ያልታየን አሟሟት- ባንተ አይቼ
ሞትህን በቁሜ ሞቼ
ሲገድሉህ የተሰበረ ቅስሜ
እስካሁን አልጠገነም ህመሜ
ሲገሉሽ ሞቼ ነው የከረምኩ
ከስቃይሽ እኔም አልተረፍኩ
ይህንን የናንተን አበሳ
ልጽፈው ብዬ ብነሳ
ሀዘን ዘልቆ ከገባ- አጥንት ድረስ
ለካስ ቃላትም- የአንጀት አያደርስ
እዬዬም ሲዳላ ነው ይባላል
እንባም ስቃይ ሲከብደው- ለካስ ይደርቃል
ደርቆ ይቅር- ድሮስ ምን ሊጠቅም እንባ
ቃላትም በኖ ይጥፋ- ያሻው ቦታ ሄዶ ይግባ
ሁለቱስ ምን አባታቸው ሊያደርጉልኝ
ሞታችሁን ብረሳ ግን- ያቺ ቀናችሁ አትርሳኝ።
**************
በሳውዲ ዐረቢያ አለምንም ጥፋታቸው ለተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ መታሰቢያ ይሁን
በለው! says
************************
መለያታችን ሳያንሰን መከፋፈልን ጨምረን
መተባባር መፋቀርን አብሮ መኖርን ጠልተን
ሁላችን በእየፊናችን ተበታትነን መመለስ አቅቶን
ጠፋን አዕምሯችን እስክንስት በተናጠል ሞትን
ለሕሙማን ብርታት ለሞቱትም ምሕረት ይስጥልን።
አቤት ግዜ አቤት ዘመን የሰው ልጅ
ወገኔ ደሙ እንደገደል ውሃ በሰው ደጅ
ዜግነት ረክሶ ሀገር ሰንደቅ ተዋርዶ
በአይናችን ያየነውን ደግመን ሰማን መርዶ
ለመሆኑ አስከመቼ? ንቀትና ቅሌት ተለምዶ !
ምነው ትውልዱ ዝም አለ ወኔውን ማን በላው
የራሱ ሀገር፣ ህዘብ፣ አስረክሶ የባዕድ ገንዘብ ገዛው?
በወገኑ ስቃይ ዋይታ የሚጫወት የሚሮጥ
በወገኑ ስቃይ የሚደሰት አጅ እግር አንገት ሲቆረጥ!
አግዚዎ ማሕረነ ለጻድቃን ለጀግኖቻችን
ዳር ድንበር ሰንደቅ ባህልና ሀገር ላወረሱን
ተከብረው አስከብረው እነሱስ አርፈው ነው ያሸለቡት
እኛ አፍጥጠን ማነነታችንን ቅርሳችንን ሸጡት!!
የባዕድ ጉዳይ አሰፈፃሚ የሀገር ውሰጥ ቅኝ ግዛት!
በብድር በልመና ሀገርና ሕዝብ በመሸጥ የለም ዕድገት
እባካችሁ ትውልዱን ንቃ በሉት ማፈሪያ አያድርጉት ::
****************************
በለው! ከሀገረ ካናዳ
welelaye says
ልክ ነህ በለው ወንድሜ
ይሄው ነው የኔም ህመሜ
ሆኖም ቀኑን ጠብቆ ትውልዱም ይነሳል
ይህ የመከራ ግንብም ይፈርሳል
የግፈኛ እጆች ይቆለመማሉ
ብርቱዎች እንደ ሸክላ ይሰባበራሉ
ያን ጊዜ የተሰደደው ይሰበሰባል
የዴሞክራሲ ስርአትም ይመሰረታል
እመነኝ ይሄ በቅርቡ ሆናል።
በለው! says
*******************
በመሬት ከበርቴው አፈር ገፊ ጭሰኛ
በደርግ ባለመሬት ሲባል ሳይበላበትም ሳይተኛ
አሁንማ ላይኖርበትም ላይቀበርበትም ሆኖ ስደተኛ
ከቶ ምን ብክነት ምክነት ነው የትውልድ ዳተኛ?
ተው ብለናል በግዜው ጉበት ሲያድር አጥንት ነው
ውሻ በቀደደው ጅብ ሊገባ ነው…
እውነትም ንቀውናል ደፍረውናል
ከውስጥም ከውጭም ሌባና ባንዳ ሸጠውናል
ሀገሬ ተሰባብራ ህዝቤማ እንዲህ ረክሶ
ካልተወለደ ቆፍጣና የትውልድ እሬት ኮሶ
ክብርና ስሟን የማይጠብቅ መልሶ
ጥቅር ውሻ ይውለድ ሽሉ ይነሳ
ልጁ አፈር ለብሶ!
እስቲ ይሁን ልቻለው ወለላዬ !
ብሶት ሀዘን ቁጭቴ በተስፋ ይሂድ ከላዬ
ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች ነው ያለነው
የተሰደደው ተሰባስቦ ተደስቶ ያዘነው
የክፍፍል ግንብ ፈርሶ ንስሐ ገብቶ ሀጥያተኛው
አይግደለኝ የሀገሬን ድነቷን የህዝቤን ኩራቱን ሳላየው
ጌታ ሆይ፣እንደቃልህ! በሀሳባችን ፍቃድህን አክለው
በአንድነት ሲቦርቅ የክብር ሰንደቁን ከፍ ብሎ ልየው!!
****************
በተስፋ ከምስጋና ጋር በለው!