በበርካታዎች ዘንድ የተለያዩ ስሞች አሏቸው፤ የአደባባይ ምሁር፣ አንጋፋ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ፣ ጋሼ መስፍን፣ ወዘተ፡፡ በእኛ ግምት ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ የሚለው ገጣሚ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በተለይ በቅርብ ዓመታት ያሳተሟቸው መጻህፍት፣ የጻፏቸው ጦማሮች፣ ወዘተ ይህንን ማዕረግ ሊያሰጥዋቸው ይችላሉ ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ ፕ/ር መስፍን በህይወት ዘመናቸው ካስተማሩትና ካስተላለፉት ዕውቀት በተጨማሪ እጅግ በርካታ መጻህፍትን በማሳተም ይህንን ለዘመናት የዳበረውን ዕውቀታቸውን ለመጪው ትውልድ እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ አራት መጻህፍትን አሳትመዋል፡፡ በመጪው ሚያዚያ ወር 83 ዓመታቸውን ከማክበራቸው በፊት ባለቅኔው መስፍን በሰማኒያዎቹ ዕድሜያቸው ይህንን ሁሉ ለማድረግ መብቃታቸው ከጻፉት መጻህፍትና አርቆ … [Read more...] about “መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ”
Literature
ጽፈኪን
“የጠቆሩ ልቦች”
“የጠቆሩ ልቦች” ይቺ አጉል ዘመናይ፣ የወንዜ ልጅ እቱ አፍሪካዊ መልኳ፤ “ደብሯት” ጥቁረቱ ፊቷን በ“ሜክ አፕ” እጇን በእንሶስላ ፀጉሯን ባንዳች ቀለም፣ ቀባችው ልትቀላ፡፡ ግን ባይገባት እንጂ፣ እንዲህ የምትደክም እንዲህ የምትለፋ … የቆዳችን ሳይሆን፣ የልባችን መጥቆር ነው አገር ያጠፋ፡፡ ሰለሞን ሽፈራው “ተወራራሽ ሕልሞች” መጽሐፍ ባለፈው “ሕልም እንኳ የታለ?” በሚል ርዕስ ላወጣነው ጨዋታ ምላሽ በመስጠት ጨዋታውን ላደመቃችሁት ዱባለ፣ በለው፣ inkopa እና Yekanadaw kebede ምስጋናችን እጅግ ከፍ ያለ ነው፡፡ በተለይ በዚህኛው አስደናቂ ቅኔዎችም ተዘርፈዋል፤ ወላድ በድባብ ተሂድና አገራችን አሁንም ባለቅኔዎችንና ጥበበኞችን እንዳላጣች እናንተ ምስክር ናችሁ፡፡ ክብረት ይስጥልን፡፡ ለዚህኛው ጨዋታ ደግሞ እስቲ ተቀኙልን! (ፎቶውን ያገኘነው … [Read more...] about “የጠቆሩ ልቦች”
ሕልም እንኳ የታለ?
ሕልም እንኳ የታለ? በሕልሜ ተኝቼ፣ ሸጋ ሕልም አይቼ በአገሬ በአፍሪካ ዲሞክራሲ በቅሎ ፍትህ፣ እኩልነት፣ መብቱ ተደላድሎ ወገኔ ሲያጣጥም የሰላምን ፍሬ ሽብር ተወግዶ በመላው አገሬ . . . ይህን እያለምኩኝ አልጋ ውስጥ አርፌ . . . ጥይት ቀሰቀሰኝ ከሞቀው እንቅልፌ፡፡ ሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል) ከፀሐይ በታች መድብል 2004ዓ.ም “መሰላል” በሚል ርዕስ ላወጣነው የግጥም ጨዋታ ድንቅ ምላሽ በመስጠት ጨዋታውን ላደመቃችሁት በለው፣ ዱባለ፣ አሥራደው (ከፈረንሳይ) እና yeKanadaw kebede ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ እያንዳንዳችሁ የቋጠራችሁት ግጥም በራሱ የግጥም ጨዋታ ሆኖ ሊቀርብ የሚችል ነው፡፡ በነገራችን ላይ ዛሬ ለጨዋታ ያቀረብነው ግጥም ከዚህ በፊት “ሕልመኛው” በሚል ካወጣነው ጨዋታ ጋር በ“ሕልም” እንኳን የማይገናኝ መሆኑን ለመግለጽ … [Read more...] about ሕልም እንኳ የታለ?
