• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

The Secret (ሚስጢሩ…)

November 13, 2013 06:31 am by Editor 1 Comment

ሚስጢሩ ወደኛ እየቀረበ ይሆን?

የሚስጢሩን መጽሃፍ እያሳጠርኩ በመጻፍ ላይ እያለሁ  ሚስጢሩን የሚአጠናክር ነገር ገጠመኝ። ከጓደኛዬ ጋር አልፈን አልፈን ውሃ የምንጎነጭባት ቤት አለች። እንደወትሮው በዛው ቤት ተገኝተናል። አንዲት ወጣት ስዊድናዊት ልታስተናግደን መጣች። ለጓደኛዬ የሞቀ ሰላምታ ሰጠችው። ስትስቅ ጉንጭና ጉንጮቿ ላይ የሚወጡት  ጎድጓዳ ምልክቶች አይን ይስባሉ።

‹‹ባለፈው ጊዜ  ስራ ለመቀጠር አስበሽ ያነጋገርኩሽ አይደለሽ?» አላት

«አዎን! ተቀጠርኩ በጣም አመሰግናለሁ»

«እኔ ምንም ያደረኩልሽ ነገር እኮ የለም»

«አንተ ሄደሽ ባለቤቱን ተይቂው ባትለኝ አልጠይቀውም ነበር። ስለጠየኩት ተቀጠርኩ። በድጋሚ አመሰግናለሁ»። ፈገግታዋን ከጎድጓዳ ጉንጮቿ የሚረጭ ይመስላል። ተለየችን

«ምንድነው ነገሩ? ስራ አስቀጣሪ ሆንክ እንዴ?» ጠየኩ

ባለፈው ሰሞን እዚህ መጥቼ… ይቺ ልጅ ጎኔ ካለው ጠረጴዛ ላይ ተቀምጣ ነበር። ለጓደኞቿ እዚህ ቤት ስራ ለመቀጠር እንደምትፈልግ አወራች። ጓደኞቿ ለንግግሯ ትኩረት አልሰጡትም እኔ ጣልቃ ገባሁ።

«ስራ ትፈልጊያለሽ ማለት ነው?»

«አዎን!»

«አስተናጋጅነት?»

«አዎን! ግን እዚህ ቤት ካልሆነ አልፈልግም። አንተ ባለቤት ነህ?» አያይዛ ጠየቀች

«አይደለሁም! ግን እንደምትቀጠሪ አውቃለሁ።»

«እንዴት?»

«ሂጂ ባለቤቱን ስራ እንደምትፈልጊ ንገሪው፣ አልኳት። ነገረችው፣ ይሄው ተቀጥራ አገኘኽት አለኝ።

«አንተ እንዴት እንደሚቀጥራት አወክ?»

ሚስጢሩን እኮ አነባለሁ አንዳንድ ሙከራዎችም አደርጋለሁ። ይሄ ከስኬቶቹ አንዱ ነው አለኝ። ስለ ሚስጥሩ መጽሐፉን አንብቤ፣ ከመጻፌ ውጭ የሚስጥሩን መከሰት በዓይኔ ያየሁትና በጆሮዬ የሰማሁት ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። ሚስጢሩ ወደኛ እየቀረበ ይሆን?

ወደ ዛሬው የገንዘብ ሚስጢር ላምራ

ገንዘብን ለመሳብ ሃብት ላይ አትኩሮት ማድረግ ይኖርብሃል። ጃክ ካንፊልድ

አእምሮህ የፀነስውን… ያገኛል። ደብልው ኤለመንት ሥቶኝ

የመሐፍ ቅዱሶቹ አብርሃም፤ ይስሃቅ፤ ያቆብ፤ ዮሴፍ፤ ሙሴና ኢየሱስ የብልጽግና አስተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ እራሳቸውም ሚሊኒሮችም ነበሩ። አሁን ዓለማችን ላይ ካሉ ሚሊኒሮች በላይ ሊገመት በማይችል ደረጃ የባለጸጋ አኗኗር ስልት ነበራቸው። ጀምስ ሬይ

የገንዘብ ሚስጢር

ገንዘብን ለመሳብ ሃብትን ለመጨመር

ማጣትን ትተኸው በማግኘት ላይ አትኩር

በገንዘብ እጥረት ላይ ወስደህበት ትኩረት

ተጨማሪ ገንዘብ አትችልም ለማግኘት

ማግኘት ይገባኛል ብለህ ያልከው ገንዘብ

ከኪሴ ተቀምጧል አለኝ ብለህ አስብ

ለዚህ እንዲኖርህ ተጨማሪ ስሜት

ስለ ዳበረ ሃብት ስለገንዘብ ማግኘት

ገጓደኞችህ ጋር አንስተህ ተጫወት

የማግኛ ምልከታህ እያደር ሲለውጥ

ይጀምራል መምጣት ሃብት ወዳንተ መሮጥ

በዚህ ጊዜ ደስታን እውስጥህ ማሳደር

ቀላሉ መንገድ ነው ገንዘብ ለመጨመር

ይሄንን ልገዛው በቂ ገንዘብ አለኝ

በማለት ተነሳ ትልቅ ምኞት ተመኝ

ሆኖም በመንገዱ ዝምብለህ አትሩጥ

ገንዘብን ለማግኘት ያንተንም ገንዘብ ስጥ

ገንዘብክን ስትሰጥ ተካፍለህ ስትበላ

እድል ትከፍታለህ እንድታገኝ ሌላ

በዚህ ቸርነትህ እርካታ ስታገኝ

ማለት ደፍራለህ ብዙ ገንዘብ አለኝ

በመልዕክት ሳጥንህ ወይም በግልህ ባንክ

አገኛለሁ ገንዘብ በጥሬው ወይ በቼክ

የሚል ስሜትህን ምኞትህን አዳብር

የማግኘት ሃይልህን ሚዛኑን አጠንክር

******************************

The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል አንድን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል ሁለትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል ሶስትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል አራትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

Filed Under: Literature

Reader Interactions

Comments

  1. frezer says

    November 15, 2013 02:47 pm at 2:47 pm

    its nice, but i think you should add that when you say ‘give to earn’, doesn’t mean give all you have to gain some. I believe in giving but it should be watched. I think we should give to those who need it most. And save some for ourselves.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule