
ህልመኛው
ህልመኛ ነው እርሱ
ሳያልም አያድርም፤
ኑሮው ማለም እንጂ
ህልሙን ኖሮ አያውቅም፡፡
የሚለውን የቃልኪዳንን ግጥም ፌስቡክ ላይ ያነበበው ታምራት አወቀ (ሚራ) “እሱ” እያለች የገለጸችው እርሱን መስሎት በመባነኑ ከያኔዎቹ ህልሞቹ አንዱን እንካችሁ ብሏል፡፡
ፍሬ አልባ አዝመራ
ሕልሜን ከእውኑ ጋር አገናኝቶ ‘ሚያሳይ
መሄጃ ጎዳና አቅጣጫ እንጂ የጠፋኝ
የሕልም የሕልምማ
ተጋድሜ ውዬ፣ ተኝቼ እያደርኩኝ
ብዙ ያመረትኩት፣ ሁሌ ‘ሚናፍቀኝ
ለሚዛን የሚከብድ፣ ፍሬ ያላፈራ፣ የሕልም አዝመራ አለኝ::
ታምራት አወቀ (ሚራ) 2003 ዓ.ም
እናንተስ ምን ትላላችሁ? የምታካፍሉት “የህልም አዝመራ” አላችሁ? ወይስ ሌላ የምትሉት አለ?
ባለፈው ኑረዲን ዒሳ እኔ ምን አገባኝ በሚል ርዕስ ላቀረበው ግጥም ምላሽ የሰጣችሁትን Tsinat፤ ሰማኸኝ፤ yeKanadaw kebede (ሁለት ጊዜ)፤ Gedeon፤ dawit እና inkopa በተዋቡት የግጥም ስንኞቻችሁ ጨዋታውን ሞቅ ደመቅ ስላደረጋችሁት ከልብ እናመሰግናችኋለን፡፡ እስቲ አሁን ደግሞ “በህልም” እንጫወት፡፡
ፍችውን ንገሩኝ
—————-
ስወለድ ሰልሜ
ቁራአን አክትሜ
ሮመዳን ፆሜ
ሕልም አየሁ በሕልሜ
እንደ ቄስ ጠምጥሜ
ሙሐመድ ነው ስሜ
ግራ ቢገባህ ነው
ገሃዱን ህልም ያልከው
ፍልሰታ አስቀድሰህ
ረመዳን ጾመህ
ያደከው ሰፈሬ
አባትህ መምሬ
አጎትህ ሼክ ናቸው::
እንዴት ቢብስህ ነው
ኑሮህን ህልም ያልከው?
በህልም አለም ሆኜ ሌላ ህልም አለምኩኝ
ካንደኛዉ ስወጣ በሌላ ህልም ኖርኩኝ::
ሕልም
የጥንት ሕፃናት፤
ገና በጨቅላነት፤
ገብተው ሳይማሩ – ፊደል ት/ ቤት፤
ልባሞች ነበሩ – ሕልም ነበራቸው፤
ሁሌ ሳይታክቱ – ማታ ማታ አቅንተው፤
ጨረቃን መቃኘት አልፈው ከምድራቸው ::
የዘመኑ ልጆች ሥራው ብዙ ናቸው
ሌት ተቀን ሲሮጡ እንቅልፍም የላቸው፤
እንኳን ለጨረቃ ላሉበት ምድራቸው፤
ሁሌ እየባዘኑ ማለም አቃታቸው ::
ሳቴላይት እና ቴሌቪዥን መጥተው
የትላንቱን ስበው የነገን ጎትተው
እያቀረቡልኝ እንደ እህል ፈትፈተው
ጊዜ ውድ ሆኖ – ደቂቃ እንደገንዘብ እየተቆረ
በጨለማው ዘመን – ሕልም ዱሮ ቀረ
በአካል ተደላድሎ
ሐሳብ በሰው ጥሎ
እንቅልፍ ከወሰደው
እውነት ህልመኛ ነው
ከቶ ህልሙን ካልፈታው
ህልሙንም ካልኖረው
ተነስ ንቃ ቅዠት ላይ ነህ በለው !
ግጥም በጣም ስለምወድ የናንተን ገፅ በማግኝቴ ተደስቻለው ።