እንደማያልፍ የለም November 19, 2013 07:33 am by Editor 1 Comment አዎ፤ የኔም እምባ ፈሷል እምነቴ ደፍርሷል ሰበዕናየ አንሷል ምክንያት ፍለጋ – መፍትሄ ፍለጋ ቀኑ እስከሚጨልም – ሌሊቱ እስቲነጋ ብቆርጥ ብቀጥል – ባነሳ ብጥለው ዘላለም ሆነብኝ – ማለቂያ የሌለው ሕመምሽ አሞኛል ድካምሽ ደክሞኛል እምባሽን ለመጥረግ – አቅም በማጣቴ ሕሊናየ ቆስሏል – ተቃጥሏል አንጀቴ እና….ጠንክሪ እህት ዓለም ይሄም ቀን ይረሳል – እንደማያልፍ የለም Share on FacebookTweetFollow us
በለው! says November 25, 2013 05:08 am at 5:08 am ************************************** “ይሁን ስንል.. ያልፋል ስንል..ይሻላል እያልን ስቃይ መከራን አባብለን በመቻቻል ይቻላል ተንበርክከን… ማን ተሸካሚ? ማን ጫኝና አስጫኝ? እንደሆነም ሳይታወቀን ቀን ቀንን እየወለደው ዐመታት አስቆጠርን እንደዋዛ ለመድነው ንቀትና ውርደትን ተንበርከን ጭነውብን ሰቅለነው ተቀምጠን ተደላድለው ጋለቡብን አሁን ማን ያውርድልን !? ጫናው ቢበዛ በገር ውርደት ሁለተኛ ዜጋ መሆን ይሻላል ብለን እርቀን ልንሞት ቤታችንን ጥለን ጠፋን የዱላም ገድ ከጭቆናም ዘረኝነት አሁንም ገረፉን:: ዓረብ ከፋ ወገኔን እጅ እግሩን አንቀቱን በሜንጫ ቀላው ስብዕናውን ገፎ ውሻ አድርጎ አዋርዶ ገደለው ! መንግስት ተብዬውማ ምን ቸግሮት አተረፈበት በቋንቋ በባሕል በቀለም በሃይማኖት በታትኖት የሰውን ልጅ ተናጋሪ እንስሳ በክልል አጥሮት ብቻውን ነግዶ አትራፊ ባለሀብት አውራ አርገውት ብሔራቸውን ነገዳቸውን ለገንዘብ ሸጠውለት ዙሪያውን ከበው ሕዝባቸውን በልተው እያባሉት አሁን በህወአት/ወያኔ/ሻቢያ እያመካኙ ከንፈር የሚመጡት ጎበዝ ንቃ ያስጠቃህ ያንተው ብሄር ዘመድ እንደሆነ እወቅበት !። ሌላው ቢቀር እንደምን ከበደ እንቢኝ ማለት? ************ እረ ጎበዝ ተዋረድን ረከስን ርሃብም ስደትም በእኛ ላይ ምንኛ አፍዝ አደንግዝ አምክን ነው የዚያ..የሞተ ራዕይ? የጠፋበት አንድ ጀግና ቆራጥ ዜግነት ዳርድንበር ሰንደቅን የሚያይ ሁሉም ጆሮውን ቀስሮ ደነቆረ ላይሰማ?ዓይኑን አፍጥቶ ታወረ ላያይ? እውነት ነው ህወአትሻቢያ ቅጥረኛ ባንዳ ሆድ-አደር፣ አድርባይ በጣም ሀፍረት ነው ቅሌት ይህ ሁሉ ምሁር ካድሬ በበዛበት ከዓረብ አብሮ ዜጋን በሕግ መሸጥ የተቃወመን መደብደብ ማገት የፓርቲያቸው ማኒፌስቶ የብሔር ብሄረሰብ ሕገመንግስት የሀገር የህዝብ ማስከበሪያ ወይንስ የኢንቨስተር መብት የአባቶችን አደራ የበላ የሚያወርሰው ምንም የሌለው ጣት መቀሰር፣ መጠላለፍ፣ መወነጃጀል፣መነጣጠል ለጅብ ነው እደግመዋለሁ ሀዘን ይብቃና ትውልዱን ንቃ በቃኝ በል በለው!። **************** በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ በለው! Reply
**************************************
“ይሁን ስንል.. ያልፋል ስንል..ይሻላል እያልን
ስቃይ መከራን አባብለን በመቻቻል ይቻላል ተንበርክከን…
ማን ተሸካሚ? ማን ጫኝና አስጫኝ? እንደሆነም ሳይታወቀን
ቀን ቀንን እየወለደው ዐመታት አስቆጠርን
እንደዋዛ ለመድነው ንቀትና ውርደትን
ተንበርከን ጭነውብን ሰቅለነው ተቀምጠን
ተደላድለው ጋለቡብን አሁን ማን ያውርድልን !?
ጫናው ቢበዛ በገር ውርደት ሁለተኛ ዜጋ መሆን
ይሻላል ብለን እርቀን ልንሞት ቤታችንን ጥለን ጠፋን
የዱላም ገድ ከጭቆናም ዘረኝነት አሁንም ገረፉን::
ዓረብ ከፋ ወገኔን እጅ እግሩን አንቀቱን በሜንጫ ቀላው
ስብዕናውን ገፎ ውሻ አድርጎ አዋርዶ ገደለው !
መንግስት ተብዬውማ ምን ቸግሮት አተረፈበት
በቋንቋ በባሕል በቀለም በሃይማኖት በታትኖት
የሰውን ልጅ ተናጋሪ እንስሳ በክልል አጥሮት
ብቻውን ነግዶ አትራፊ ባለሀብት አውራ አርገውት
ብሔራቸውን ነገዳቸውን ለገንዘብ ሸጠውለት
ዙሪያውን ከበው ሕዝባቸውን በልተው እያባሉት
አሁን በህወአት/ወያኔ/ሻቢያ እያመካኙ ከንፈር የሚመጡት
ጎበዝ ንቃ ያስጠቃህ ያንተው ብሄር ዘመድ እንደሆነ እወቅበት !።
ሌላው ቢቀር እንደምን ከበደ እንቢኝ ማለት?
************
እረ ጎበዝ ተዋረድን ረከስን ርሃብም ስደትም በእኛ ላይ
ምንኛ አፍዝ አደንግዝ አምክን ነው የዚያ..የሞተ ራዕይ?
የጠፋበት አንድ ጀግና ቆራጥ ዜግነት ዳርድንበር ሰንደቅን የሚያይ
ሁሉም ጆሮውን ቀስሮ ደነቆረ ላይሰማ?ዓይኑን አፍጥቶ ታወረ ላያይ?
እውነት ነው ህወአትሻቢያ ቅጥረኛ ባንዳ ሆድ-አደር፣ አድርባይ
በጣም ሀፍረት ነው ቅሌት ይህ ሁሉ ምሁር ካድሬ በበዛበት
ከዓረብ አብሮ ዜጋን በሕግ መሸጥ የተቃወመን መደብደብ ማገት
የፓርቲያቸው ማኒፌስቶ የብሔር ብሄረሰብ ሕገመንግስት
የሀገር የህዝብ ማስከበሪያ ወይንስ የኢንቨስተር መብት
የአባቶችን አደራ የበላ የሚያወርሰው ምንም የሌለው
ጣት መቀሰር፣ መጠላለፍ፣ መወነጃጀል፣መነጣጠል ለጅብ ነው
እደግመዋለሁ ሀዘን ይብቃና ትውልዱን ንቃ በቃኝ በል በለው!።
****************
በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ በለው!