
እዩት በየቦታው የሚታደገው አጥቶ
እንዲያው ሲንከራተት ከሀገሩ ወጥቶ
ወይ አላለፈለት ወይ እፎይ አላለ
ሁሌ በባርነት እንዲሁ እንደቆዘመ
ዘመናዊ ለማኝ አስጠጉኝ ባይ ሆነ
መገፋቱ ሳያንስ መገደሉ ባሰ ።
ባርነት ባአረብ አገር
እስር በዐገር ቤት
ስደት ካገር ውጭ
ችግር በራስ አገር
እርዛት አና እስር
ሆኖል የብሶት መንደር ።
ወገን አልባው ወገን
ጠባቂ አልባው ግልገል
መንጋው ተበተነ ዋይታው ለኛ ሆነ
ገዳዩም ጠያቂ አጣ ስቃዩም ቀጠለ ።
አቤት ፍርጃ ለዛውም ጠያቂ ያጣ
ምን ይሆን ሚስጥሩ እንዲህ የመሆኑ?
ማብቂያውስ መቸ ነው እንግልት ስደቱ
አገር ሰላም ሆኖ ሰርቶ እሚኖርበት ሁሉም አንደቤቱ።
መንግስት ምን አገባኝ ጆሮ ዳባ ልበስ ካለ
ለህዝብ ለወገኑ ላገሩ ካልቆመ
የወገን ደም እንደቀለም መንገድ ላይ ሲዘራ
በባእዳን እጂ ወገን ሲሆን መቀለጃ
ቆሞ ተመልካች ሙሾ አውራጂ ብቻ
አውጋዥ ማን አረገው ጥቃት ተከላካይ አንጂ
መንጋውን ከቀበሮ ከፍየል እጂ ።
ዳሩ ምን ያደርጋል አሳዳጁ ማን ሆነና
የችግሩ መንስኤ ገፊ እና አስገዳጂ
ዘር ከገበሬ ነጥቆ መሬት ሻጭ
ከገዛ አገር ኣፈናቃይ ሰርቶ እንዳይበላ
ሰርቶ አደር ገዳይ ፍት ህን አጉዳይ
ለነጻነት ታጋይን አሸባሪ ባይ
አሳሪና ገዳይ እንዲሁም ቆሞ አስገዳይ።
ይሀው ነው ውጤቱ መንግስት ያለቦታው
ያለህዝብ ምርጫ ስልጣን ላይ መውጣቱ
ለህግ ሳይገዙ በህግ ስበብ ህዝብን ማሸበሩ ።
ይሁና የምንልበት ጊዜ አብቅቶል
የወገን ደም ያለ አግባብ ፈሶል
የራሳችንን አስተዋጾ የምናደርግበት ጊዜ
ግዴታችንን የምንወጣበት ወቅት አሁን ነው
ለሞት እምቢ ለግዞት ለባርነት
እንዲሁም ለንግልት እስከመቸ?
ተነሱ እንነሳ ድምጻችንን አናሰማ
ላለቀው ወገናችን ላለው በሰቆቃ
ደግሞም እንጩህ ወደፈጣሪያችን
አይቶ ወደሚምረው ወደ አምላካችን።
ከምስራቅ መንበሩ
Leave a Reply