በበርካታዎች ዘንድ የተለያዩ ስሞች አሏቸው፤ የአደባባይ ምሁር፣ አንጋፋ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ፣ ጋሼ መስፍን፣ ወዘተ፡፡ በእኛ ግምት ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ የሚለው ገጣሚ ነው ብለን እናምናለን፡፡ በተለይ በቅርብ ዓመታት ያሳተሟቸው መጻህፍት፣ የጻፏቸው ጦማሮች፣ ወዘተ ይህንን ማዕረግ ሊያሰጥዋቸው ይችላሉ ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡
ፕ/ር መስፍን በህይወት ዘመናቸው ካስተማሩትና ካስተላለፉት ዕውቀት በተጨማሪ እጅግ በርካታ መጻህፍትን በማሳተም ይህንን ለዘመናት የዳበረውን ዕውቀታቸውን ለመጪው ትውልድ እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ አራት መጻህፍትን አሳትመዋል፡፡ በመጪው ሚያዚያ ወር 83 ዓመታቸውን ከማክበራቸው በፊት ባለቅኔው መስፍን በሰማኒያዎቹ ዕድሜያቸው ይህንን ሁሉ ለማድረግ መብቃታቸው ከጻፉት መጻህፍትና አርቆ አሳቢነታቸው በተጨማሪ በአድናቆት ሊጠቀስ የሚገባው የመንፈስ ጥንካሬ ነው፡፡
በመጻህፍትና በመጽሔት ብቻ አልተወሰኑም፤ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ከወጣት እስከ ጎልማሳ ምሁራን በብዛት የማይጠቀሙበትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመገልገል አስተዋዩ መስፍን በራሳቸው ብሎግ ላይ ጦማራቸውን እያተሙ በየጊዜው ያስተምሩናል፤ የወደፊቱን አበሳ እንድንወጣ ሥራቸውን ለዘመኑ ወጣት በፍጥነት ያስተላልፋሉ፡፡ ምክንያቱም ለመስፍን “ዝምታ ወርቅ” አይደለም፤ “አያገባኝም” ማለትም መፍትሔ አይደለም፡፡
የአገራችን ታሪክ ፈጽሞ እየተዛባና መስመር እየለቀቀ፤ የሕዝባችን ሞራልና ሰብዓዊነት ዕርቃኑን እየቀረ፣ እጅግ በርካታ ባዕድ ነገሮች እንደ ኢትዮጵያዊ ባህል ለዘመናት እየተጨመሩ ባለበት ባሁኑ ወቅት ፕ/ር መስፍን የሚያሳትሟቸው መጻህፍት በዕድሜያቸው ያካበቱትን ልምድ ለአሁኑ ዘመን ትውልድ ዋቢ ይሆን ዘንድ የተጻፉ ብቻ ሳይሆኑ በህዝባችን ውስጥ ለዘመናት የተንሰራፋውን ችግር ግልጽና ማንም ሊያስተውለው በሚችል መልኩ በትነው የሚስተምሩ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ችግሩ ብቻ አይደለም የሚጽፉት፤ መፍትሔውን ጭምር እንጂ፡፡ “ነቢይ በአገሩ አይከበር” እንደሚባል የአገራችንን አዋቂዎች ድንቅ ሥራዎች ቸል እያልን ወደምዕራባዊያንና ሌሎች የባዕድ ቋንቋ ሥራዎችና ትምህርቶች በማተኮራችን መሠረታዊውን የአገራችንን ችግር በውል ለመለየትና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ቸግሮናል፡፡
ከውጪ በቀጥታ በተቀዱና ለኢትዮጵያውያን ባህልና አኗኗር ፈጽሞ ባዕድ የሆኑ የፖለቲካ አመለካከቶችን በህዝባችን ላይ ተጭነው የሚናገረውን የማያውቅ ሰባኪ ቋንቋውን ለማያስተውል ሕዝብ ሲሰብክ ስንት ዘመን አለፈ?! ችግሩ መጫኑና ከሌሎች መቀዳቱ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ እንዲሆን አለመደረጉ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ የሥልጣኔ ዕድገት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ … እንዲመጥን ተደርጎ ኢትዮጵያዊ እንዲሆን ሳይደረግ በመቅረቱ ችግሩ ያለው ችግሩ ላይ ይሁን ወይም መፍትሔው ላይ በውል ሳይታወቅ የሥልጣኔ ቀደምት የነበርን የዓለም ጭራ ሆነናል፡፡ ፕ/ር መስፍን እንደሚሉት ሥልጣንን መግራት አቅቶናል፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የታተሙት የፈላስፋው መስፍን መጻሕፍት “ሥልጣን፤ ባህልና አገዛዝ፤ ዴሞክራሲና ምርጫ”፤ “የክህደት ቁልቁለት” እና “አደጋ ያንዣበበበት የአፍሪካ ቀንድ” ከላይ የጠቀስናቸውን ብቻ ሳይሆን እጅግ ሰፋ ያሉና ጥልቀት ያላቸውን የአገራችንን ጉዳዮች ይዳስሳሉ፡፡ የችግራችንን ምክንያትና ምንጭ ያስረዳሉ፡፡ ግልጽና ለማንም የማያሻማ መፍትሔ ይሰጣሉ፡፡
