ይመቻችሁ ጌቶቼ January 18, 2014 03:10 am by Editor 1 Comment ኩርዳዊ ነኝ ከኢራን – ኢማን አባስ እባላለሁ በቋንቋዬ እንዳልቀኝ – እንዳልከትብም ሁኛለሁ፤ የኔ ጌቶች ያሻቸውን – እሆን ዘንዳ ቢያስጨንቁኝ ግዳይ ጣልኩኝ እራሴን – ጭካኔያቸው ቢብሰኝ፤ ያውላችሁ ያሻችሁት – እንዳልሆን እሆን ፍርዳቸሁ አንደበቴን ተቆልፌ – ዐይኖቼን ተለጉሜ ይመቻችሁ እላለሁ – ጆሮቼን አስከርችሜ፤ ብእሬን ወርውሬ – ቀለሙን ደፍቼ ፍረዱኝ እላለሁ – እናንት ወገኖቼ፤ (ለምሥራቅ ኩርድ ባለቅኔው ለኢማን አባስ አመጽ መታሰቢያ) Share on FacebookTweetFollow us
DASSENNECH says January 18, 2014 06:52 am at 6:52 am ከትልቅ ጥራዝ መጽሃፍ የበለጠ መልዕክት የተሸከመ ሰዕል፤ ህማ በጣም ግሩም ነው፤ አምባገነኖች የሚፈልጉት ሁሉም ህዝብ እንደ ኢማን ጆሮውም፤ አይኑም፤ አንደበቱም ታስሮ እጁ ብቻ እነሱ የሚፈልጉትን እንዲሰራ ነው፤ አበራ ለማ በጣም አመሰግናለሁ ታላቅ መልዕክት! Reply
DASSENNECH says
ከትልቅ ጥራዝ መጽሃፍ የበለጠ መልዕክት የተሸከመ ሰዕል፤ ህማ በጣም ግሩም ነው፤ አምባገነኖች የሚፈልጉት ሁሉም ህዝብ እንደ ኢማን ጆሮውም፤ አይኑም፤ አንደበቱም ታስሮ እጁ ብቻ እነሱ የሚፈልጉትን እንዲሰራ ነው፤
አበራ ለማ በጣም አመሰግናለሁ ታላቅ መልዕክት!