ቅኔ January 24, 2013 02:18 am by Editor 7 Comments የዘወትር የድረገጽ ጋዜጣችን ተሳታፊ የሆኑት ወዳጃችን ዱባለ፤ አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ያባታቸውን የኪነት ስራ አስባስበው ካሳተሙት መጽሕፍ ያገኘሁት የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ቅኔ ነው ብለው ገጣሚ ከሆነ ምስል ጋር የላኩልንን ግጥም ነው፡፡ እንዲህ ይነበባል፡- ጎድን ከዳቢት ስብራዳ ይገባ ነበር ለእንግዳ አያችሁት ወይ ይህን ቀን ታላቅ ታናሽ ሲሆን? Share on FacebookTweetFollow us
በለው ! says January 24, 2013 03:04 am at 3:04 am ************* ምን ብርሃን አለና ይህ ምን ቀን ነው ታላቅ ታናሽ ሲሆን ያየኸው እባክህ ጌታዬ አልነጋም ቀኑ ጭለማ ነው ድቅድቅ ጨለማ ታላቅና ታናሽ የማያሳይ ከቶ ምን አለ መበላለጥን የሚያሳይ እንደቀን ጣይ? ******************** Reply
YeKanadaw Kebede says January 24, 2013 09:05 pm at 9:05 pm ያለው፤ የደላው ሲቀብጥ ክታላቅ ታናሽ ያማርጥ ለኔ -ቢጤ ግን ላማረው ሥጋ፤ ሁሌም ሥጋ ነው Reply
ዱባለ says January 24, 2013 11:41 pm at 11:41 pm ብዙ ሰው ጠይቄ መልስ ያላገኘሁለት ቃል:: መዝገበ ቃላት ላይም ያላገኘሁት:: ቀኛዝማቸ ስብራዳ የሚል ቃል መጀመርያው ስንኝ ላይ ተጠቅመዋል:: ስብራዳ የትኛው ብልት ነው? ብልትስ ካልሆነ ምን ማለት ነው:: ለዚህ መልስ የሚስጥ ካለ በቅድምያ አመሰግናለሁ:: Reply
እስከመቼ says January 25, 2013 01:20 am at 1:20 am አቶ ደስታ ተክለ ወልድ በዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው፤ ሰብድራ፤ ከጭቅና ጋራ ያለ ኹለት የበሬ ጎድን። ሲሉ ትርጉም ሠጥተውታል። ይኼ የሚረዳ ከሆነ Reply
ዱባለ says January 25, 2013 07:57 pm at 7:57 pm በጣም አመሰግናለሁ ወንድሜ እስከመቼ!!! ከላይ ቀኝአዝማች ያልኩት ይታረምልኝ ነጋድራስ ነው የማእረግ ስማቸው:: ሰውየው ተረበኛ (ይህ ቃል አሁንም አራዳ ተብዬዎች ይጠቀሙበት ይሆን?) ነበሩ ይባላል:: አንድ ጊዜ አሉ የመኪናቸው ጎማ ተንፍሶ መንገድ ላይ ቆመው ሲያስሩ ኧንድ በጣም ወፍራም የሆኑ ወዳጃቸው ያዩያቸዋል:: እሳቸውም ሊረዷቸው ብለው መኪናቸውን ያቆሙና ና እኔ ላድርስህ ይሏቸዋል:: ነጋድራስም እሺ ይሉና ጎማውን አብሮ ቆሞ ለሚያሰራው ሰውዬ አንተ ስትጨርስህ መኪናውን ይዘህ ና እኔ በተነፋው እሄዳለሁ አሉት ይባላል:: ያንተን አላቅም እኔ ይሄን ያነበብኩ ጊዜ ጦሽ ብዬ ነው የሳኩት:: ባዶ ኪስ የማይሞላ ምስጋና ምን ያደርጋል ብዬ ነው ይቺን የመረቁልህ:: መልካም ቀን ይሁንልን!! Reply
አሥረዳው (ከፈረንሳይ) says January 26, 2013 07:51 pm at 7:51 pm ይባል ነበር ዱሮ : « እስከ ዛሬ ድረስ የሥጋ ጣ’ም ሳላቅ፤ እንዴ ይጣፍጣል ታናሽና ታላቅ :: » አሁን : በስምንተኛው ሺ እኛ ባለንበት፤ በጣም ይጣፍጣል የሰው ሥጋ መብላት፤ ለቁርስ ለምሳ ካስፈለገም ለ’ራት :: ተመስገን ፈጣሪ መቆየት ደግ ነው፤ ለማየት አበቃን ሰውን ሰው ሲበላው :: Reply
አሥረዳው (ከፈረንሳይ) says January 26, 2013 09:48 pm at 9:48 pm ይቅርታ የመጀመሪያው ቅጂ ግድፈት ስለነበረው በዚህ ይስተካከል :: ዱሮ እንዲህ ይባል ነበር: « እስከ ዛሬ ድረስ የሥጋ ጣ’ም ሳላቅ፤ እንዴት ይጣፍጣል ታናሽና ታላቅ :: » አሁን : በስምንተኛው ሺ እኛ ባለንበት፤ በጣም ይጣፍጣል የሰው ሥጋ መብላት፤ ለቁርስ ለምሳ ካስፈለገም ለ’ራት :: ተመስገን ፈጣሪ መቆየት ደግ ነው፤ ለማየት አበቃን ሰውን ሰው ሲበላው :: Reply
በለው ! says
*************
ምን ብርሃን አለና ይህ ምን ቀን ነው
ታላቅ ታናሽ ሲሆን ያየኸው
እባክህ ጌታዬ አልነጋም ቀኑ ጭለማ ነው
ድቅድቅ ጨለማ ታላቅና ታናሽ የማያሳይ
ከቶ ምን አለ መበላለጥን የሚያሳይ እንደቀን ጣይ?