ሰሞኑን ያሳተሙት “መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ” የሚለው መጽሐፍ ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር የሚያውቅና አማርኛ የሚያስተውል ሁሉ ሊያነበው የሚገባ ነው፡፡ “ለምን ግን እኛ ኢትዮጵያውያን እንዲህ ሆንን?” ብሎ የሚጠይቅ ሁሉ የከሸፍንበትን ምክንያትና በየትኛው መስክ እንደከሸፍን ለማወቅ ይህ መጽሐፍ ለዘመናት ሲመኘው የነበረ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ መጽሐፉ ሲጀምር ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፤ እንዲህ በማለት
ቁም! በመጀመሪያ ለአንባቢው አንድ ማስጠንቀቂያ ልስጥ፤ መጽሐፉ በጠቅላላ፣ በተለይም ይህ መቅድም የከረረ ንዴት መግለጫ ነው፤ በኢትዮጵያ አጠቃላይ ሁኔታ ያልተናደደ፣ የማይናደድና ያልተበሳጨ፣ ወይም ደልቶት የሞቀው ይህንን መጽሐፍ፣ በተለይም ይህንን መቅድም አያንብበው፤ የረጋውን መንፈሱን ያስሸብረዋል፡፡
ፕ/ር መስፍን መጽሐፍ በማሳተም ለመበልጸግ የሚመኙ ሰው እንዳልሆኑ የሚያስተውል ሁሉ ይህንን መጽሐፍ እዚህ ላይ ማስተዋወቃችን የትርፍ ጉዳይ ሳይሆን ለአገራችንና ለወደፊት ትውልድ ከማሰብ እንደሆነ ለማሳሰብ የሚያስፈልግ አይመስለንም፡፡ ስለሆነም መጽሐፉም ሆነ ሌሎች መጽሐፎቻቸውን በአሜሪካ አገር ትርፍ ላይ መሠረት ባላደረገ ነገር ግን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ሙያው የሚጠይቀው ወጪ ወጥቶባቸው ታትመው ስላሉ በቀጥታ ከአሳታሚዎቹ ወይም ከሕጋዊ ወኪሎቻቸው መግዛት አንድኛው የዜግነት ግዴታ እንደሆነ በግልጽ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ በተለያየ መልኩ በርካሽና ጥራቱን ባልጠበቀ ሁኔታ እያሳተሙ ለጥቂት ትርፍ መሯሯጥና ህጋዊ ሻጭ መስሎ የራስን ኪስ ለማደለብ መሞከር አንዱ የሥነምግባር ውድቀታችንና የመክሸፋችን ምልክት ነውና ህገወጥ ሥራን አናደፋፍር፤ በገሃድ ስናይም እንቃወም፡፡ ጥቂት ብሮችን ለማትረፍ ኅሊናችንን አናሸቅጠው!
አዲሱ መጽሐፍ “መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ”እና ቀደምት የፕ/ር መስፍን መጽሐፍቶች በሚከተሉት መንገዶች ማግኘት ይቻላል፡፡
የመስፍን ወልደማርያም ብሎግ
http://mesfinwoldemariam.wordpress.com/
(617) 543-3462 (ለማንኛውም ጥያቄ ይህንን ስልክ ይደውሉ)
ESAT Store
http://ethsat.com/store/
Tenadam International Market
3817 S George Mason Drive
Falls Church, VA 22041-3763
(703) 933-6038
Dama Restaurant
1503 Columbia Pike
Arlington, VA 22204
(703) 920-3559
Rosalind’s Ethiopian Restaurant
1044 South Fairfax Avenue Los Angeles, CA 90019
(323) 936-2486
Maru Grocery
8353 Park Lane Dallas, TX 75231
(214) 373-6278
Lalibela Cultural Gift Clothing And Variety Store
2257 Massachusetts Ave, Cambridge, MA 02140
(617) 876-2259
sintayhu tesfaye says
etopyan peopil lov popel
a says
Yes Sintayhu, I agree, we do love people !
I do appreciate if people strive to bring democracy and good governance to their country, but I wonder why they go to the extent of defacing their own country! To consider an extreme example, we all hate Hitler but we don’t have problem with the Germany.
a says
(same message as above with minor correction)
Yes Sintayhu, I agree, we do love people !
I do appreciate if people strive to bring democracy and good governance to their country, but I wonder why they go to the extent of defacing their own country! To consider an extreme example, we all hate Hitler but we don’t have problem with Germany.