ያልታየን አሟሟት- ባንተ አይቼ ሞትህን በቁሜ ሞቼ ሲገድሉህ የተሰበረ ቅስሜ እስካሁን አልጠገነም ህመሜ ሲገሉሽ ሞቼ ነው የከረምኩ ከስቃይሽ እኔም አልተረፍኩ ይህንን የናንተን አበሳ ልጽፈው ብዬ ብነሳ ሀዘን ዘልቆ ከገባ- አጥንት ድረስ ለካስ ቃላትም- የአንጀት አያደርስ እዬዬም ሲዳላ ነው ይባላል እንባም ስቃይ ሲከብደው- ለካስ ይደርቃል ደርቆ ይቅር- ድሮስ ምን ሊጠቅም እንባ ቃላትም በኖ ይጥፋ- ያሻው ቦታ ሄዶ ይግባ ሁለቱስ ምን አባታቸው ሊያደርጉልኝ ሞታችሁን ብረሳ ግን- ያቺ ቀናችሁ አትርሳኝ። ************** በሳውዲ ዐረቢያ አለምንም ጥፋታቸው ለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ መታሰቢያ ይሁን … [Read more...] about ቀናችሁ አትርሳኝ!
Literature
ጽፈኪን
የነፍስ ስደተኞች (the immigrants of survival)
ባገሩ የሚኮራ ፤ ሀገሩን አፍቃሪ ለወገን ሟች ስፍሱፍ ፤ አብሮነት ዘማሪ የነፍስ ስደተኛ ፤ እውነት አስመስካሪ የሀገሩ ነገር ፤ የወገኑ እጣ ሁሌ የሚያስጨንቀው ፤ ሲበዛ ግፍ ጣጣ ስለተገለለ ፤ አማራጭ ስላጣ እኛን ካልሆንክ ተብሎ ፤ ሕሊናው ተሸጣ ደሞ ስለተገፋ ፤ ታይቶ እንደ ባላንጣ አላፈናፍን ተብሎ ፤ ጅቡ እየተቆጣ አላቃምስ ተብሎ ፤ በራብ እየተቀጣ ወገን ሲለይበት ፤ ሆኖ ዘር መረጣ ቢብሰው ተነሣ ፤ ለስደት ጎረፈ ከሞት ጋር ተፋጦ ፤ ሞትን እያለፈ ግፍ እየተጋተ ፤ እየተቀሰፈ ገና ባልጸናለት ፤ በጨቅላ ትከሻ ስንት ስቃይ ዐየ ፤ የጣር መጨረሻ ወገኑን እያጣ ፤ የዓሣ ሲሳይ ሆኖ በአራዊት ተበልቶ ፤ በድንገት ታድኖ ስለተደፈረ ፤ እራሱን ኮንኖ በራብ በውኃ ጥም ፤ እየቀረ ደብኖ በኢሰብአዊ … [Read more...] about የነፍስ ስደተኞች (the immigrants of survival)
ሰቆቃወ ወገን!
ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about ሰቆቃወ ወገን!
