የጤንነት ሚስጢር ማንም ህመምተኛ የወሰደው ኪኒን ያድነኛል ብሎ ከቻለ ለማመን ስላስተላለፈ ለአዕምሮው መልዕክት በርግጥም ይችላል ጥሩ ፈውስ ማግኘት በሰውነትህ ውስጥ ህመም የሚኖረው በሽታውን ትኩረት ስትሰጠው ብቻ ነው የጤና መዛባት ስሜት ከተሰማህ ህመሙን አታስፋ ለሰዎች ተናግረህ ስዎች ስለህመም ሲያወሩ ማዳመጥ መንገዱን መክፈት ነው እንዲባባስ ይበልጥ ህመማቸው ጸንቶ ቢወተውቱ እንኳን በመልካም ነገሮች ለውጠህ ወሬውን ባነጋገር ብቃት ትችላለህ ማዳን የአዕምሮ ፈጠራን የእርጅቻለሁ እምነት ከራስህ መንጭቀህ ይገባሃል ማውጣት ወጣት ነኝ አሁንም ብለህ በማተኮር ደስታን ጤናን ይዘህ ትችላለህ መኖር ስለዚህ አረጀሁ ብለህ በመጨነቅ ህመም እያወራህ እድሜህን ከመሰቅ ራስህ ራስህን በዚህ ዘዴ ጠብቅ ****************************** The Secret … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
Literature
ጽፈኪን
ስደበኝ
ጉሮሮህን ጠራርገህ፤ ምላስህን ሳልና እንደ ሽንኩርት የምልጠው እንደ ኪኒን የምውጠው ጥሩ ቃላት ምረጥና እንደ እበት ሳትለድፍ እንደ ጭቃ ሳትለጥፍ ልክ ልኬን ንገረኝ ደስ ይበልህ…ስደበኝ ባንተ መለኪያ ተለክቸ ባንተ መነፀር ታይቸ ሙሉ እንደማልሆን አውቃለሁ ባልተገራ ምላስህ ባዶ በሆነው ራስህ ማንነቴን ስትናገር፤ ማንነትህን አያለሁ እና…አንተን ደስ እንዲልህ የተጫንከው እንዲቀልህ ……………..ስደበኝ ለአቶ ዓልምነው መኮነን የአማራ ክልል ም/ፕሬዘዳንትና የብአዴን ፅ/ቤት ኃላፊ … [Read more...] about ስደበኝ
ዕጹብ ሠዓልያን
እጅግ የረቀቀው ፤ የሰው ልጅ ሠልጥኖ እጅግ መራቀቅን ፤ ሀ ያለው ጀግኖ ለመቸውም ቢሆን ፤ ሆኖ የታደለ ለሥልጣኔው ግንብ ፤ መሠረት የጣለ ረቂቅ ሥዕላትን ፤ ነው ያኔ እንደሣለ ያለእነዚያ ሥዕሉ ፤ በአገልግሎታቸው አይገቡበት ነገር ፤ ምንም ስለሌለው እንኳን እዚህ ሊደርስ ፤ እረቆ ሊማማር ምንም ምን ለማድረግ ፤ ከቶም አይችል ነበር በዓይን የማይታዩን ፤ በመሣሪያም ቢሆን የማይዳሰሱም ፤ ብቻ የሚሰሙን የሣለ ዕለት ነው ፤ ድንቅ አድርጎ እነሱን በጆሮዎቹ ብቻ ፤ የሚያዳምጣቸውን ለተለያዩ ድምፆች ፤ መልክ ቅርጻቸውን እነ አበገደን ፤ እነ አሌፍ ቤትን የሣለ ጊዜ ነው ፤ ጥንት በድሮ ዘመን የኛ አያቶች ደግሞ ፤ በዚህ ጥበባቸው እጅግ በረቀቀው ፤ የሥዕል ሞያቸው የሚያህላቸው የለም ፤ … [Read more...] about ዕጹብ ሠዓልያን
መቼ ነው?
መቼ ነው ይሄ ቀን - ከኛ ቤት ’ሚያልፈው ለመኖር መደፋት - ተረት የሚሆነው? መቼ ነው ወገኔ - መኖር የሚችለው እንደሰው ለመኖር - ሰውን እሚመስለው? መቼ ነው ረሃቡ - ተረታሁ የሚለው እሳቱ እሳት ሁኖ - ኑሮን ’ሚያበስለው? መቼ ነው ይሄ ቀን - ተረት እሚሆነው መኖር አለመኖር - መሆኑ እሚያከትመው? … [Read more...] about መቼ ነው?
“ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”
ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣልፍቅር ያሸንፋል-- የኔ ሳይሆን የትውልድ ድምጽ ነውእዳ አለ የምንል ከሆነም፤ እዳ የሚከፈለውና የሚሸፈነው በፍቅር ብቻ ነው የፍቅር ጉዞ ከሚለው ሃሳብ እንጀምር፡፡ መነሻው ምንድነው? “አቦጊዳ ብዬ፣ ፊደል “ሀ”ን ቆጥሬ፤ የፍቅርን ትርጉም ለልቤ አስተምሬ፣ ይዤሽ በአኮፋዳ እንደቆሎ ተማሪ፣ አቦጊዳ ልበል የፍቅር ጀማሪ…” እንዲህ ነው የኔ የዘፈን ህይወት የሚጀምረው። አሁን የፍቅር ጉዞ ላይ ደርሷል፡፡ ሁላችንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ውስጥ እናልፋለን። ብዙ ቅሬታና ብዙ ደስታ፣ ብዙ ትክክል የሆኑ ነገሮችና ብዙ ትክክል ያልሆኑ ነገሮች አሉበት - ያለፍንበት ታሪክ፡፡ ትልቁ ነጥብ፣ ካለፍንበት ታሪክ ተነስተን ለሚቀጥለው ጊዜ ምን እናድርግ የሚለው ነው፡፡ ያዘንበትን ነገር በይቅርታ ሰርዘን፣ የወደድነውን ነገር ደግሞ አሳድገን … [Read more...] about “ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”
ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጅ አሸባሪ ናት ብየ አላምንም!
የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ስራዎች በቅርብ ተከታትያለሁ! ውንጀላ እስራቷን ፣ ህክምና እንድታገኝ መደረጓን እና የቤተሰብ እና የወዳጆችዋ ጉብኝት እንዳታገኝ መከልከሏን ሰምቻለሁ ! ይህ ሁሉ በዚህች የመናገር የመጻፍ ነጻነቷን ተጠቅማ ህገ መንግስታዊ መብቷን በተጠቀመች ወጣት ጋዜጠኛ ላይ የሚከፈል መስዋዕትነት ቢሆንም ስቃይ መከራዋ ፣ በደል መገፋቷ ያንገበግበኛል!እናም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ተተገፈፈቸው መብቷ ይመለስ ዘንድ በሚደረገው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ደጋፊ ነኝ ! ርዕዮት አሸባሪ አይደለችም ብየ አምናለሁና ፊርማየን ለድጋፍ ሳስቀምጥ ኩራት ይሰማኛል ! ፍትህ ለጋዜጠኛ ርዕዮትና ለመሰሎቿ ስመኝ ለኢትዮጵያስ እንኳንም ተወለድሽ የምላት አሁንም በኩራት ነው! ግጥሙን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: … [Read more...] about ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ እንጅ አሸባሪ ናት ብየ አላምንም!
ይመቻችሁ ጌቶቼ
ኩርዳዊ ነኝ ከኢራን - ኢማን አባስ እባላለሁ በቋንቋዬ እንዳልቀኝ - እንዳልከትብም ሁኛለሁ፤ የኔ ጌቶች ያሻቸውን - እሆን ዘንዳ ቢያስጨንቁኝ ግዳይ ጣልኩኝ እራሴን - ጭካኔያቸው ቢብሰኝ፤ ያውላችሁ ያሻችሁት - እንዳልሆን እሆን ፍርዳቸሁ አንደበቴን ተቆልፌ - ዐይኖቼን ተለጉሜ ይመቻችሁ እላለሁ - ጆሮቼን አስከርችሜ፤ ብእሬን ወርውሬ - ቀለሙን ደፍቼ ፍረዱኝ እላለሁ - እናንት ወገኖቼ፤ (ለምሥራቅ ኩርድ ባለቅኔው ለኢማን አባስ አመጽ መታሰቢያ) … [Read more...] about ይመቻችሁ ጌቶቼ
ሰማቹህ ወይ መርዶ
ሰማቹህ ወይ መርዶ ? ሀገር ተገምድሎ ሰማቹህ ? ወይ ነዶ!! ፤ ካገርህ ተከፍሎ ሀገርህ ተቆርጦ ፤ ለሱዳን ተሰጠ መንግሥት ነኝ ባለው ፤ ራሱን ባስቀመጠ ብለው ሲያወሩልኝ ፤ መንፈሴ ተናጠ አንጎሌ ተናጋ ፤ አቅሌ ተናወጠ ብርድ ብርድ አለኝና ፤ እያቅለሸለሸ ወይ ወደላይ አይል ፤ እንዲሁ እያሸ ባዕድ የሆነ ስሜት ፤ ሲያውከኝ አመሸ አሳድሮ አዋለኝ ፤ ሰንብቶም አልሸሸ ይሄን የሀገር ክህደት ፤ ይሄን የሞት ዜና ሙሾ ልጻፍለት ፤ ብየ ተነሣሁና ወረቀት ብዕሩን ፤ ካለበት አንሥቸ ለታሪክ ለትውልድ ፤ ከትቤ ላልፍ ትቸ ከዚህች ቀን በፊት ፤ በሀገሩ ታሪክ እንደዚህ ያለ ጉድ ፤ እንዲህ ያለ መታወክ በገዛ መንግሥቱ ፤ ለባዕድ ሲበረከት ሽንጥ ገትሮ በሐሰት ፤ ለባዕድ ሲሟገት ገጥሞት አያውቅምና ፤ ብዕሩ … [Read more...] about ሰማቹህ ወይ መርዶ
ሥራ በኢትዮጵያ
በሀገረ ሐበሻ ፤ ክቡር ነበር ሥራ የሥራ ባሕሉ ፤ ነበረ ጠንካራ በዓለም መድረክ ላይ ፤ ያደረገው አውራ ኃያል ጉልበተኛ ፤ እጅግ የሚፈራ የግዛት ሀገሩን ፤ በምዕራብ ምሥራቁ አስፋፍቶ ያስያዘው ፤ እያስገበረ ዕንቁ ዛሬ ግን ስናየው ፤ ያ አውራ ሐበሻ የቀን ጎደሎ ገጥሞት ፤ ነክሶት ክፉ ውሻ እዚህ ሀገሩ ላይ ፤ ከእሱው መዳረሻ ከቶ የማይነካውን ፤ ብዙ የሥራ ድርሻ ይህ ጨዋ የጨዋ ዘር ፤ የጌታ ልጅ ጌታ የሎሌ የባሪያ ነው ፤ ያለውን ገበታ ርቆ ይሄድና ፤ ከሩቃኑ ጓዳ ተደብቆ ከወገን ፤ ታይቶ እንዳይከዳ ያለዕረፍት ይሠራል ፤ ተግቶ አስንቆ ባዳ መጥቶ የማይነግረንን ፤ ሳያፍር ሳይጎዳ ባሪያው ከነበሩት ፤ ካሳያቸው ፍዳ ፡፡ ሥራን ወዶ ማክበር ፤ ሠርቶም ሀብታም መሆን ከጥንት ጀምሮ ፤ ነበር ባሕላችን ወደ ኋላ ግና ፤ የአውሮፓ ሚሲዮኖች አዩትና አቅሙን ፤ … [Read more...] about ሥራ በኢትዮጵያ
The Secret (ሚስጢሩ…)
ጥሩ ግንኙነት ከሰዎች ለመፍጠር ማወቅ የሚገባህ የሚስጥሩ ተግባር አመለካከትህ ያለህ አስተያየት ካፍህ የሚወጣው የንግግር ቃላት ከፍላጎትህ ጋር ግጭት እንዳይፈጥር አጢነህ ተመልከት እራስህን መርምር እራስህ እራስህን ማርካት ከተሳነህ ለሰው የምትሰጠው ምንም ነገር የለህ አክብሮት ስትሰጥ እራስህን ስትወድ ሌላው እንዲያከብርህ ትፈጥራለህ መንገድ ስለራስህ መጥፎ ነገሮች ስታስብ ለሰዎች ያለህን ፍቅር በመገደብ ለነገር ጫሪዎች ስሜት ለሚያስቆጡ መንገድ ትከፍታለህ ወዳንተ እንዲመጡ የሰዎችን ድክመት አጋነህ ከመውቀስ ጥንካሬአቸውን ጠቅሰህ ስታሞግስ አንተ በምትሻው በፈለከው መንገድ ይተባበራሉ አብረውህ ለመሄድ እንግዲህ ወዳጄ ይሄ ነው ሚስጥሩ ትልቁ ብልሀት አብሮ ለመኖሩ። ****************************** The Secret (ሚስጢሩ…) … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)