !” ከሀገረ ካናዳ

    Reply
  2. Alelign says

    January 8, 2013 11:59 pm at 11:59 pm

    የኔ የዋህ ገላ ግብግቡ አድክሞሽ
    ቀለምሽን ለመሸሽ አልሸሽ ሲልሽ
    ያለሺን መለወጥ ስትቸጋገሪ
    ነጩን እንዳትጎጂው ፤ ከራስሽ እደሪ
    ባለነጩ ቆዳ እንዴት እንዳጠላው ጠጉሩን ሲያከረድድ በጄል ሲለውሰው
    የሽንብራ ማሳ መስሎ ሲያጋጊጠው?
    አላየሽም እንዴ …..አፍሪካዬ ድንግል
    የሌለን መናፈቅ የሁሉ ስራ ነው
    ነጩ ራሱን ጠልቶ
    ጸኃይ ላይ ተሰጥቶ
    ጆሮውን በሳስቶ
    ፊቱን ቀረዳዶ
    በአዲስ ሞዴል ሂሳብ ሲንጎራደድልሽ?
    የተፈጥሮሽ ውበት እርሱን አስክሮታል
    ለመዘረፍ እሺ
    ለመገደል እሺ
    ለመታለብ እሺ ባልሽበት ቀን ሁሉ
    ፍቅርሽ ፈገግታሽ ሰላምሽ ደንቆታል
    የንቺን ነገር ወስዶ ባለው የመሰለው ተኮንኖበታል
    እሱ የሸሸውን ፈልገሽ ስትሄጂ ፊትሽን ስታነጪ ተስፋው ይጨልማል
    ራሱን እንዳጠላ መሄጂያ በማጣት በሃዘን ይሞታል፡፡
    አደራ አፍሪካዬ ለሱ ብለሽ እንኩዋን ነጩን አትምሰይ
    በነጭ ቆዳውስጥ ለመሸገው ሰይጣን
    በጥቁር ቆዳውስጥ ያለው ውብ ብርሃን ይገለጥለታል
    እየተጎተተ ከግርሽ ስር ይወድቃል
    በጥቁር ቆዳ ውስጥ ነጭ ልብ እያየ ይሰለፍልሻል
    እውነቱን ላስታውሺሽ ተጎጂ መርታቱን አለም ቀድሞም ያውቃል
    Ethiochristian.net

    Reply
  3. Yekanadaw kebede says

    January 10, 2013 05:01 pm at 5:01 pm

    ቀለም ቀቢዎቹ
    ወሬ አቀባዮቹ
    ጆሮና ዓይን ናቸው፤ ልብ ምን አጠፋ
    ከጓዳ ሳይወጣ፤ሌት ከቀን በለፋ
    አጭሩን ረጅም፤ጥቁሩን ነጭ ብለው
    ለቅሶን በሙዚቃ ዘፈን አስመስለው
    ከክተው፤ አቡክተው ካላቀረቡለት
    ልብ ‘ልብ’ የለውም የሚመዝንበት
    እንደዛሬ ዳኞች፤ነው የልብ ነገር
    ጥላ ሲሉት መጥላት
    አፍቅር ሲሉት ማፍቀር

    Reply
  4. ዱባለ says

    January 10, 2013 07:49 pm at 7:49 pm

    ባይገባን ነው እንጂ ሁሉም ይወደዳል
    ባመት በአል በደስታ ነጭ ይለበሳል
    አንዳንዱም ሲፈልግ በጥቁር ይዋባል
    ባግባብ ከተያዘ ሁሉም ቀለም ያምራል::
    አናመሳስላቸው ጥቁርና ክፉን ስራ
    ነጭም ጥላሸት ነው አጥፊ እንደ ኖራ
    መታ መታ አርገው ሚያቦኑት እንደ አቧራ
    ነጭ ሰው አያደምቅም በራሱ ካልኮራ
    ውስጠ ባዶ ሆኖ መነፋት በጉራ
    ያጋልጣልና ለባሰ መከራ::

    Reply
  5. inkopa says

    January 11, 2013 02:50 am at 2:50 am

    ልክ እንደፊታችን
    ቢነበብ ልባችን
    ጨለማው ጓዳችን
    የውስጡ ጥቀርሻ
    የሌለው ማበሻ::
    ይፋ ቢወጣማ!
    ድብቁ ከተማ
    ሽፍኑ ጉራንጉር
    ሰው ያቆመው ነበር
    ጠፈርን መመርመር
    መሄድ እግዜር ሰፈር::
    ጦርነት አቁሞ የዓለም ወታደር
    ሃሳቡን ጊዜውን
    ገንዘብና ዓቅሙን
    ባዋለው ነበረ እዚህ ላይ ዕውቀቱን
    ማንጣት በታገለ የጠቆረ ልቡን!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
Copyright © 2026 · Goolgule