ሕልም እንኳ የታለ?
በሕልሜ ተኝቼ፣
ሸጋ ሕልም አይቼ
በአገሬ በአፍሪካ ዲሞክራሲ በቅሎ
ፍትህ፣ እኩልነት፣ መብቱ ተደላድሎ
ወገኔ ሲያጣጥም የሰላምን ፍሬ
ሽብር ተወግዶ በመላው አገሬ
. . . ይህን እያለምኩኝ አልጋ ውስጥ አርፌ
. . . ጥይት ቀሰቀሰኝ ከሞቀው እንቅልፌ፡፡
ሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል) ከፀሐይ በታች መድብል 2004ዓ.ም
“መሰላል” በሚል ርዕስ ላወጣነው የግጥም ጨዋታ ድንቅ ምላሽ በመስጠት ጨዋታውን ላደመቃችሁት በለው፣ ዱባለ፣ አሥራደው (ከፈረንሳይ) እና yeKanadaw kebede ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ እያንዳንዳችሁ የቋጠራችሁት ግጥም በራሱ የግጥም ጨዋታ ሆኖ ሊቀርብ የሚችል ነው፡፡ በነገራችን ላይ ዛሬ ለጨዋታ ያቀረብነው ግጥም ከዚህ በፊት “ሕልመኛው” በሚል ካወጣነው ጨዋታ ጋር በ“ሕልም” እንኳን የማይገናኝ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
አሁን ደግሞ “ሕልም እንኳን የታለ?” ይለናል የ“አክሱምን አቃጥሉት” እና ሌሎች ግጥሞች ደራሲ ሰለሞን ሞገስ (ፋሲል)፡፡ እናንተስ ምን ትላላችሁ? “ሕልም ዱሮ ቀረ …” ወይስ … እስቲ በግጥም አድርጉታ ጨዋታውን!
ዱባለ says
አይመሳሰሉም ሕልምና ቅዠት
ሕልም ሰላማዊ ቅዠት ነው እብደት
ሚያስፈራ; ሚያስጮህ; ሚያፈራግጥ ቅዠት
ሕልም ግን በአንጻሩ እጅግ ጥሩ ምኞት
ለድህ ህብት ለጋሽ ሰላም ሰጪ ለህብታም
ላዘነ አጽናኝ አገናኝ ነው ለናፋቂም
ማን ያውቀዋል ዛሬ ጊዜው ተቀያይሯል!!
ባገሬ ኢትዮጵያ ሕልሙ ቅዠት ሆኗል::
በለው ! says
ሁሌ እየተመኙ እንቅልፍ ሊወስድዎ
አስራአንደኛው ሰዓት ፍጥጥ ማለትዎ ?
ከቶ ማነው ያለው ሕልም ነው የሌለው
ሁሉ እያሰበ የሚያልምነው የጠፋው
ዲሞክራሲ በዘር የሚበቅል በነበር
አጭደንም ከምረን እንወቃው ነበር
ፍትህ እኩልነት ሰላም ብልፅግና
ያሰብነው ተሳክቶ ፍሬው በአፈራና
ሀገሬን እነደጥንት ባረጓት ገናና
ይች ነበረች ሕልሜ ሁሌም የማልማት
ሕልምን ወደድኩና ማሸለብን ጠላኋት።
*****************
በለው!ከሀገረ ከናዳ ከምስጋና ጋር
inkopa says
ህልምም ሆነ ቅዠት
አይገቡም ከኔ ቤት
ተባይ ፈልቶ በቅቶት
ጠግቦ በሚያድርበት
ስናውዝ አድሬ ስወጣ በጠዋት
ህልም ህልም አትበሉኝ ቁንጫን ጠይቋት
Yekanadaw kebede says
ሕልም የሚፈታ ሰው ጠይቄልህ ነበር
ሰላም፤ዴሞክራሲ፤ፍትሕ፤ ገሌ-መሌ
የሚባለው ነገር
አርጅቷል መሬቱ፤ አይበቅልም እኛ አገር
የጮኸውም ጥይት አንተን ያባነነው
የነቃ፤ ያወቀ፤ ሌላ አስተኝቶ ነው