ሚስጢሩ አሁን በሀይለኛ ሂደት ላይ ወቷል። እርስዎም የውለታ ምስጋናን፤የሚፈልጉትን ነገር በዓይነ ህሊና አስቀድሞ ማየትን፤የተግባር ሀይልን ሂደቶች የሚረዱበት ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ማለት ነው።ለመሆኑ አስቀድመው ይሄን ሁኔታ የተሸጋገሩ ምን ይላሉ? ያሁኑ ማንነታችን ያለፈው አመለካከታችን ውጤት ነው። ቡድሃ የየቀኑ ምስጋናህ ፀጋ ወደ አንተ የሚመጣበት ማስተላለፊያ ቀዳዳ ነው ዋላስ ዋትልስ መተንበይ ሁሉንም ነገር ነው።የህይወት መጻኢ መስህቦች ቅድመ እይታ ነው። አልበርት አንስታይን ሀይለኛው ሂደት የምትፈልገውን አጥብቀህ መጠበቅ ሊረዳህ ይችላል ፍላጎት እንዳይርቅ ስትተኛም ሆነ ጠዋት ስትነሳ በያንዳንዱ ነገር ማመስገን አትርሳ በጅህ ባለ ነገር ማመስገን ስትጀምር መንገድ ትፈጥራለህ ሌላ ለመጨመር የምትፈልገውን በዓይነ ህሊና አስቀድመህ አይተህ አስተካክለውና ማግኘትህን … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
Literature
ጽፈኪን
እኔና አንቺ … ፩
መቼም እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን ይሄው ደግሞ ተሰደንም ልንስማማ አልደፈርንም። ሳትሰሚኝ አጣጥመሽ እኔም ያንቺን ሳላውቅልሽ መግባባቱ እንዳቃተን በየአቅጣጫው ተበታትነን ስንፋተግ ዕድሜ ገፋን። እውነታውን ስንሸሸው፣ መወያየት ስንፈራ ቀለብ ሆነን ሀሜት ጉራ። በይ ተይው ግዴለም፣ ድሮውንም ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን። ለነገሩ ትተነውስ ወዴት ልንደርስ ግደለሽም እኛው ደፍረን እንዋቀስ የዕለት የዕለቱን ትተነው ዘላቂውን እንመርምረው። የጋራ ችግራችንን ተነጋግረን በጋራ እንፈታለን እያልን በአፍ ብቻ ስንወተውት ከልብ አጣን ስምምነት። ስለሀገሬ ስለሀገርሽ አንቺም ስሚኝ፣ እኔም ልስማሽ! የማተያት፤ የማልተዋት የጋራችን አንድ ሀገር ናት። ታዲያ … [Read more...] about እኔና አንቺ … ፩
ሀገር ማለት
በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ አስቀድሞ ደራሲ በዓሉ ግርማ በኋላም ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ግጥሞቻቸውን ጽፈው ነበር፡፡ ሌላም የጻፈ ይኖራል፡፡ ነገር ግን እነኝህ የሥነ-ጽሑፍ ሰዎች ግጥሞቻቸውን ሲጽፉ የተቆነጸለ ወይም የተሳሳተ ትርጉም ሊያሰጥ በማያስችል ሁኔታ ግጥሞቻቸውን ባለመጻፋቸው እንደምገምተው እነሱም ሊሉ ባልፈለጉት መንገድ ተተርጉሞ የቅጥረኞች መጠቀሚያ እስከመሆን ድረስ በቃና ሕዝብን ለማደናገሪያ አገለገለ፡፡ ከሕዝቡ ጥቂት የማይባል ወገንም በመወናበድ ይሄንን የተሳሳተ ትርጉም ይዞ ማንጸባረቅ ያዘ፡፡ ይህም መሆኑ ሀገር በሕዝብ ልብ ውስጥ የነበራት ቦታና ትርጉም ከመዛባቱም ባሻገር በወደፊት የሀገር ህልውና ላይ ከባድ አደጋ የጋረጠ ሆኖ ቁጭ አለ፡፡ እናም እንደዜጋ አሳሰበኝና ይሄንን የተሳሳተ ትርጉም ለማረም የሀገርን ትርጉም ሳይቆነጸል ሳይጎነጠል ለማስፈር ተገደድኩና ይህችን ግጥም … [Read more...] about ሀገር ማለት
እንኳን ደስ አለን ለሁላችን!!