********************
YeKanadaw Kebede says
ያለው፤ የደላው ሲቀብጥ
ክታላቅ ታናሽ ያማርጥ
ለኔ -ቢጤ ግን ላማረው
ሥጋ፤ ሁሌም ሥጋ ነው
ዱባለ says
ብዙ ሰው ጠይቄ መልስ ያላገኘሁለት ቃል:: መዝገበ ቃላት ላይም ያላገኘሁት:: ቀኛዝማቸ ስብራዳ የሚል ቃል መጀመርያው ስንኝ ላይ ተጠቅመዋል:: ስብራዳ የትኛው ብልት ነው? ብልትስ ካልሆነ ምን ማለት ነው:: ለዚህ መልስ የሚስጥ ካለ በቅድምያ አመሰግናለሁ::
እስከመቼ says
አቶ ደስታ ተክለ ወልድ በዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው፤
ሰብድራ፤ ከጭቅና ጋራ ያለ ኹለት የበሬ ጎድን። ሲሉ ትርጉም ሠጥተውታል።
ይኼ የሚረዳ ከሆነ
ዱባለ says
በጣም አመሰግናለሁ ወንድሜ እስከመቼ!!!
ከላይ ቀኝአዝማች ያልኩት ይታረምልኝ ነጋድራስ ነው የማእረግ ስማቸው:: ሰውየው ተረበኛ (ይህ ቃል አሁንም አራዳ ተብዬዎች ይጠቀሙበት ይሆን?) ነበሩ ይባላል:: አንድ ጊዜ አሉ የመኪናቸው ጎማ ተንፍሶ መንገድ ላይ ቆመው ሲያስሩ ኧንድ በጣም ወፍራም የሆኑ ወዳጃቸው ያዩያቸዋል:: እሳቸውም ሊረዷቸው ብለው መኪናቸውን ያቆሙና ና እኔ ላድርስህ ይሏቸዋል:: ነጋድራስም እሺ ይሉና ጎማውን አብሮ ቆሞ ለሚያሰራው ሰውዬ አንተ ስትጨርስህ መኪናውን ይዘህ ና እኔ በተነፋው እሄዳለሁ አሉት ይባላል:: ያንተን አላቅም እኔ ይሄን ያነበብኩ ጊዜ ጦሽ ብዬ ነው የሳኩት:: ባዶ ኪስ የማይሞላ ምስጋና ምን ያደርጋል ብዬ ነው ይቺን የመረቁልህ::
መልካም ቀን ይሁንልን!!
አሥረዳው (ከፈረንሳይ) says
ይባል ነበር ዱሮ :
« እስከ ዛሬ ድረስ የሥጋ ጣ’ም ሳላቅ፤
እንዴ ይጣፍጣል ታናሽና ታላቅ :: »
አሁን :
በስምንተኛው ሺ እኛ ባለንበት፤
በጣም ይጣፍጣል የሰው ሥጋ መብላት፤
ለቁርስ ለምሳ ካስፈለገም ለ’ራት ::
ተመስገን ፈጣሪ መቆየት ደግ ነው፤
ለማየት አበቃን ሰውን ሰው ሲበላው ::
አሥረዳው (ከፈረንሳይ) says
ይቅርታ የመጀመሪያው ቅጂ ግድፈት ስለነበረው በዚህ ይስተካከል ::
ዱሮ እንዲህ ይባል ነበር:
« እስከ ዛሬ ድረስ የሥጋ ጣ’ም ሳላቅ፤
እንዴት ይጣፍጣል ታናሽና ታላቅ :: »
አሁን :
በስምንተኛው ሺ እኛ ባለንበት፤
በጣም ይጣፍጣል የሰው ሥጋ መብላት፤
ለቁርስ ለምሳ ካስፈለገም ለ’ራት ::
ተመስገን ፈጣሪ መቆየት ደግ ነው፤
ለማየት አበቃን ሰውን ሰው ሲበላው ::