The Secret (ሚስጢሩ…)
ሚስጢሩ ወደኛ እየቀረበ ይሆን? የሚስጢሩን መጽሃፍ እያሳጠርኩ በመጻፍ ላይ እያለሁ ሚስጢሩን የሚአጠናክር ነገር ገጠመኝ። ከጓደኛዬ ጋር አልፈን አልፈን ውሃ የምንጎነጭባት ቤት አለች። እንደወትሮው በዛው ቤት ተገኝተናል። አንዲት ወጣት ስዊድናዊት ልታስተናግደን መጣች። ለጓደኛዬ የሞቀ ሰላምታ ሰጠችው። ስትስቅ ጉንጭና ጉንጮቿ ላይ የሚወጡት ጎድጓዳ ምልክቶች አይን ይስባሉ። ‹‹ባለፈው ጊዜ ስራ ለመቀጠር አስበሽ ያነጋገርኩሽ አይደለሽ?» አላት «አዎን! ተቀጠርኩ በጣም አመሰግናለሁ» «እኔ ምንም ያደረኩልሽ ነገር እኮ የለም» «አንተ ሄደሽ ባለቤቱን ተይቂው ባትለኝ አልጠይቀውም ነበር። ስለጠየኩት ተቀጠርኩ። በድጋሚ አመሰግናለሁ»። ፈገግታዋን ከጎድጓዳ ጉንጮቿ የሚረጭ ይመስላል። ተለየችን «ምንድነው ነገሩ? ስራ አስቀጣሪ ሆንክ እንዴ?» ጠየኩ ባለፈው ሰሞን እዚህ መጥቼ… ይቺ … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
ወገኔ በከንቱ
እዩት በየቦታው የሚታደገው አጥቶ እንዲያው ሲንከራተት ከሀገሩ ወጥቶ ወይ አላለፈለት ወይ እፎይ አላለ ሁሌ በባርነት እንዲሁ እንደቆዘመ ዘመናዊ ለማኝ አስጠጉኝ ባይ ሆነ መገፋቱ ሳያንስ መገደሉ ባሰ ። ባርነት ባአረብ አገር እስር በዐገር ቤት ስደት ካገር ውጭ ችግር በራስ አገር እርዛት አና እስር ሆኖል የብሶት መንደር ። ወገን አልባው ወገን ጠባቂ አልባው ግልገል መንጋው ተበተነ ዋይታው ለኛ ሆነ ገዳዩም ጠያቂ አጣ ስቃዩም ቀጠለ ። አቤት ፍርጃ ለዛውም ጠያቂ ያጣ ምን ይሆን ሚስጥሩ እንዲህ የመሆኑ? ማብቂያውስ መቸ ነው እንግልት ስደቱ አገር ሰላም ሆኖ ሰርቶ እሚኖርበት ሁሉም አንደቤቱ። መንግስት ምን አገባኝ ጆሮ ዳባ ልበስ ካለ ለህዝብ ለወገኑ ላገሩ ካልቆመ የወገን ደም እንደቀለም መንገድ ላይ ሲዘራ በባእዳን እጂ ወገን ሲሆን መቀለጃ ቆሞ … [Read more...] about ወገኔ በከንቱ
“ሁለቱም ባዶዎች ነበሩ!”
እ’ስራና ቅል ... አፈጣጠራቸው፣ ቢሆንም ለየቅል፤ እንደ አቅማቸው፣ ሠርተው በሀሳብ - ተግባር፣ ተግባብተው፤ ሰላም አግኝተው፣ አንድነት ይኖሩ ነበር፣ በአንድ ቤት። በፍቅራቸው፣ የሚቀናው ዱባ ግን፣ ጉረቤታቸው፤ ያሴር ነበር ሴራ፣ የሚያሥር ይሸርብ ነበር ነገር፣ የሚያደናግር፤ ያጠምድ ነበር፣ ወጥመድ ባረፉበት ቤት፣ ሳይቀር በመንገድ። እ’ሰራን ሲያገኘው፣ ብሎ ጎንበስ - ቀና የሰላምታ አይነት፣ ያዥጎደጉድና፤ በማር የተቀባ፣ የመርዝ ቃላት ይነግረው ነበረ፣ መስሎ ተቆርቅሪ፣ ለሱ ያዘነለት። ቅልንም ሲያገኘው ወይም ቤቱ ሄዶ ከአስረደው በኋላ፣ እንደሚፈልግው በፍቅሩ ተገዶ፤ ምክር ነው እያለ፣ ነገር ይነግረዋል በማያውቀው ጉዳይ፣ ደሙን ያፈለዋል። ከለ'ታት አንድ ቀን፣ ሥራ በፈቱበት በነገር ተይዘው፣ ''በተሰለቡበት''፤ እ’ስራ ተክዞ፣ … [Read more...] about “ሁለቱም ባዶዎች ነበሩ!”
እኔና አንቺ…፪
መቼም እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን የኛ ብለን ክብር ሰጥተን ያመነው ሰው ደ’ሞ ከዳን። ይሄን ሰማሁ ይሄውልሽ አንቺም ሰሚው አይቅርብሽ እንደው ቢገርመኝ እንጂ ነገሩ፥ይሄማ ምኑ ይወራል የኛ ያሉት ሲከዳ፥ቃሉ ለአፍ ይመራል ብቻ ምን ይደረግ? ”ውሻ በቀደደው…” ይባል የል የሱስ መክደት ምን ይደንቃል? እንደው ግን ለነገሩ፤ እየገደሉ እያያቸው በደም ተጨማልቆ እጃቸው ከነሱ ጋር አብሮ እየደለቀ ከበሮ የተለጠፈው ውስጣቸው ምን አግኝቶ ምን አጥቶ ነው? በምኑስ ላይ ምን ሊጨምር? መች አነሰው? ንዋይ ክብር በይ ተይው ግድ የለም፤ መቼም-እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን። እንግዲህ ካልሰማሽም ስሚ፤ ከሰማሽም-ቻልአድርጊው እኛን ያልከዳን ማን አለ? የበደለን … [Read more...] about እኔና አንቺ…፪
”ዛሬም ታለቅሳለች!”