እንዴት ሀገር (ህዝብ) ይጥፋ?
እንዴትሀገር (ህዝብ) ይጥፋ? ያለመተማመን ስለዘራን ዘር እንሰበስባለን የማያልቅ ‘መከር’። ‘’መግዛት’’ እውቀት ሆኖ፣ ገንዘብና ሀይል አቋራጭ ጎዳናው ‘መቦልተክ’ ሆኗል። ሃይማኖት ተንቃ ስትሆን መቀለጃ የእግዚአበሄርም ቃል ሆነ ምነገጃ። ሳይሰሩ ያገኙት ሀብት፣ ክብር - ዝና ያስከብር ጀመረ መናቁ ቀረና። ፈረሀ - እግዚአብሄር ከልባችን ወ’ቶ ህገ - አውሬ ይገዛናል ሰው-ከሰው አባልቶ። ለመሾም - መሸለም፣ መክዳት - መከዳዳት ምግባራችን ሆኗል ዋናው ሀይማኖት። እያለን የሌለን ስለሆን ተመፅዋች መጠሪያችን ሆነ እናንተ ለማኞች። እውነት ተገንዞ ስለተቀበረ ውሸት ገዥ ሆነና ሰው ለ’ሱው አደረ። ፍቅርና ሰላም ፈላጊ ስለአጡ ተባረው ሄደዋል በአገር እንዳይመጡ። በሌሎች ደም - እምባ፣ ንዋይ … [Read more...] about እንዴት ሀገር (ህዝብ) ይጥፋ?
መሰላል
መሰላል መሰላል ለመውጣት አለው ትልቅ ብልሃት፡፡ የላዩን ጨብጦ፣ የታቹን ረግጦ፣ ወደላይ መመልከት፡፡ እጆችን ዘርግቶ በኃይል መንጠራራት፡፡ ጨብጦ መጎተት የላዩን! ላዩ ታች እንዲሆን! አንድ ባንድ እየረገጡ፣ መሰላል የወጡ፡፡ ብልሆች የማይጣደፉ፣ ሞልተዋል በያፋፉ! ዘርግተው የጨበጡትን መርገጥ፣ የመውጣት ሕግ ነው የማይለወጥ ሲወርዱ ግን ያስፈራል፤ የረገጡትን ያስጨብጣል፡፡ (መስፍን ወልደማርያም፣ እንጉርጉሮ፣ 1967) yeKanadaw kebede “በሳቅ ፍርስ አሉ” በሚል ርዕስ ላቀረቡት የግጥም ጨዋታ ዱባለ፣ በለው እና dawit ለጨዋታው ምላሽ ስለሰጣችሁ ከልብ እናመሰግናችኋለን፡፡ የጨዋታውን ደራሲ yeKanadaw kebede እንዲሁ፡፡ ስለ “መሰላል”ስ ምን ትላላችሁ? እስቲ ጨዋታውን አምጡታ!? … [Read more...] about መሰላል
ማነው ተጠያቂው?
ማነው ተጠያቂው? ለኅሊናችን፣ ለትወልድ፣ ለሀገር ሰው - ስለ ሰው ብሎ፣ እስቲ ሰው ይናገር፤ በዚች ዓለምችን፣ መለኪያው ምንድን ነው ከገዥና ተገዥ፣ ተጠያቂው ማነው? ጥቂቶች በቡድን፣ ብዙሀኑን ገፍተው የሰውን ስብዕና፣ ማንነቱን ገፈው፤ በጥይትም ይሁን፣ በታንክ ደፍጥጠው እነሱ እንዲገዙ … ማነው የፈቀደው? ሰለኅሊናችን፣ ስለ እውነት በሀቅ ሰው - ለራሱ ብሎ፣ ‘ራሱን ይጠይቅ። ብዙ በልተው - ብዙ ‘ለማበት’ ብዙ ተግተው - ብዙ ለመሽናት፤ …ለጮማ - ቅርናታቸው… …ለውስኪ - ቅርሻታቸው… …ለእኩይ - ምግባራቸው፤… እንደ አንድ ሰው ሆነው፣ሲቆሙ በአንድነት ለክቡር አላማ፣ ሌላው ሲሆን “ኩበት’’፤ እነሱ ምን ያ’ርጉት?... ምንስ ያቅርቡለት…? ሰው ነኝ የሚል ዜጋ፣ ከተነዳ እንደ ከብት። ሀገርን አፍርሰው፣ ትውልደን አጥፈተው እንድ ቅርጫ ስጋ፣ ህዝብንም … [Read more...] about ማነው ተጠያቂው?
በሳቅ ፍርስ አሉ
በሳቅ ፍርስ አሉ አገራቸውን በመክዳት ወገናቸውን ለመጉዳት ያልነበረ ሕግ ጥሰው በነስብሐት ነጋ – በነ መለስ ተከሰው ሽብርተኛ ሲባሉ ‘በሳቅ ፍርስ አሉ’ አሉ፡፡ ሽ-ሽ-ት በሚል ርዕስ ላቀረብነው የአብዲ ሰኢድ ግጥም ግሩም የሆነ ምላሽ በመስጠት ጨዋታው ሞቅ ደመቅ ላደረጋችሁት dawit፣ ሽማግሌው፣ በለው፣ yeKanadaw kebede እና ዱባለ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ በዚህ የግጥም ጨዋታችን የዘወትር ተሳታፊ የሆኑት የካናዳው ከበደ (yeKanadaw kebede) “ለሚቀጥለው የግጥም ጨዋታ አድርጓት” ብለው “በሳቅ ፍርስ አሉ” በሚል ርዕስ “አሸባሪ” በመባል ተከስሰው በእስር የሚማቅቁት ወገኖቻችንን በተመለከተ የላኩልንን ግጥም ነው ላሁኑ ጨዋታችን ያቀረብነው፡፡ እስካሁን ግጥም ስናቀርብ የነበረው ከሌሎች ቦታዎች ነበር አሁን ግን የካናዳው ከበደ የራሳቸውን … [Read more...] about በሳቅ ፍርስ አሉ
ሽ – ሽ – ት …!
ሽ - ሽ - ት …! እንደዋዛ ሲከንፍ ዕድሜዬ እኔን ጥሎ ስም ያልዘራሁበትን ወኔዬን ጠቅልሎ እንደ ቀልድ ፤ እንደ ህልም ፤ ሲከስም ወዘናዬ ብ … ን … ! ሲል የኋሊት ጠጉሬ ከላዬ እንደው እንደ ዘበት ልጆች ሲሉኝ ጋሼ መናገር ያምረኛል ዕድሜዬን ቀንሼ፡፡ ይህንንም ግጥም ያገኘነው ከፌስቡክ ላይ ሲሆን ታዋቂው ገጣሚ አብዲ ሰኢድ ነው የገጠመው፡፡ ምስጋናችንን እንቸረዋለን፡፡ በሥራ መደራረብ እንደታሰበው በወቅቱ የግጥም ጨዋታችንን በማዘግየታችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ ባለፈው “ህልመኛው” በሚል ርዕስ ላወጣነው ግጥም አጸፋ መልስ የሰጣችሁ የዘወትር ገጣሚዎቻችንን yeKanadaw kebede፣ inkopa፣ Tsinat፣ እና አሥራደው ከፈረንሳይ ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ስለ “ሽሽት” ምን ትላላችሁ? ሽሹ! ሽሹ! ወይስ …? እስቲ ጨዋታውን አምጡት? … [Read more...] about ሽ – ሽ – ት …!
ሞተ ያለው ማነው?
ፕ/ር አስራት አስራት ወልደየስን ሞተ ያለው ማነው? በረከቱን ያጣ የሞተ መለስ ነው፣ ፕ/ር አስራት አልሞተም ውሸት ነው፣ ኢትዮጵያን ሲቆርሷት ቁጭብየ እንደ ግርማ አላይም ነው ያለው፣ ታሞነው የሞተው? ማነው የገደለው? ያለ ይመስለኛል ስሙን ቀይረውት አለማየሁ ብለው፡፡ ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል … [Read more...] about ሞተ ያለው ማነው?
ማን ጸሎት ያሳርግ
ወ/ሮ ለምለም ጸጋው በእስልምና ሃይማኖትም ሆነ መብታቸውን ለማስጠበቅ በመናገራቸው በእስር ቤት ለሚማቅቁ ሁሉ በፎቶ አስደግፈው የጻፉትን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about ማን ጸሎት ያሳርግ