በሳቅ ፍርስ አሉ
አገራቸውን በመክዳት
ወገናቸውን ለመጉዳት
ያልነበረ ሕግ ጥሰው
በነስብሐት ነጋ – በነ መለስ ተከሰው
ሽብርተኛ ሲባሉ
‘በሳቅ ፍርስ አሉ’ አሉ፡፡
ሽ-ሽ-ት በሚል ርዕስ ላቀረብነው የአብዲ ሰኢድ ግጥም ግሩም የሆነ ምላሽ በመስጠት ጨዋታው ሞቅ ደመቅ ላደረጋችሁት dawit፣ ሽማግሌው፣ በለው፣ yeKanadaw kebede እና ዱባለ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡
በዚህ የግጥም ጨዋታችን የዘወትር ተሳታፊ የሆኑት የካናዳው ከበደ (yeKanadaw kebede) “ለሚቀጥለው የግጥም ጨዋታ አድርጓት” ብለው “በሳቅ ፍርስ አሉ” በሚል ርዕስ “አሸባሪ” በመባል ተከስሰው በእስር የሚማቅቁት ወገኖቻችንን በተመለከተ የላኩልንን ግጥም ነው ላሁኑ ጨዋታችን ያቀረብነው፡፡ እስካሁን ግጥም ስናቀርብ የነበረው ከሌሎች ቦታዎች ነበር አሁን ግን የካናዳው ከበደ የራሳቸውን ግጥም በመላክ ጨዋታው ከኛው ለኛው እንዲሁን ስላደረጉ በጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ሌሎቻችሁም እንዲሁ ለጨዋታ የሚሆን እጥር ምጥን ግጥም ከላካችሁልን በደስታ የምናስተናግድ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
yeKanadaw kebede says
The Picture you (the editor) picked gives it more meaning.
Thank You
ዱባለ says
ሲረግሙት ውለው
በነቀለሕ ብለው
ባልተፈጠረ ባላየነው
ሲደርስ የተመኙት
በምታት በጸሎት
በስግደት በሶላት
ለተመኙት ነገር አልቅሱ ተባሉ
ከለቅሶ በኋላ በሳቅ ፍርስ አሉ::
በለው ! says
ይቺ ነች ሳቅ ወደ ውስጥ የማይታይ ኃይሉ
እንዴት ?እኮ ለምን? በሳቅ ፍርስ አይሉ
ባልነበረ ህግ ተከሰው!! ሕዝብ ይፍረደን እያሉ !
ሀገራቸውን ከዱ ሕዝባቸውን ጎዱ አሉ?
እኩልነት ሰላም ፍትህ ስለጠየቁ ለሁሉ
አሸባሪ ከተሸባሪው ይለይ ስለአሉ ?
የሚረዳ አጥተው ደከሙ ማረፊያ ቤት ዋሉ
ከዚህ በላይ ምን ፌዝ አለና በሳቅ ፍርስ አይሉ?
በለው! ከሀገረ ካናዳም ሳቀ እሰይ አንበሶቼ ይበሉ።
dawit says
ከሳቅ ሁሉ፣ከሚያንከተክተው
ሆድ እያቆሰለ ከሚያንፈረፍረው፤
የሚያስቀው ነገር፣የሚያብከነክነው
ግልብ የሆነው ጉዳይ ሚዛን መድፋቱ ነው፤
መገረም ሲያስቀን
ሃፍረት ሲያስፈግገን
የሳቃችን መብዛት ለ-ምባ ከዳረገን፤
ደስታ የሚመስለው ለቅሶን ተክቶ ነው!!
ሳቅ ለቅሶን ተካልን አ-በጀ ማለት ነው፤
abedu rohmane says
ma shaa allahe