''ዛሬም ታለቅሳለች!'' ትላ’ትናም - ዛሬም ቁማም - ተቀምጣም በውኗም - በህልሟም፤ እምባ እያዘነበች ደም እያፈሰሰች፤ ሁሉንም እያየች ዛሬም ታለቅሳለች።……. ‘’ረስታ - ተረስታ በራሷ ላይ ዘግታ፤ ከጥዋት እስከማታ እንቅልፏን ተኝታ’’። ተብሎ ተወርቶባት ለብዙ ዘመናት ታሪክ ተጽፎባት፤……. እሷ ግን፣ እሷ ናት ዓለም የሚያያት፤ እምባ እያዘነበች እህህ…… ትላለች ትንሰቀሰቃለች፤ ሁሉንም እያየች ዛሬም ታለቅሳለች።……… ተማፅኖ ተማሎ ተገዝቶ ምሎ ገ’ሎና አስገድሎ ፤ ‘’ለ’ርሀብ - ‘ርዛትሽ ለልመና - ፅናትሽ ለፍትህ - እጦትሽ ለሰላም - ለፍቅርሽ፤ መድሀኒት አውቃለሁ እኔ እሻልሻለሁ’’፤ ብሎ የሚገባው እምባዋን ሊጠርገው መፍሰሱን ሊያቆመው፤...... ጭራሽ አብሶባት ሀዘን ደራርቦባት፤ ማቁን አስለብሶ አመድ … [Read more...] about ”ዛሬም ታለቅሳለች!”
ምሁር (intellectual)
ከሰው ወይ ከአምላክ ፤ ተምሮ የረቀቀ ቀለም ብዙ የጠጣ ፤ ከባሕር እየጠለቀ ተለይቶ የወጣ ፤ በርቶለት የራቀ አንጥሮ አብጠርጥሮ ፤ መርምሮ የላቀ በአዎንታዊ እሴቶች ፤ ጌጦ ያሸበረቀ ደግነትን ከሸር ፤ ልማትን ከጥፋት ፤ ለይቶ የጠበቀ የሚያሰነካክለውን ፤ የት እንዴት እንደሆን ፤ ነቅቶ የጠነቀቀ ነበር ምሁር ማለት ፤ መሻል መብለጣቸውን ፤ አጣጥሞ ያወቀ አዬ ድንቄም አያ ii ፤ ምሁሩ ሊቅ ዐዋቂ የሀገር አደራ ጠባቂ በአረጋዊያን ተመራቂ በታናናሾቹ ተደናቂ ትውልድን አናጭ አምጣቂ አብእናን ቀራጭ አላቂ በዕውቀት በጥበብ አርቃቂ ለችግር መፍትሔን አፍላቂ የሥልጣኔን ብርሃን ፈንጣቂ ለሀገር ለወገን መከታ ለትውልድ ተስፋ አለኝታ መመኪያ ደጀን ስጦታ አይደለም ? ትርጉሙ ሲፈታ ? አዪ … እ !! ድንቄም ዐዋቂ የመጠቀ የእንስቷን ተስፋ የደመቀ በወላጅ … [Read more...] about ምሁር (intellectual)
ለቅሶ እንድረስ
ቀብር ውጡ ወዳጆቼ - ጌታ ብእር አረፈ ደራሲው ሰው ሆነ - ፈጣሪነቱን ተገፈፈ፤ በመጋኛ ተቦትልኮ - በዘር ሀረግ ተጠርንፎ ጌታ ብእር ተሻረ - ካባ ማእረጉን ተገፎ የት ይደርሳል ያልነው ጎበዝ - ተስፋ ያልነው ሽል ጨንግፎ፤ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለቅሶ እንድረስ