ይገርማቹሀል ይሄንንና እዚህ ላይ አሁን ለእናንተ ያላቀርብኩትን በግእዝ (አማርኛ) ፊደል ቁጥርና የቁጥር ስሞች መቸ፣ የት፣ እንዴት፣ ተፈጠሩ? የሚለውንና ባጠቃላይ በቋንቋችን ላሉ ሌሎች ምላሽ ያልነበራቸው ጉዳዮችን ምላሽ የሚሰጥ የጥናትና ምርምር ሥራ ከሐሳብ ወደ ተግባራዊ ሥራ ተሸጋግሬ መሥራት የጀመርኩት ዐሥራዎቹ መገባደጃ የዕድሜ ክልል እያለሁ ጀምሬ ነበር፡፡ ከብዙ ዓመታት ድካምና ጥረት በኋላም ሥራውን ጨረስኩ ባልኩ ጊዜ ምቹ ሁኔታና ጊዜ ይመጣል ብየ ብጠብቅ ብጠብቅ ቀጠሮ ያልያሳዘኝ ነገር መቅረቱ አሳሰበኝና ከሁለት ዓመታት ወዲህ ጀምሬ ለአንዳንድ የመገናኛ ብዙኃንና ዕውቅና ለሚሰጡ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ ተቋማት አቀረብኩት፡፡ ታዲያ እዚያ ያሉት ሰዎች ፊደላት ካልተነቀነሱ ሞተን እንገኛለን የሚሉና ከዚያም አልፈው ወደ 91 የሚደርሱ ሆሄያትን አስወግደው በተቋም ስም መጽሐፍ … [Read more...] about እንኳን ደስ አለን ለሁላችን!!
ስምና ገመድ!!
በተለያዩ ምክንያቶች ለረጅም ጊዜ አቋርጠነው የነበረውን የግጥም ጨዋታ እንደገና ጀምረናል፡፡ ከዚህ በፊት እናደርገው እንደነበረው አንባቢያን ይህንን ግጥም አንብባችሁ አስተያየታችሁን በግጥም እንድትሰጡና ጨዋታውን እንድታደምቁት እንጋብዛለን፡፡ ለዛሬ የመረጥነውን ግጥም ከነፎቶግራፉ ያገኘነው ከደመቀ ከበደ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው፡፡ገጣሚ ደመቀ ከበደን ለግጥሙና ለፎቶው ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ስምና ገመድ!! አዝማሪ እንዲህ አለ፤ "ሰው ሰበበኛ ነው - ምክንያት አያጣም እንኳን ዝናብ ዘንቦ - ሲዳምን አይወጣም፤" እኔ ግን እላለሁ፤ አተተ በተተ ወዘተ ወዘተ በሚል አርቲ ቡርቲ - ዕድሜ ከምንጨርስ ህይወት ከምናጣ ፋይዳ ላለው ነገር - ቁልቁለት እንውረድ አቀበት እንውጣ፤ ያኔ አላስወርድ ካለህ - ወይም አላስወጣ ማሰሪያ ከሆነህ - አሊያም ጋሬጣ ያኔ አይንህን … [Read more...] about ስምና ገመድ!!
The Secret (ሚስጢሩ…)
ስለተከሰተው ሚስጢርና የሚስጢሩን ቀላል መደረግ አሁን የሚጠይቁኝ አይመስለኝም።ይልቁንም አጠቃቀሙ እንዴት ነው? ይሉኝ ይሆናል።ለዚህ በክፍል ሶስት ጽሁፌ መልስ ይዣለሁ።ከዛ በፊት ግን ታላቁ መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላል?የሚስጢሩ ተጠቃሚዎችስ ምን ይነግሩናል?ይሄን አንብበው ወደ ሚስጢሩ አጠቃቀም ይሻገሩ። "አምናችሁም፤ በፀሎት፤ የምትለምኑትን፤ ሁሉ ትቀበላላችሁ።" ማቴዎስ፤ ፳፩-፳፪ "የፀለያችሁትን፤ የለመናችሁትንም፤ እንዳገኛችሁት እመኑ። ይሆንላችሁማል።” ማርቆስ፤ ፲፩-፳፬ "ነገሮች ሁሉ፤ ይለወጡልህ ዘንድ ዓለም እንደገና ራሷን ታዘጋጃለች።” ዶ/ር ጆ ቫይታል "የመጀመሪያው መነሻህ ታማኒነት ይሁን።የደረጃውን መጨረሻ አጠቃለህ ማየት አያስፈልግህም።ዝም ብለህ ወደ መጀመሪያው ደረጃ ውጣ።" ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ የሚስጢሩ አጠቃቀም የምትፈልገውን ለመፍጠር … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
በሁሉም አትሌቶቻችን ኮርተናል!
የኢትዮጵያ አትሌቶች በ14ኛው የዓለም አትሌክቲክስ ሻምፒዮን ውድድር አስደናቂ ውጤት አስመዘገበዋል ! አትሌቶቻችን 1 ወርቅ፣ 2 ብር፤ እና 1 ነሃስ ያገኙ ሲሆን እውነትም አረንጓዴው ጎርፍ የሚለውን ስማቸውን አድሰዋል። በውጤቱም በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን፤ 2ኛ ለሌሳ ደሲሳ, 3ኛ ታደሰ ቶላ, 4ኛ ጸጋዬ ከበደ እና 8ኛ የማነ ጸጋዬ የወጡ ሲሆን፤ በሴቶች 5000 ሜትር ሩጫ ደግሞ፤ 1ኛ መሰረት ደፋር፣ 3ኛ አልማዝ አያና 5ኛ ብዙ ድሪባ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በአጠቃላይ በዛሬው እለት ብቻ 1 ወርቅ ፣ 2 ብር እና 1 ነሀስ በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን በመጨመር ኢትዮጵያ ከራሺያ፤ ከአሜሪካ፤ ከጃማይካ እና ከኬንያ በመቀጠል በ6ኛነት በ3 ወርቅ፣ 3 ብር እና 4 ነሀስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኝት የኢትዮጵያ ባንዲራ በሞስኮ ስታዲዮም ከፍ ብሎ እንዲወለበለብ ላደርጉት ብርቅዬ አትሌቶቻችን … [Read more...] about በሁሉም አትሌቶቻችን ኮርተናል!
The secret (ሚስጢሩ…)
የግጥም አፃፃፍ ዘዬን ያመጡ ነፍሳቸው ትባረክ።”ሚስጢሩ ቀላል ተደረገ” የሚለውን የሚስጢሩን ሁለተኛ ክፍል እነሆ! በአጭር መስመሮች ግጥም ማጠቃለል ቻልኩ።የዚህን ስራ የመጀመሪያ ክፍል ያነበቡ አስተያየት ሰጭዎች ”አቀራረብህ መጽሐፉን ላነበቡ ይገባ እንደሆን እንጂ ለሌላው አንባቢ ግልጽ ሊሆንለት አይችልም!” አሉኝ።ለትሁት አስተያየታቸው ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው። በዚህ ምክንያት ግን ስራውን ልገታው አልፈለኩም። ቀጣዮቹ ክፍሎች የአንባቢን የመረዳት ሀይል ይጨምራሉ የሚል ግምቴ በልጦ ስለታየኝ ቀጠልኩ። ሚስጢሩ ቀላል ተደረገ ህገ ተፈጥሮ ነው ስበት አይወግንም ለአንደኛው ከልክሎ ለሌላው አይፈቅድም ነገር ግን ጉዳዩን ወደ ተሞክሮህ ማምጣት ይገባሃል አንተ ራስህ ስበህ መጥፎ እየተሰማህ መልካም አስተሳሰብ ሊኖርህ አይችልም ይሄንን ተገንዘብ እንዳተ አስተሳሰብ ተጓዳኝ … [Read more...] about The secret (ሚስጢሩ…)
ሞሄ አሳካህው! ዛሬም ዳግም ኮራን!
በሞስኮ 800 ሜትር ወርቅ ባለቤት በመሆን አገሩን ላኮራው መሃመድ አማን፤ ነቢዩ ሲራክ በዚህ ግጥም ኩራቱን ገልጾዋል፡፡ (ግጥሙን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ሞሄ አሳካህው! ዛሬም ዳግም ኮራን!
በጥሩየ ዳግም ኮራን!
በዚህ ዓመቱ የዓለም አትሌቲክስ ውድድር በ10,000 ሜትር ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ያስገኘችውና በጃፓን በተደረገው የ1999ኙ የዓለም አትሌቲክስ የ10,000ሜትር ወርቅ ተሸላሚ ጥሩነሽ ዲባባ:: ትላንት የተደረገውን ውድድር ሲዘግቡ የነበሩት commentators የጥሩነሽን አንጸባራቂ ድል በሚከተለው ሁኔታ ገልጸውታል:: በመጨረሻው ዙር ተፎካካሪዎችዋን ጥሳ ስትወጣ:- "(Tirunesh Dibaba) the empress Ethiopian" ድል ከተቀዳጀች በኋላ፡- "Tirunesh Dibaba confirmed her status as one of the greatest female distant runners in history." ይህንን የጥሩነሽ ድል በአገራችን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማጣመር ነቢዩ ሲራክ “በጥሩየ ዳግም ኮራን” በማለት ይህንን ግጥም አቅርቧል፡፡ (ግጥሙን ለማንበብ እዚህ … [Read more...] about በጥሩየ ዳግም ኮራን!