ቀይ-ሽብር ሲጀምር
ከደርግ ዲሞክራሲ
ከወያኔ እኩልነት……ከሰማይ ዳቦ ስንጠብቅ
ሰብዕናችን ተፍቆ
ማንነታችን ተንቆ…..ከዕምነታችን ስንርቅ
ውርደታችንን ተመልክተን፤
በቃ ማለት ካቃተን
ታስሮ መታረድ አይቀርም እንደ በግ ተጎትተን
—————–
ዘመናት አስቆጥራ
ብዙ ትውልድ ተሻግራ
መቃብር ዛፍ ሲያበቅል፤ የብሶቱ ቀን ሲርቅ
የደም አሻራ ሲጠፋ፤ የወላጅ እምባ ሲደርቅ
ያኔ ይመስለኝ ነበር ታሪክ እራሷን የምትደግም
ሕብረተ-ሰቡ ሲዘናጋ፤ ሰው ከሐዘኑ ሲያገግም
ለካ ተሳስቻለሁ!
መፃፍ፤ መናገር ሲከለከል:
ማሰር፤ ማሳደድ ሲጀመሩ
የሐሰት ዶኩሜንታሪ በቴሊቪዥን ሲሠሩ
በጋዜጣ ሲያስፈራሩ፤ በሬዲዮ ሲፎክሩ
የሰው በር እየሰበሩ
ቤት-ንብረት ሲበረብሩ
እንዲህ እያለ ነበር
ቀይ-ሽብርም ሲጀምር
Feb. 20, 2013
Yekanadaw Kebede
(Picture: washermansdog-ajnabi.blogspot.com)
netsanet says
ውይ ቀይ ሺ ብር
እንዲህ ብር ሊታፈስ
ደም ሲቀዳ ዊስኪ ሲፈስ
ሆዳአምላኩ በሞላበት
ነውር ሞቶ ተቀብሮ ብርማፈስ ከሞላ
ወንድም ወንድሙን ሲበላ
ያ ቢጎትት ያ ቢጎተት
ማን ማንን ሊያድን ?
ማን ማንን ሊያድን ?
የገደለው ባልሽ
የሞተው ወንድምሽ
ለማን ታለቅሻለሽ
የትስ ታለቅሻለሽ
ቀይሺ …ብር አዳሜ ሆነብን እንጂ ነገሩ
ሽብር አይቆይም ነበር በምድሩ!
ደም ነጥቆ ብር ቢታፈስ
ጤና አይሆን እድሜ አይሆን ክብር አይሆን
አግዚአብሄርን ከፈራን
የፍትህ አምላክ እግዚአብሔር
በነካካው እጁ አሸባሪ ያለውን
ማን አሸባሪ ማን ተሸባሪ እንደሆን
በቀብር ቀን አንዳየን
እንደተሸበረ…
ሬሳው በሰው መሃል አደረ፡፡
ለካ ሽብር እራሱ ይፈራናል!
እግዘአብሔርን ከፈራን
ዳኝነቱን እናያለን እንደአየን!