• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ቀባሪ ያጣው የወያኔ/ኢህአዴግ የአገዛዝ ስረአትና ባለቤት የሌላት ኢትዮጵያ

February 14, 2013 06:39 am by Editor Leave a Comment

እንደ ወያኔ/ኢህአዴግዊ ሀገርንና ትውልድን የሚያጠፋ እኩይ አመለካከትና ምግባር ይዞ ተነስቶና ተሳክቶለትም የሚገዛ ከኢትዮጵያ ውጭ በአለም ላይ ያለ ሀገርም ሆነ የሚገዛ ህዝብ የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግ የገዛ ወገኑንና ሀገሩን በጠላትነት ፈርጆ፣ ታጥቆና ተደራጅቶ የሚወጋና የሚያፈራርስ የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግዊ አገዛዝም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊንን የማጥፋቱንና የመበታተኑን ምግባር እንዲያቆም እሽሩሩ የተባለና እየተለመነ ያለ የለም።…..

በልመና ቢሆን…..

ፍትህ – እኩልነት

በልመና ቢሆን…

ነጻነት – አንድነት

በልመና ቢሆን….

ሰላምና ሕይወት፤

እመጣ ነበረ– አንች ካለሽበት

ትመጭልኝ ነበር – እኔ ካለሁበት

ዓለም ይሆን ነበር፣ የሁላችንም ቤት።

እንደ ደርግ ያለ አምባገነን መንግስት ሀገሩን በክህደትና በጥላቻ ለተሞሉ፤ እንደ ሻአቢያዊንና እንደ ወያኔያዊያን ላሉ ሀገሩን አሳልፎ የሰጠ የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግ ያሉ ተቃዋሚዎች ልፍስፍስ፣ ወኔ ቢስ፣ እርስ-በርስ የሚናቆሩና ከትላንቱ የማይማሩ፣ ሁሌም የጠላት መሳሪያ ሆነው የሚያገለግሉ ”ቦለቲከኞች” ማግኘት ይከብዳል።

አንድ ጀርመናዊ የጥንት ፈላስፋ ”መግደልም ሆነ መገደል በፍጹም አልፈልግም፤ ግን ክብሬ ከሚዋረድ ከሁለቱ አንዱን እመርጣለሁ።” ማለቱ ይነገራል። እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን ሳንታገለም፣ ሳንኖርም፣ የቁም ሞትንና የውርደት ህይወትን ”መኖር” ብለነው፤ ኢትዮጵያን የሚያክል ሀገር በባንዳ ልጆች፣ የልጅ ልጆቻቸውና በሆድ-አደር ሎሌዎች ስትፈራርስና አንጡራ ሀብቷ የባዕዳንና የወያኔዎች መቀለጃ ሲሆን እያየን አመታት አሳለፍን። ግፋ ቢል እነሱ ስራቸውን ሲሰሩ አኛ አናወራላቸዋለን። እጅግ በጣም ጥቂት በጣት የሚቆጠሩት እውነተኛ ሀገራዊ ትግል ቢጀምሩም፤ በግፈኛ ወያኔውዎች የሚደርስባቸው ግድያና እስራት አንሷቸው፤ አኛ የተለያየ ስም እንሰጣቸዋለን።

በዚህ በያዝነው ዘመን፣ ሰው ”ሰው” በመሆኑ ብቻ ተከባብሮና ተሳስቦ፤ ድንበር እያፈረሰ በአብሮነት መኖርና መበልጸግ በተቻለበት አለም፤ በኢትዮጵያ ግን ለእውነትኛ ሀገራዊ ልዕልና፣ ለህዝቦቿ አንድነተና ህልውና የሚቆም መጥፋቱ ሲታሰብ፤ የምናሳዝንና የሚታዘንልም ዜጎች ብቻ ሳንሆን፤ በእርግጥም ጤንነታችንም የሚያጠያይቅ ነው። ለዚህም ነው አቶ ገሪማ መታፈሪያ የሚከተለውን ስንኝ የቋጠሩት:: ………

”… ሁሉ በሽተኛ፣ ሁሉ ራሴን ባይ

ባሀገሬ ደህና ሰው ላይገኝ ነወይ?

ባሀገሬ ጤነኛ ላይገኝ ነወይ?…..” ።

 በአጠቃላይ በስብዕናችን፣ በመፈሳዊነታችን፣ በማንነታችን፣ በኢትዮጵያዊነታችን …….ወርደን …..ወርደን…….ወርደን……

– በአለም የመጨረሻዋ ደህ፣ተመጽዋችና ስደተኛ ህዝቦች መሆናችን አልበቃ ብሎ፤ አንድ  ቁጥር ዘረኛና አምባገነን ስርአት የምናስተናግድና ‘’ኢትዮጵያዊ አይደለንም እያሉን’’ የምንገዛ እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን።

– ገዥዎቹ ወያኔዎችና ሆድ-አደር  ሎሌዎቻቸው በአለም ላይ አንድ  ቁጥር የደሀ-ደሀ የሆነች ሀገር እየገዙ፤ ባለጸጋ ሀገሮች እንኳ’ ሊያልሙት የማይችሉትን የተደላቀቀና የተፈላሰሰ ግን የአውሬነት ኑሮ የሚኖሩባት ሀገር ኢትዮጵያችን ነች።

– ፊደል ቆጥረናልና ተምረናል የሚሉት የሀገሪቱ ዜጎች፤ ያስተማራቸውን ህዝብ ከድህነተና ከድንቁርና አውጥቶ፣ ፍትህና እኩልነት ያለበት ሀገር ለመገንባት በመታገል ፋንታ፤ ከእነ’ሱ በእውቀትም ሆነ በስብዕና ለሚያንሱ የወያኔ ቡድኖች ጉዳይ አስፈጻሚ  በመሆን፣ ወገናቸውንና ሀገራቸውን ለሆዳቸው፣ በሆዳቸው የሚሸጡ ፍጡራን እንደ አሸን የሚፈላባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች።

– ዜጋው መጠለያ ጎጆ የሚቀልስበት ቦታና ጥማድ በሬዎቹን የሚያውልበት ሽራፊ መሬት ተነፍጎት፤ የኢትዮጵያን ውድቀትና ጥፋት እንደ ማለዳ ጸሀይ ለሚናፍቁ፤ ግን እየተለመኑ ሀገር እየተቆረሰ የሚታደልባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች።

– በተለይም ወጣቱ ትውልድ በአገዛዙና በሀገሪቱ ተስፋ ከመቁረጡ የተነሳ፤ የሚበጀውን ለራሱና ለወገኑ ከመታገል ይልቅ፤ ባዕዳን’ ተስፋ በማድረግ፤ ለባህርና ለውቅያኖስ አሳ ነባሪ፣ እንዲሁም ለበርሀ አሸዋ ‘ራሱን አሳልፎ በመስጠት ትውልድ እየጠፋባት ያለች ሀገር ኢትዮጵያ ነች። በህይወት የተረፈም ለግርድናና ለሽርሙጥና ሲዳረግ፤ በሞቱት ስደተኛ ወገኖቹ የሚቀና ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው።

– የህክምና ባለሙያዎች፤ በማንኛውም መንገድ ይሁን የሰውን ልጅ ህይወት የመርዳትና የማትረፍ አላማ አድርገው በደሀው የገበሬ ገንዘብ  እንዳልተማሩና ቃለ-መሀላ እንዳልፈጸሙ ሁሉ፤ ወገናቸው ህክምና  ፍለጋ አግዳሚ ወምበር ላይ ተጋድሞ እያቃሰተ እያዩት፤ ነገር ግን የሀይል መስጫ ምግብ (ግልኮስ) መግዣ ለግዜው ሳንቲም ስሌለው ብቻ ህይወቱ እንድታልፍ ”ፍርድ’ የሚሰጣባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች።

– የሀይማኖት አባቶች እጅግ በሚዘገንና በማይታመን መልኩ በዘረኝነትና በአፍቅሮ ንዋይ ታውረው፤ ለገዥዎች ሎሌነት በማደር፤ እምነት የረከሰባትና የተናቀባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች።

– የሀገሪቱ የኪነ-ጥበብ ሰዎች፤ ንፋስ ወደ ነፈሰበት እየነፈሱ፣ የገዥዎች አፍና እጅ በመሆን፤ ክቡሩ የህሊና ሙያ ለከርስና ለጥቅማጥቅም የሚቸበቸብባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች።

– ወያኔዎች የዘሩት የዘረኝነት ዘር አፍርቶ፤ በአሁኑ ወቅት የአንድ ቤት-ቤተሰብ አባላት እንኳ’ የማይተማመኑበትና፤ ወንደሙ፣ ወንድሙን ለጥቅም አሳልፎ የሚሰጥበት ሀገር ኢትዮጵያችን ነች።

– ኢትዮጵያ… ግፈኞች፣ ወንጀልኞች፣ አምባገነኖች፣ ከሀዲዎች፣ ሆድ-አደሮች፣ ውሸታሞች፣ ሌቦች፣ ባንዳዎች፣ ሙሰኞች፣ ጠባብ መንደርተኞችና ህሊና ቢሶች በኩራት ደረታቸውን ነፍተው የሚጎሩሩባትና እንደ ሜዳ አህያ የሚፏሉሉባት፤ በተቃራኒው ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ለህሊናቸው፣ ለሀገራቸው ልዕልናና ለህዝባቸው ፍትህና እኩልነት የሚታገሉና የሚደክሙ አንገታቸውን ደፍተውና አቀርቅረው የሚሄዱባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች።………ግን ምነዋ ኢትዬጵያ…?

እንደ ይሁዳ ከዱ ልጆችሽ ሸፈጡ

እንደ ኤሳው ሆኑ ቡክርናቸውን ሸጡ

በመታመን ፋንታ ኑፋቄን መረጡ።

እንደ ባህር አሸዋ – እንደ ሰማይ ከዋከብት

ምነዋ ኢትዬጵያ… በዛብሽ ጠላት?……

——–//———-

ፊልጶስ /e-mail: philiposmw@gmail.com

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Literature

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule