ሚስጢሩ አሁን በሀይለኛ ሂደት ላይ ወቷል። እርስዎም የውለታ ምስጋናን፤የሚፈልጉትን ነገር በዓይነ ህሊና አስቀድሞ ማየትን፤የተግባር ሀይልን ሂደቶች የሚረዱበት ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ማለት ነው።ለመሆኑ አስቀድመው ይሄን ሁኔታ የተሸጋገሩ ምን ይላሉ?
ያሁኑ ማንነታችን ያለፈው አመለካከታችን ውጤት ነው።
ቡድሃ
የየቀኑ ምስጋናህ ፀጋ ወደ አንተ የሚመጣበት ማስተላለፊያ ቀዳዳ ነው
ዋላስ ዋትልስ
መተንበይ ሁሉንም ነገር ነው።የህይወት መጻኢ መስህቦች ቅድመ እይታ ነው።
አልበርት አንስታይን
ሀይለኛው ሂደት
የምትፈልገውን አጥብቀህ መጠበቅ
ሊረዳህ ይችላል ፍላጎት እንዳይርቅ
ስትተኛም ሆነ ጠዋት ስትነሳ
በያንዳንዱ ነገር ማመስገን አትርሳ
በጅህ ባለ ነገር ማመስገን ስትጀምር
መንገድ ትፈጥራለህ ሌላ ለመጨመር
የምትፈልገውን በዓይነ ህሊና
አስቀድመህ አይተህ አስተካክለውና
ማግኘትህን አምነህ ተዘጋጅተህ ጠብቅ
ነገሩም በቅርቡ እንደሚገኝ እወቅ
በመጨረሻዋ በየአንዳንዷ ቀናት
ወደ አልጋህ ስትሄድ ሳትተኛ በፊት
ወቅትን አመዛዝነህ ያልነበረን ኩነት
አመቻችተህ እደር በምትሻው አይነት።
******************************
The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል አንድን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል ሁለትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል ሶስትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
Leave a Reply