The Secret በሚል ረዕስ በሮዳን ቢይርን ተጽፎ በጋሻው አባተ ሚስጢሩ… በማለት ወደ አማርኛ የመለሰውን መጽሐፍ በአድናቆት አነበብኩ። ሚስጢሩ… ”ወዳንተ የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ወደ ሕይወትህ የምትጎትተው አንተው ነህ” ይለናል። አዎን! በእርግጥ ብዙዎች ምስክርነት ሰጥተውበታል።ይህም በመጽሐፍ ላይ ተካቶ ይገኛል። መጽሐፉ በአስራ አንድ ርዕሶች የተከፋፈለ ነው። ከዛ ውስጥ የመጀመሪያውን ዕርስ ማጠቃለያ ፍሬ ሀሳብ፤ በግጥም ስሠራው እንዲህ እንሶና ጭምቅ ብሎ ወጣልኝ። ለወገኖቼ ባካፍልስ ብዬ አሰብኩ፤ ወደናንተም ላኩት።ሁለተኛው ርዕስና ሌሎቹም ይቀጥላሉ።
የተከሰተው ሚስጢር
ሕይወት ለመለወጥ፤ የተገኘው ሚስጢር፤
ስበት እንደሆነ፤ አውቀህ ሕጉን ተማር።
የፈለከው ነገር፤ ወደ ዓለም ተልኮ
የልብህን ምኞት፤ ያመጣዋል ማርኮ።
ከንግዲህ ሕይወትህን፤ ካሻህ ለመለውጥ
መስመሩን አስተካክል፤ ፍሪኮንሲ ምረጥ።
አንተው ነህ ለራስህ፤ ሀይል ማሰራጫ
ጎትተህ አቅራቢ፤የሕይወትህን ምርጫ።
ስለዚህ ከዓለም፤ ሁሉን እንድታገኝ
በስበት ተማምነህ፤ ደህና ነገር ተመኝ።
አሁን ለምነግርህ፤ ለዚህ ለሚስጢሩ
የመረጃው ብዛት፤ በርካታ ነው ቁጥሩ።
መልዕክትና አስተያየት ካለዎት Welelaye2@yahoo.com
birhanu says
It is good book. I read it five years ago and I use it success fully .
ኦንዳለው ካሳ says
መፅሀፍን በኦዲዮ ቢለቀቅ